Get Mystery Box with random crypto!

አዳብና መልቲ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ adabnamidea — አዳብና መልቲ ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ adabnamidea — አዳብና መልቲ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @adabnamidea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 817

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-30 13:31:06
የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር አዲሱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ሳሙኤል

ህዝብን ማገልገል መመረጥ ነው።
10 views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 13:05:08
ከአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ አጭር መግለጫ

የማህበራችን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተለዉን ውሳኔ አሳልፏል።
****
እንደሚታወቀው የማህበራችን መስራችና ፕሬዝዳንት አቶ ዘፀአት ቱቼ  ለማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  መልቀቂያ  ማስገባቱ ይታወቃል።በመሆኑም የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች መልቀቂያውን ተቀብለን በተከታታይና በጥልቀት ከተወያየን በኋላ የአመራር ሽግሽግ በማድረግ የማህበራችን ም/ል ፕሬዝዳንት የነበረው አቶ ኢሳያስ ሳሙኤል አቶ ዘፀአት ቱቼን ተክቶ ማህበሩን በፕሬዝዳንትነት እንዲመራ በሙሉ ድምፅ ወስነናል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ዘፀአት ቱቼ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ በመሆን የማስተባበሩ ስራ እንዲያግዝና ማህበሩ የጀመራቸው በጎ ስራዎች አዲስ ከተሾመው የማህበሩ ፕሬዝዳንት  ጋር በመሆን ወደፊት እንዲያስቀጥል ውሳኔ አሳልፈናል።በዚህ አጋጣሚ ለማህበራችን አባላትና በአጠቃላይ ለጉራጌ ተወላጆች ማህበራችን በቅርቡ ለሚጀምራቸው እንስቃሴዎች የማህበሩ አባል በመሆንና በመሳተፍ፣በማስተባበር፣በእውቀትና በገንዘብ በማገዝ ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።


የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ሚያዚያ 20/2015
አዲስ አበባ

አይመለል ቆርኛን
40 views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 07:44:37
7 views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 08:26:23

216 views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 03:46:45 ምሩ ገረ
አዲሱ የመስፍን ሲማ ሙዚቃ ክሊፕ ተለቋቋል።



182 viewsedited  00:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 16:02:58
329 views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 21:14:24 ገና በክስታኔ ቤተ ጉራጌ
**
የገና በዓል በክስታኔ ጉራጌ ዘንድ በአብዛኛው በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተለመደው ሃይማኖታዊና ባህላዊ የገና አከባበር እንዳለ ሆኖ ነገር ግን በክስታኔዎች ዘንድ ሌሎች ሃይማኖታዊ ትውፊት ያላቸው ባህላዊ ክንዋኔዎች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ዪምር ዪምር፣፣አንቃትና፣እንዞሪቴ የሚጠቀሱ ናቸው።
በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ ገና ላይ ከሚከውኑ ባህላዊ ክንውኖች አንዱ ዪምር ዪምር ነው።ዪምር ዪምር በአንድ መንደር የሚኖሩ ልጃገረዶችና ወጣቶች የገና ዕለት ወንፊት ፣ጠላ በጣሳና በቂቤ የታሸ የገብስ ቆሎ ይዘው በመንደሩ ቀጣይ በምታገባው ልጃገረድ ግቢ ውስጥ ባለ መስክ ላይ በሰብስበው ያያዙትን ወንፊት ወደ ፀሀይ አቅጣጫ (ወደ ምስራቅ) በማንሳትና ፊታቸውን በያዙት ወንፊት በመሸፈን "ዪምር ዪምር አንድ፣ ዪምር ዪምር ሁለት... "እያሉ እስከ 12 ጊዜ ከቆጠሩ በኋላ የያዙትን ወንፊት ወደ መሬት ወርውረው በመጣል ወጣቶች የሚያከብሩት ስነስርዓት ነው።በመቀጠል ወጣቶቹ እስከ 12 ጊዜ ዪምር ዪምር ካሉ በኋላ የያዙትን ወንፊት ወርውረው ይጥሉታል።በመቀጠልም እያንዳንዳቸው ይዘው የመጡትን ጠላና በቂቤ የታሸ ቆሎ አንድ ላይ በማደባለቅ ቆለው እየበሉ ጠላውን እየጠጡ ጫወታቸው ይቀጥላሉ። በመጨረሻም ዪምር ዪምር ብቅ ቤል የዳኮኛ(የሚትኛ) ጠላት ጠክ ቤል" በማለት የዪምር ዪምር ስነስርዓታቸው ያጠናቅቃሉ።
የዪምር ዪምር ትውፊታዊ አመጣጡ
በክስታኒኛ(ጉራጊኛ) ቋንቋ ዪምር ማለት ፀሀይ ወይም ኮከብ ማለት ሲሆን ዪምር ዪምር ማለት ደግሞ ፀሀይ ፀሀይ ወይም ኮከብ ኮከብ ማለት ነው።የዪምር ዪምር ጥሬ ትርጉሙ ይሄ ከሆነ የልጃገረዶችና ወጣቶቹ ወደ ፀሀይ አቅጣጫ በመዞር ፊታቸውን በወንፊት በመጋረደ "ዪምር ዪምር አንድ ..." እያሉ 12 ጊዜ መቁጠራቸው ትርጉሙ ምንድነው የዪምር ዪምር ስነስርዓት ከገና በዓል ጋር ያለው አጠቃላይ ስዕልና ቁርኝት እንዲሁም ሃይማኖታዊ ዳራው ለመረዳት እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው።የልጃገረዶቹና የወጣቶቹ ፊታቸውን ወደ ፀሀይ አቅጣጫ በማዞርና በወንፊት በመጋረድ 12 ጊዜ "ዪምርዪምር አት፣ ዪምር ዪምር ኪት፣ዪምር ዪምር ሶስት..." እያሉ መቁጠራቸው ሰባሰገል የክርስቶስን መወለድ ያበሰራቸው የምስራቅ ከከብ ተከትለው እየሱስ የተወለደበት ስፍራ ለመድረስ ያደረጉትን ፍለጋ የሚያሳይ ነው በማለት የአካባቢው የአይማኖት አባቶች እና ሽማግሌዎች ይናገራሉ። ሰባ ሰገል(ሰባሰገል ማለት በግዕዝ የጥበብ ሰዎች ማለት ነው) ከምስራቅ ተነስተው ወደ እየሩሳሌም ከመድረሳቸው በፊት እንደመፅሐፍ ቅዱስ ገለፃ የምስራቋ ኮከብ አንዳንዴ ትሰወርባቸው ነበር።ሰባሰገሎችም ጎዞቸው ለመቀጠል ሰማይ ላይ ካሉት እልፍ አህላፍ ከዋክብት የምስራቋን ኮከብ ፈልገው ማግኘት ግድ ይላቸው ነበር።
አባቶች እንደሚናገሩት ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በተወለደበት ጊዜ ሰባሰገል በምስራቅ ኮከብ ምሪት ወደ ተወለደበት ሥፍራ በመሄድ ሰግደው እጣንና ከርቤ በስጦታ ካበረከቱበት ሂደት ጋር በማያያዝ 'ይምር ይምር'' በማለት በወንፊቱ ቀዳዳዎች የሚታየው ከኮከቦች መካከል የሚፈለገው ኮከብ ፀሀይ ሲወጣ ጨለማን ስለሚገልጥ በክርስቶስ መወለድ የሰው ልጅ ከሀጢያት ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን መግባትና ነፃ ከመውጣት እንደሚያመለክት፧ 12 ጊዜ ይምር ይምር የሚቆጠረው በእየሱስ ክርስቶስ የተመረጡት ሐዋሪያት ብዛትን እንደሚወክል ይገልፁታል። ይምር ይምር ጨዋታ አባላት የገና በዓል ከተከበረበት ቀን አንስቶ ሙሽሪት ቤት ማታ ማታ በመገናኘት የተለያዪ ጨዋታዎችና ጭፈራዎች እየተጫወቱ አብረው የሚያድሩ ሲሆን እስከ አስትረ/አስትሮ/ ማሪያም ጥር 21 ድረስ የሚቆይ ነው::
አንቃት(የገና ጫወታ)
አንቃት( የገና ጨዋታ) በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ ውስጥ ሐይማኖታዊና ባህላዊ ይዘት ኖሮት ይከበራል።በዓሉ ከገና ወይም ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ከአንድ ወር በፊት በከብት እረኞች እና በአካባቢ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጎረምሶች በገና ጭዋታ(አንቃት) ይጀመራል። ለዚህም መነሻ የሚሆነው ሐይማኖታዊ አንድምታ "ከመፅሐፍ ቅዱስ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ 2፥8-20 የሚገኙትን የጌታን መወለድ ከመልአኩ የሰሙትን እረኞችን ይወክላል" በማለት የሐይማኖት መሪዎችና ታላላቅ የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ። ይህ ባህላዊ ጨዋታ የራሱ የሆነ ህግ እና የራሱ የሆነ የመጫዎቻ እቃዎች አሉት እነዚህም፦
1ኛ/የገና ዱለ(ጉማ ወይም ፋርጉጌ)ጫፉ ወፈራም እና ቆልማማ የሆነ ከባህርዛፍ ወይም ከወይራ ዛፍ በሥርዓት ተጠርቦ የሚዘጋጅ ነው።
2ኛ/ሩር(አንቃት)ከእንጨት ዛፍ ስር ወይም ተፈልፍሎ እንደ ኳስ ድቡልቡል ተደርጉ አንደይሰነጠቅ በእሳት ተለብልቦ የሚዘጋጅ ሲሆን ፤ለጫወታው ምቹ እና ለጥ ባለ ሰፊ በሆነ ሜዳ ላይ ዳኛ(ያኖግ)በመሰየም ጫወታው ይካሄዳል። ይህም ባህላዊ ጫወታ መንደር ከመንደር ቀበሌ ከቀበሌ በግጥሚያ ወይም በውድድር መልክ ተዘጋጅቶ ይቀርባል በዚህም ጫወታ ቂም በቀል ጌታና ሎሌ ታናሽና ታላቅ ተብሎ የሚበላለጥ እና በቅሬታ የሚያዝ ቂም ቁርሾ ፀብ አይኖርም።
እንዞሪቶ
በዘመነ ዮሐንስ ከሆነ በታህሳስ 27በሌላው ጊዜ ደግሞ በታህሳስ 28ማታ ወይም በገና ዋዜም ሆያሆዬ(እንዞሪቴ)ጭፈራ ይጀመራል ጭፈራውም በእድሜ አቻ የሆኑ ወንድ ወጣቶች ቤት ለቤት በመዞር ይጨፍራሉ ለዚህም ብር እና በአይነት የእህል ስጦታን ከአባወራው ወይም ከእማወራዋ ይቀበላሉ ከዚህም በተጨማሪ ልጅ ያልወለደች ሴት ቤት በመሄድ ስለት ምርቃትን ይቀበላሉ ሰለቱም እንዲሰምር ምስጋና ያቀርባሉ እንዲህም ብለው ያዜማሉ፦
"እየበል እየበል እያሆ ሆበል×2እያሃን እየበል×2 "
"የገኒ አማኒለ ያብሽን የዲ ያዪለ"
"የገኒ ባልወለደ ያብሽን የጎሸ ወለደ"።
በማለት መልካሙን ምኞታቸውን በመግለፅ ይጫወታሉ ሴቲቱም "እንዳ አፋችሁ ያደርልግኝ እስከ ዛሬ አመት ልጅን ካገኘሁ ለቀጣይ አመት ገና እንዲህ አደርግላችኋለሁ" በማለት ስለት ትገባለች እነሱም ስለቱ እንዲፈፀም ተማፅነው እና አመሠግነው ይሄዳሉ ከቤት ወደቤት በመሄድ እየጨፈሩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይዞራሉ በዕለተ ገናም የገና ጫወታንና ፈረስ ጉግስ በቡድን በግል በመሆን ይጫወታሉ ሴት ልጃገረዶች ደግሞ በዘመኑ ከምታገባ ሴት ሙሽራ ቤት ወይም በእድሜ ከሁሉም ከፍ ያለች ገና ሰብሳቢ ሴት ልጃገረድ ቤት ድረስ በቂቤ የታሽ የገብስ ቆሎ በመሶብ(በቁርስ ሌማት) በመያዝ እና በመሰባሰብ ከሰብሳቢዋ ግቢ ውስጥ በራፍ (ጋጌታ)ላይ ምንጣፍ(ጅባ ወይም አንጮት)በማንጠፍ ወንፊት(የሺተር ጎንቺት)በመያዝ ወደ ፀሐይ ፊታቸውን በማዞር" ኢምር ኢምር "በማለት ያዜማሉ ይጫወታሉ በመጨረሻም ከገና ጫወታ መልስ ከሚመለሡ ጎረምሳ ወንዶች ጋር እስከ ማምሻው ድረስ አየተበላ እና እየተጠጣ በጨዋታ ይመሻል ይህም ጫወታ በየተራው ሴት ልጃገረድ ቤት በዙር ይፈፀማል ለዚህም የሚሆን ሴት ልጃገረዶች ከቤተሰብ የሚያገኙትን የእህል ስጦታ(ዱፍና)ይጠቀማሉ።
ወንዶችም ከሆያሆዬ(እንዞሪቴ)በስጦታ የተሰጣቸውን ብር እና ያገኘቱን እህል ወደ ብር በመቀየር በግ ወይም ፍየል በመግዛት አንድ ቤት ላይ በመሰብሰብ በጋራ አርደው ጠብሰው ይበላሉ ይህም ስርዓት "ላጎ" ይባላል በመጨረሻም በመመራረቅ ለአመት በሠላም እንዲያደርሳቸው በመመኘት የገና ዱላቸውን እና ሩርራቸውን ቆጥ ላይ አስረው በማስቀመጥ ይለያያሉ።

ዘፀአት የዘጌ ገቾ
392 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 13:19:44
ዛሬ አይቀርም ጉራንስ !

#ዬብር_ጫማ_የሙዚቃ_ድግስ
#ዛሬ_ቅዳሜ_ታህሳስ_15_ከምሽቱ_12_ሰአት_ጀምሮ
#ሳርቤት_በሚገኘው_ዮድ_አቢሲኒያ_የባህል_አዳራሽ
===
የተለያዩ ተወዳጅ መዚቀኞች ይገኛሉ :- ከነዚህ መሃከል ተወዳጁ ሀይሉ ፈረጃ ይገኝበታል !!
291 views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 17:22:24
ተጋብዛችዋል
398 views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 10:46:08
በቅርብ ቀን
463 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ