Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 88.65K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-01-08 20:33:15 ትምህርት ሰፍቷል ስብዕናችን ወርዷል
ቡርሀን አዲስ
ክፍል -1
አቅራቢ -ትዕግስት አንተንጉስ

ክፍል-2

@zephilosophy
@zephilosophy
2.3K viewsedited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 08:49:13
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
3.0K viewsedited  05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 17:07:27 እውነት ምንድነው?

ምንጭ ፦ የፍልስፍና አፅናፍ
ፀሀፊ ፦ አለማየሁ ገላጋይ

በአንዳንድ መመዘኛዎች አብዛኛው ሰው እውነት ብሎ የተስማማበት ነገር ከሞላ ጐደል እውነትነት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ይሁንና ይሄ ብያኔ ከብዙ የእውነታ ማረጋገጫ መንገዶች አንዱ እንጂ የመጨረሻ ማጠቃለያው እንዳልሆነ ልብ ማለት ይገባል፡፡ ስለዚህ አንተም ሆንክ የሀዲስ ኪዳኑ ጲላጦስ «እውነት ምንድር ነው?›› ስትሉ ለጠየቃችሁት የጓደኞችህ መደምደሚያ አርኪ ምላሽ አይሆንም።

ከሁሉም በፊት ውሸት እንድንናገር የሚገፋፉን ነገሮች ምንድን ናቸው ብለን መነሳት የእውነትን ተፈጥሮ መርምሮ ለማግኘት ይረዳናል:: አንድ ሰው እንደማያፈቅራት ልቡናው የሚያውቀውን ሴት ‹‹አፈቅርሻለሁ› ቢል ውሸት ተናግሯል ማለት ነው:: ወይም አንድ ልጅ የብስኩት ማስቀመጫውን አድፋፍቶ እያለ እናቱ ስትጠይቀው ‹‹አላደረኩም›› ቢል ዋሽቷል፡፡ ውሸት ማለት የምታውቀውን የምታስበውንና የሚሰማህን ክደህ መናገር ነው፡፡ እንዲህ ያለው ድርጊት በየዋህነት ወይም በስህተት ከሚፈፀመው የተለየ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ የእግር ኳስ ዳኛ በአጠራጣሪ ሁኔታ የገባን ጎል ቢሽር ማለት ነው፡፡

የቅርብ ጊዜው አሜሪካዊው ታላቁ ፈላስፋ ጆሲያህ ሮይስ (Josiah Royce) ለውሸት ትርጓሜ ሲሰጥ የሰው ልጅ ይሆነኝ ብሎ የድርጊት መወከያ ቃላቱን በማቀያየር የሚያውቀውን እውነታ ሲቃረን ነው ይላል፡፡ «አይደለም» መባል የሚገባውን «ነው በሚልበት ጊዜ፤ ወይም «ነው» ማለት ሲገባው «አይደለም›› ለማለት ሲደፍር። ሮይስ ውሸትን የፈታበት መንገድ ወደ ጥንታዊ የእውነት ትርጓሜ ይመራናል፡፡ ከ2ሺህ 5 መቶ አመታት በፊት ፕሌቶና አርስቶትል በዚሁ መንገድ ለእውነትና ውሸት ብያኔ ሰጥተው ነበር፡፡

ፕሌቶና አርስቶትል እንደሚሉት የጨበጥነው አስተያየት ትክክለኛ መሆኑ የሚረጋገጠው <<ነው» መባል ያለበት <<ነው» ተብሎ ሲገኝ ወይም ‹‹አይደለም› መባል የሚገባው «አይደለም» ሲባል ነው፡፡ በአንፃሩ አስተያየታችን ሐሰት ሆኖ የሚገኘው ደግሞ የተገላቢጦሽ «ነው› መባል ያለበት <<አይደለም» በሚል ተለውጦ ሲገኝ ወይም ‹አይደለም›› በ«ነው» ተተክቶ ስናገኘው ነው፡፡ ፕሌቶና አርስቶትል እንደሚሉት የአስተያየታችን እውነትነት የሚረጋገጠው ከገሃዱ ዓለም ተጨባጭ ሁናቴና ከተፈጥሮ ህግ ጋር እየተመሳከረ ይሆናል፤ አስተያየታችን ከገሃዱ ዓለም ሆነ ከተፈጥሮ ህግ ጋር የተስማማ ሆኖ ከተገኘ እውነትነት ሲኖረው በአንፃሩ ከተጣረሰ ደግሞ ስህተት ተናግረናል ማለት ይቻላል ይላሉ፡፡

ስለዚህ ከላይ እንደተመለከትነው የእውነታን ምንነት አንጥሮ ማውጣት በጣም ቀላል ነው:: ፍቺውንም መረዳት ያን ያህል አዳጋች አይደለም፡፡ ጲላጦስ ኢየሱስን ስለእውነት ምንነት ሲጠይቅ ምናልባትም ምላሹ በኋላ ለሌላ ጥያቄ እራሱን አዘጋጅቶ ነበር «የተነገረን እውነት ይሁን ሐሰት እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? በነገራችን ላይ አንተና ጓደኞችህ ስለእውነት መቋጫ ለመስጠት የሞከራችሁት ለዚህ ለጲላጦስ ያልተጠየቀ ጥያቄ ምላሽ በመሻት ነበር የተነገረን እውነት ይሁን ሐሰት እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?››

ለዚህ ጥያቄ ሶስት ዋና ዋና ምላሾች አሉ፡፡ አንዳንዱ ጉዳይ በራሳችን ተጨባጭ እውነታ የምንዳኘው ነው፡፡ «ድፍኑ ከቁራሹ ይበልጣል›> ይሄ እውነት በራሳችን አይተን ያረጋገጥነው በመሆኑ በየትኛውም አግባብ ተቀይሮ ቢመጣ ልንቀበለው የሚያዳግተን ነው፡፡ ድፍኑን እናውቃለን፤ ቁራሹንም እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ቁራሹ ከድፍኑ ሊበልጥ የሚችልበት አንድም መንገድ የለም፡፡ የአንዳንድ ነገር እውነትነት የምናረጋግጥበት አግባብ ቁራሹ ከድፍኑ የአለመብለጡ እውነታን መመዘኛ አድርገን ነው፡፡

ሁለተኛው እውነታን የማረጋገጫ መንገድ ደግሞ ልምድ ወይም ምልከታን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ አንድ ሰው ያለፈው አንድ ወር ሙሉ ቺካጐ ውስጥ አንዴም አለመዝነቡን ቢነግረን ሜትሮሎጂ ያዘጋጀውን የአየር ንብረት ሁኔታ መዝገብ በመመልከት ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ወይም ስለመዋኛው ገንዳ ውሃ ሙቀት ቢነግረን አንድ እግራችንን ሰደድ አድርገን ማረጋገጥ ነው። እዚህ ላይ ሳይንስ ነክ ማጠቃለያዎች እንደ እውነታ የሚወሰዱት ተቃራኒ ሐሳብ እስካላጋጠማቸው ጊዜ ድረስ ብቻ ነው።

ሶስተኛው መንገድ በራሳችን ተጨባጭ እውነታ ሆነ በሶስተኛ ወገን ማረጋገጫነት የምንዳኘው እውነታ ሲያጋጥመን የምንጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ ለምሳሌ ስለአንድ ሰው ባህርይ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ስለአንድ ምርት ውጤታማ አገልግሎት እንዲህ ያለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው ድምፅ በማሰባሰብ ሂደት አብላጫ ተቀባይነት ያለውን በመለየት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አብላጫ ድምፅ ያገኘ ነገር እንደ እውነት የመቆጠር እድሉ እጅግ በጣም ሰፊ ነው::

ይሄ ሶስተኛው የእውነታ ማረጋገጫ መንገድ ጓደኞችህ በደፈናው የነገሩህ መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን አብዛኛው ሰው በደፈናው የተስማማበት ነገር «እውነት ምንድነው» ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ ሰጪ አይሆንም፡፡ የዚያኑ ያህል የተሟላ ምላሽም ሊሆን አይችልም፡፡

እውነትን መግለጽ ቀላል ነገር ነው:: የሚነገረንን እውነት ይሁን አይሁን ለይቶ ማውቁ የበለጠ ከብዶ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የራስን እውነት ለሌሎች ለማስረዳት መሞከር ዋነኛው አዳጋች ጉዳይ ነው፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.5K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 12:00:06 በፍቅር መድፈር

ምንጭ ፦ ህያውነት (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ሀብታሙ ተስፋዬ

በጥልቀት ካፈቀራችሁ ፍርሃት ድራሹ ይጠፋል፡፡ ፍርሃት እጦት፣ አሉታዊ ነገር ነው፡፡ ይህንን በጥልቀት ልትገነዘቡት ይገባል፡፡ ይህን ግንዛቤ ካልጨበጣችሁ የፍርሃትን ባህርይ ልትረዱ አትችሉም፡፡ ፍርሃት እንደጨለማ ነው:: ጨለማ የሌለ ቢሆንም ያለ ይመስላል፡፡ ጨለማ የብርሃን እጦት ነው:: ብርሃን ግን አለ፤ ብርሃኑን ካስወገዳችሁት ጨለማው ብቅ ይላል::

ጨለማ የለም፤ ጨለማን መግፈፍ አትችሉም፤ የፈለጋችሁትን ነገር ብታደርጉ ጨለማን ማስወገድ አትችሉም፣ ልታመጡት ወይም ልትወረውሩት አትችሉም፡፡ ጨለማን አንድ ነገር ማድረግ ከፈለጋችሁ ብርሃንን መጠቀም ይኖርባችኋል፣ ምክንያቱም አንድ ነገር ማድረግ የምትችሉት ህያው የሆነን ነገር ነው:: መብራቱ ስታጠፉት ጨለማ ይሆናል፤ መብራቱን ስታበሩት ጨለማ አይኖርም - በብርሃን አንድ ነገር ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ጨለማን ግን ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡

ፍርሃት ጨለማ ነው፣ የፍቅር እጦት ነው፡፡ ምንም ልታደርጉት አትችሉም። ልታስወግዱት ብዙ በጣራችሁ ቁጥር የበለጠ ፈሪ ትሆናላችሁ- ምክንያቱም የበለጠ የማይቻል ይሆንባችኋል፤ችግሩ ይበልጥ ውስብስብ ይሆናል፡፡ ጨለማን ከታገላችሁት ትሸነፋላችሁ፡፡ ጐራዴ ይዛችሁ ጨለማን ልትገድሉት ብትሞክሩ ትርፉ ድካም ብቻ ነው፡፡ በመጨረሻም አዕምሮ “ጨለማ ሃይለኛ ስለሆነ ነው የተሸነፍኩት” ይላል፡፡

ይሄን ጊዜ ነው ምክንያታዊ አስተሳሰብ ስህተት የሚሆነው፡፡ ሁኔታው ፍፁም ስነ-አመክኖያዊ ነው ከጨለማ ጋር ታግላችሁ ልታሸነፉ ወይም ልታጠፉት ካልቻላችሁ “ጨለማ በጣም፣ በጣም ሃይለኛ ነው፡፡ እኔ ከእሱ ጋር ስነፃፀር ደካማ ነኝ” ብሎ ማሰብ ትክክለኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ እውነታው ግን የተለየ ነው፡፡ እናንተ ሳትሆኑ ጨለማው ነው ደካማ፡፡ በእርግጥ ጨለማው እዚያ ስለሌለ ነው ልታሸንፉት ያልቻላችሁት፡፡ የሌለን ነገር እንዴት ማሸነፍ ይቻላል?

ከፍርሃት ጋር አትታገሉ፣ አለበለዚያ የበለጠ ፈሪ ትሆናላችሁ፡፡ አዲስ ፍርሃት በውስጣችሁ ይገባል፡፡ ፍርሃትን መፍራት ነው በጣም አደገኛው ነገር፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርሃት እጦት ነው፡፡ ሁለተኛው ነገር ፍርሃትን ፍራቻ፣ እጦትን ማጣት ነው፡፡ ከዚያም ወደ እብደት ታመራላችሁ!

ፍርሃት ምንም ሳይሆን የፍቅር እጦት ነው፡፡ ፍርሃትን እርሱትና በፍቅር አንድ ነገር አድርጉ፡፡ በደንብ ካፈቀራችሁ ፍርሃት ይጠፋል፤ በጥልቀት ካፈቀራችሁ ፍርሃት ድራሹ ይጠፋል፡፡

ለአንዲት ቅፅበት እንኳን አንድን ሰው አፍቅራችሁ ፈርታችሁ ታውቃላችሁ? ሁለት ሰዎች ተገናኝተው በጥልቅ ፍቅር ከወደቁ - ለአንዲት ቅፅበት እንኳን ቢሆን በመሃላቸው ፍርሃት አይኖርም፡፡ መብራት በርቶ ጨለማ ሳይኖር አነድ ሚስጥራዊ ቁልፍ አለ - ፍቅር፡፡

በህያውነታችህ ውስጥ ፍርሃት እንዳለ ከተሰማችሁ የበለጠ አፍቅሩ። በፍቅር ድፈሩ፣ ደፋር ሁኑ፤ የፍቅር ጀብደኛ ሁኑ፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የበለጠ አፍቅሩ፣ የበለጠ ባፈቀራችሁ ቁጥር ፍርሃታችሁም የዚያኑ ያህል ይቀንሳል፡፡

ፍቅር ስል ከፆታ እስከ ሳማዲ ያሉትን እርከኖች ማለቴ ነው፡፡ በጥልቀት አፍቅሩ።

በፆታዊ ግንኙነት በጥልቀት ካፈቀራችሁ ከአካላችሁ ብዙ ፍርሃት ይወገዳል፡፡ ሰውነታችሁ በፍርሃት የሚንቀጠቀጥ ከሆነ የፆታ ፍርሃት አለባችሁ ማለት ነው፤ ከዚህ በፊት በጥልቅ የፆታዊ ግንኙነት ውስጥ አልነበራችሁም፡፡ አካላችሁ ሲንቀጠቀጥ ሰውነታችሁ አልተረጋጋም ማለት ነው፡: .

በጥልቀት አፍቅሩ - ወሲባዊ እርካታ ፍርሃታችሁን በሙሉ ጠራርጐ ያጠፋባችኋል፡፡ ፍርሃታችሁ ተጠራርጐ ይጠፋል ማለት ደፋር ትሆናላችሁ ማለት አይደለም፡፡ ደፋሮች የፈሪዎች ግልባጮች ናቸው:: ፍርሃት በሙሉ ተጠራርጐ ይጠፋል ስል ፍርሃትም፣ ድፍረትም አይኖሩም ማለቴ ነው፡፡

ደፋር የምትሉዋቸውን ሰዎች ተመልከቷቸው:: በውስጣቸው ጥልቅ የሆነ ፍርሃት እንዳለባቸው ትገነዘባላችሁ፣ ከውጭ ሸፋን አበጅተው ነው ደፋር የመሰሉት፤ ድፍረት ፍርሃት አልባነት አይደለም:: ድፍረት ጥሩ መከላከያ፣ ከለላ፣ ጥሩር ያለው ፍርሃት ነው፡፡ "

ፍርሃት ሲጠፋ ፍርሃት አልባ ትሆናላችሁ፡፡ ፍርሃት የሌለበት ሰው በማንም ላይ ፍርሃትን አይለቅም፤ ሌላም ሰው ፍርሃት እንዲያሳድርበት አይፈቅድም፡፡

ጥልቅ የሆነ ወሲባዊ እርካታ አካልን ያረጋጋል፡፡ ሰውነት ምሉዕነት - ስለሚሰማው በጣም፣ በጣም ጥልቅ የሆነ ጤንነት በአካላችሁ ይሰራጫል፡፡

ሁለተኛው ደረጃ ፍቅር ነው። ሰውን ያለ ገደብ አፍቅሩ በአእምሮአችሁ ውስጥ አንድ የሚገድባችሁ ነገር ካለ ማፍቀር አትችሉም። እነዚያ ሁኔታዎች እንቅፋት ይሆኑባችሗል። ፍቅር አስፈላጊያችሁ ከሆነ ስለ ሁኔታዎቹ ለምን ትጨነቃላችሁ? ያለ ገደብ በጥልቀት ማፍቀር በጣም አስፈላጊ ነው - በምላሹ ምንም አትጠይቁ ሰዎችን በመውደድ ምክንያት ብቻ ፍርሃት አልባነትን ማዳበር ከቻላችሁ ለደስታችሁ ስትሉ ብቻ ታፈቅራላችሁ?

ተራ ሰዎች ሁኔታዎቻቸው ሲሟሉሏቸው በቻ ያፈቅራሉ፡፡ “እንዲህ ከሆነክ ብቻ ነው የማፈቅርህ” ይላሉ፡፡ እናት ልጅዋን “ፀባየኛ ከሆንክ ብቻ  እወድሃለሁ” ትለዋለች፡፡ ሚስት ባሏን “እንዲህ ከሆንክ አፈቅርሃለሁ” ትለዋለች፡፡ ሁሉም ሰው ቅድመ - ሁኔታ ሲያስቀምጥ ፍቅር ይጠፋል፡፡

ፍቅር ወሰን የሌለው ሰማይ ነው! ልታጠቡት፣ ልትወስኑት አትችሉም፡፡ ቤታችሁ ውስጥ ንፁህ አየር አስገብታችሁ መስኮቶቻችሁንና በሮቻችሁን ብትቆላልፉ ብዙም ሳይቆይ የታመቀ ይሆናል፡፡ ፍቅር የሚመጣው በነፃነት ነው፡፡ ያን ንፁህ አየር ወደቤታችሁ አስገብታችሁ እንደቆለፋችሁበት ወዲያውኑ ሁሉም ነገር የታመቀ፣ ቆሻሻ ይሆናል።

ይህ የጠቅላላ ሰው ችግር ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሰዎች በፍቅር ሲወድቁ ሁኔታዎችን ስለማይደረድሩ ሁሉም ነገር መልካም ይመስላል፡፡ የተፈቀሩት ሰዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይቀራረባሉ፡፡ ከተረጋጉ በኋላ፣ ፍቅር መሰጣጠት ከጀመሩ በኋላ፣ ቅድመ - ሁኔታዎች ይመጣሉ፡፡ ፍቅር የገበያ ዕቃ ይመስል “ይሀን ካልመሰልክ፣ እንዲህ ካልሆንሽ” ይባባላሉ፡፡

በሙሉ ልባችሁ ካላፈቀራችሁ እየተደራደራችሁ ነው:: ሌላኛውን ሰው የሆነ ነገር ካላደረግክልኝ እያላችሁ እያስገደዳችሁ ነው፡፡ ይህ ቅድመ ሁኔታችሀን ካልተሟላ ፍቅራችሁን ትከዳላችሁ፡፡ አሁን እያፈቀራችሁ ሳይሆን ፍቅራችሁን እንደ መቅጫ፣ እንደማስገደጃ እየተጠቀማችሁበት ነው:: ፍቅር ተቀባይ ወይም ፍቅር ሰጪ ብትሆኑም በሁለቱም መንገድ ፍቅር መጨረሻ አይደለም፡፡

ያገባችሁ ከሆነ ለሚስታችሁ ስጦታ ይዛችሁላት ትሄዳላችሁ - ይሄን ጊዜ ደስ ብሏት እያቀፈች ትስማችኋለች፡፡ ወደ ቤታችሁ የሆነ ነገር ይዛችሁ ካልገባችሁ ግን መራራቅ ይፈጠራል፡፡ እንኳን ልትስማችሁ አጠገባችሁ አትደርስም፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ስታደርጉ ፍቅር ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእናንተም ጠቃሚ እንደሆነ ዘንግታችኋል ማለት ነው፡፡ ፍቅር የሚጠቅመው አፍቃሪዎችን ነው፤ የተፈቀሩትንም ይጠቅማል፡፡

ሰዎች ወደ እኔ ይመጡና “ጓደኛዬ አያፈቅረኝም” ይላሉ፡፡ “እኔ አላፈቅረውም ብሎ የሚመጣ የለም:: ፍቅር ማስገደጃ ሆኗል፡፡ “ጓደኛዬ አያፈቅረኝም።" ስለሌላው እርሱ! ፍቅር እጅግ ድንቅ ክስተት ነው፡፡ ስታፈቅሩ ደስተኛ ትሆናላችሁ፡፡

ብዙ ባፈቀራችሁ መጠን ደስተኛ መሆናችሁም በዚያው ልክ ይጨምራል። ፍቅራችሁ ባነሰ ቁጥር ሌሎች እንዲያፈቅሯችሁ ትጠብቃላችሁ፤ ደስተኛነታችሁ ይቀንሳል፤ የበለጠ ውስን ትሆናላችሁ፤ የራስ ኩራታችሁ ጥገኛ ትሆናላችሁ::

@Zephilosophy
@Zephilosophy
31 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 13:52:00 ጤንነት ምርጫ ነው
በዶ/ር ዳዊት መንግስቱ

Credit to dawit dreams
@Human_Intelligence
1.2K viewsedited  10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 11:46:30 የደስተኝነት ምስጢሮች

ደስተኝነት እንዲያው በዘፈቀደና እንደ አጋጣሚ ሳይሆን በፍላጎት ወይም ደስተኛ መሆንን በመምረጥ እንዲሁም ደስተኛ ለመሆን በመዘጋጀት ሊገኝ የሚችል በጎ ስሜት ነው፡፡
   ደስተኝነትን ለማዳበር የሚረዱ አምስት        ምስጢራት
ተስፈኝነት ፦ ተስፈኛ ሰዎች በብርጭቆ ውስጥ በከፊል የሞላን "ውሀ ግማሽ ሙሉ " ብለው ሲጠሩት ተስፈኛ ያልሆኑት ፀለምተኞች "ግማሽ ጎዶሎ" ይሉታል፡፡ ተስፈኞች ህልማቸው ሊሳካ የሚችለው አዎንታዊውን የአስተሳሰብ መንገድ በመከተል እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ተስፈኝነት የአዎንታዊ አስተሳሰብ ትሩፋት ሲሆን የደስተኝነትም ዋነኛ ግብአት ነው፡፡
  ትህትና ፦ ደስተኛ ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ትሁትና አዛኝ መሆንን ይመርጣሉ። ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን የሚያስተናግዱበት መንገድ ለሚሰማቸው ስሜትና በአጠቃላይም የማንነታቸው መገለጫ መሰረት እንደሆነ ይገነዘባሉ።
ይቅር ባይነት ፦ ደስተኛ ሰዎች የጎዷቸው ሰዎች ላይ እንኩዋን ቢሆን የቂም እና የበቀል ስሜቶችን በውስጣቸው አምቀው ማቆየት የሚቻላቸው አይደሉም። በሰዎች ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ የሚያበሳጭ ፣ የሚያስቀይም እና የሚያስከፋ ፀባይ ጠፍቶ የማያውቅ ቢሆንም ደስተኞችን ልዩ የሚያደርጋቸው ባህሪይ ግን በእንዲህ ያለው ስብእና መጠለፍ ፈፅሞ የማይፈቅዱ መሆናቸው ነው። ደስተኞች በሌላው ፀባይ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ሀዘኔታ የሚሰማቸው ናቸው።
በፀጋ መቀበል ፦ ደስተኛ ሰዎች መቆጣጠር የሚችሉትንና የማይችሉትን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች ግን ሁሉንም ሰው ወይም ሁኔታ ለመለወጥ ሁልጊዜ ጥረት እንዳደረጉ ናቸው። በዚህ የተነሳ ዘወትር ምቾት የማጣት ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል። ደስተኞች ግን በምንም አይነት ሁኔታ ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደማይችሉ ፣ እንደማያስፈልጋቸው ጭምር ስለሚረዱ መላ ትኩረታቸውን መቆጣጠር በሚችሉት ነገር ላይ ያሳርፋሉ።
አመስጋኝነት ፦ ደስተኛ ሰዎች የሌሏቸውን ነገሮች በማሰብ ምሬት ውስጥ የሚገቡ ሳይሆኑ ስላላቸው ነገር የሚያመሰግኑ ናቸው። መስማት ፣ መናገር ፣ ማየት ወይም መራመድ ያልታደሉት እንኳን በርካቶቹ ደስተኞች የሚሆኑበት ምስጢር ትኩረታቸውን ባጡት ነገር ላይ ሳይሆን ባሏቸው ነገሮች ላይ ማድረግ መቻላቸው ነው።

ምንጭ ፦ ስድስተኛው ስሜት
ትርጉም ፦ ፍቅሩ በለጠ

@Human_Intelligence
1.9K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 19:04:29 1. ስኬትህ የምታደርገው ነገር ነፀብራቅ ነው

ከቀደመው ማንነታችን የተሻልን ለመሆን ጥረት ባደረግን ቁጥር በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ የተሻሉ መሆን ይጀምራሉ።

~ የተሻለ ሰው መሆንህ በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ማለትም የአኗኗር ዘይቤህን፣ ቤተሰብህን፣ ጓደኞችህን፣ ማህበረሰብህን የሚጠቅም ተዘዋዋሪ ተጽእኖ ይፈጥራል።


2. የምናብ ሰው ሁን

" አለምን የማየው እንዲከሰት ከምፈልገው ነገር አንፃር እንጂ ከሚታየው ነገር አንፃር አይደለም።"

~ ሰዎች ዓለምን እንዳለች መቀበልን ቢመርጡ ኖሮ ታላላቅ ፈጠራዎች አይከሰቱም ነበር።

~ ታላላቅ ስኬቶች እና ፈጠራዎች ‘አይቻልም’ የሚል አስተሳሰብን ችላ በማለት ይጀምራሉ።

3. በራስህ መንገድ ላይ አተኩር

ሌሎች ሰዎች ተጽእኖ ሊያሳድሩብህ ይችላል፤  ነገር ግን የሌላ ሰው ህይወት መኖር ከጀመርክ ግራ የተጋባ ሰው ትሆናለህ።

~ ምክር መቀበል እና ከሌሎች መማር ምንም ችግር የለውም፣ ነገር ግን የምትሄድበት መንገድ ከአንተ ፍላጎት እና ዝንባሌ ጋር የሚስማማ መሆኑን አረጋግጥ።

4. አሰልቺውን ተመሳሳይ ህይወት ስበረው

እያንዳንዱ ቀን ከቀጣዩ ቀን ጋር ተመሳሳይ በሚሆንበት ጊዜ ሰዎች በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚከናወኑትን መልካም ነገሮች ለይተው ማወቅ ስለሚያቅታቸው ነው።

~ ምስጋና በእያንዳንዱ ቀን ውስጥ ጥሩውን የማግኘት ልምምድ ነው።

5. ፍርሃት ከሚያጋጥምህ ማንኛውም እንቅፋት የበለጠ ትልቅ እንቅፋት ነው።

~ ፍርሃትህን አትፍራው ብትፈራውም ከማድረግ አታፈግፍግ!

6. አሁንን ተቀበል
ሁልጊዜ አሁን ባለህ ነገር ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ።

~ ባለፈው መኖር እና ያለፈው ህይወትህ አንተን እንዲገልፅ መፍቀድ ወይም ስለወደፊቱ መጨነቅ ምንም ፋይዳ የለውም። 

7. ወስን
አንድ ሰው ሲወስን፣ መጀመሪያ ውሳኔውን ሲወስን አያውቃቸው ወደነበሩ ቦታዎች የሚወስደው ኃይለኛ ፍሰት ውስጥ እየገባ ነው።

~ ድርጊት በውሳኔህ ላይ ከመተማመን የሚመነጭ ነው።  አጥር ላይ መቀመጥ የትም አያደርስም። ስለዚህ ወስን! የውሳኔ ሰው ሁን!

8. ሁልጊዜ እርምጃ ውሰድ

" ለመማር አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፤  ይህም ተግባር ብቻ ነው""

9. እንደገና መነሳትህን ቀጥል

" የሕይወት ምስጢር ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።"
ምክንያቱም ስምንተኛው ጊዜ የአንተ ግኝት ሊሆን ይችላል።

@Human_Intelligence
1.7K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 08:19:12 Lesson for a New year

ራስን መቀየር የሚያስችሉ የህይወት መርሆች
በዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ

@Human_Intelligence
800 viewsedited  05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 08:07:03 ወይ አክሙት!
ወይ አክስሙት!

የእግዜር ቃል አይደለም
አልወረደ ከላይ፣
ያጣነው እልፍነው
ከፊደሉ በላይ!

ሰማያዊ ልባስ
በውስጡ መርዝ ይዞ
ስንቱ መንገድ ሳተ
ያቺን አንቀፅ መዞ

አውጡት ከፓርላማው
አቡሽ ዘለቀ
2.2K viewsedited  05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 22:30:30 ሊሞቱ 3 ወር የቀራቸው ሰዎች ባለማድረጋቸው የሚቆጫቸው አስር ነገሮች

Lesson for a Life Time
በዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ

@Human_Intelligence
1.7K viewsedited  19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ