Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2022-12-10 16:38:50
በዛሬው እለት በአሶሳ ዩኒቨርስቲ የጃል መሮና የሸመልስ አብዴሳ ተማሪዎች ፦

"ፋኖ አሸባሪ ነዉ!"
"ፋኖ ገዳይ ነው!"
"ጃላማሮ መንግስታችን ነው!"
"ኦነግ ለኛ የነፃነታችን ምልክት ነው!"

የሚል መፈክር እያሰሙ ፥ ነውረኛና ሀገር አፍራሽ ተልዕኳቸውን ሲያራምዱ ሲውሉ ፥ በግቢዉ ያሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንኳንስ ሊያስቆሟቸው አጃቢዎች ሆነው መዋላቸው ታውቋል!

"ተበዳይ ዝም ሲል በዳይ ከሳሽ ይሆናል!" ማለት ይህ አይደለምን?

የአማራ ህዝብ ህልውናው የሚከበረውና መፃኢ እጣፋንታው የሚፃፈው በገዛ መራራ ትግሉ በመሆኑ ፥ ከዛሬውም ይልቅ የወደፊቱ እንደሚከፋ አውቆ ዳርእስከዳር ለሁለንተናዊ ትግል መነሳት ይኖርበታል! አለያ ግን የሚከፋና የሚብስ እንጂ የሚቆም ግፍና
መከራ አለመኖሩን ተረድቶ ራሱን ለከፋው ሰቆቃ ያዘጋጅ!
2.5K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 14:08:48
2.8K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 14:08:41 በወልንጭቲ ዙሪያ ትናንት የጀመረው የቤቶች ቃጠሎና ዘረፋ ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑ ተገለፀ!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በምትገኘዋ የወለንጭቲ ከተማ ዙሪያ ከትናንት ጀምሮ ቤቶች እየተቃጠሉ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።

በርካታ ህዝብ ከገጠር ቀበሌዎች ተፈናቅሎ ወደ ከተማዋ መግባቱን ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ዙሪያ በሚገኙ ቀበሌዎች የፀጥታ ችግር ከተከሰተ አምስት ቀን ሆኖታል ያሉት ነዋሪዎቹ፣ ቤቶች በሌሊት እየተቃጠሉ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የተከመረ የጤፍ ጭድ እየተቃጠለ እንደሆነና ከብቶችም እየተዘረፉ መሆኑን ጠቅሰው ፣ ድርጊቱ ወደ ከተማው እየተጠጋ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ ከወለንጭቲ ከተማ በቅርብ እርቀት ከፍተኛ የጥይት ተኩስ ድምጽ እንደሚሰማቸው ነው የገለጹት፡፡

ወገሬ ማርያም ፣ ቡታ ደንቆሬ እና ቡታ ኩርፋ ከሚባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተፈናቅሎ ወደ ከተማዋ መግባቱ የተነገረ ሲሆን ፣ ተፈናቃዮች ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደነበር ተሰምቷል፡፡

ወደ አጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች የሄዱ መኖራቸውንም የጠቀሱት ነዋሪዎቹ በአካባቢው ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እንዳለና በተለይ ደግሞ በከረዩ አካባቢ መንገድ ላይ ዘረፋና እገታ መባባሱን ተመላክቷል፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊትም በአካባቢው በሚሰራ የመንገድ ሥራ ላይ የነበሩ ከ25 በላይ ሠራተኞች በኦነግ ሸኔ ታግተው እንደተወሰዱም ተነግሯል፡፡ በሌላ በኩል ከሳምንት በፊት ወደ15 የሚሆኑ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞችና አመራሮች ታግተው ከ300-500 ሺህ ብር በነፍስወከፍ ከፍለው መለቀቃቸውም ይታወሳል፡፡

የወለንጭቲ ነዋሪዎች "ቤታችንን ዘግተን ነው ወደ ከተማ የገባነው" ያሉ ሲሆን ፣ << እስካሁን መንግሥት ምንም ባለማድረጉ ሰላምና ደህንነታችንን ሊያስጠብቅልን ይገባል!>> ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
2.9K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 20:52:11 የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ "አበባየሆሽ" ነው!

" ፈሴን ልፈሳ ነውና ማመካኛ ልጄን ጥሪልኝ!" አሉ አለቃ ገብረሀና፡፡ የሀገራችን መንግስታዊ የፖለቲካ ስርአትና በተቃውሞ ስም አስመሳይ የመንግስታዊ ፖለቲካው ፓራሳይት የሆኑ የፖለቲካ ቡድኖች ፥ ድክመታቸውን ፣ ልሽቀታቸውንና መበስበሳቸውን የሚያለባብሱበት " ማመካኛ ወይም ማሳበቢያ" እንዲሁም ፖለቲካ የሚሰሩበት ትርክት ወለድ ጠላት ካልፈጠሩ መቆም እንደማይችሉ አምነው የተቀበሉ ናቸው፡፡

ትህነግ/ህወሓት ደርግን ሲረግምና ልሽቀቱን ሁሉ በደርግ ሲያመካኝ ኖረ፡፡ ለፖለቲካ ማደራጃነትም "ጠላት" ብሎ የፈረጀውን የአማራ ህዝብ ከጫካ ጀምሮ የጥላቻ መርዝ ማራገፊያ አድርጎት ፥ በለስ ቀንቶት ስልጣን ሲይዝም ተቋማዊና ስርአታዊ ቅርፅ አስይዞ "በጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት" ይህን መከረኛ ህዝብ ፍዳውን ሲያሳየው ኖረ፡፡

ትህነግ በህዝብ ትግል ከስልጣኑ ተገፍቶ መቀሌ ሲከትም ኃላም ወደአማፂነቱ ሲመለስ ፥ በአብራኩ የተፈጠሩት የኦሮሞ ፅንፈኛ ሀይሎች ደግሞ "አማራ/ነፍጠኛ ጠላት ነው!" በሚለው የፖለቲካ ማደራጃ ትርክት ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ፥ እድሜ ዘመናቸውን የስርአታዊ ልሽቀታቸው ፥ የሀገር አፍራሽነት ሚናቸው ፣ የአቅመ ቢስነታቸውና የሀገራዊ ቁልቁለት መሪነታቸውን የሚያሳብቡት በትህነግ ላይ ብቻ እንጂ ወደራሳቸው የሚያመለክት ጣት ፈፅሞ የላቸውም፡፡

ለቆመለት እኩይ አላማም ቢሆን ጠንካራ አደረጃጀት ፈጥሮ ፊት ለፊት የገጠመውንና አስጨንቆ ተደራዳሪ መሆን የቻለውን "ትህነግ" በማሳበቢያነት መጠቀም ቢያቆሙ እንኳ ፥ ሌላ ማመካኛ ወይም ለመፈረጂያ የሚያገለግል ሀይል ፈልገው ይቀቡታል፡፡ ወይም ራሳቸው በአብራካቸው የፈጠሩትን ፥ ያደራጁትንና የሚደግፉትን መሀል ሀገር በመቶ ሺህ ሰራዊት አሰማርቶ የሚንቀሳቀሰው ጨፍጫፊና አራጅ ቡድን ለየዋሁ ህዝብ ማሳበቢያና የልሽቀታቸው ሰበብ መደረቻ አድርገው ይቀጥላሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ "መንግስት ነን" እያሉ ይህ ከመንግሥት ጦር በላይ የሆነ አሸባሪ ሀይል መሀል ሀገር እንዲህ እንዳሻው የሚፈነጨው በእነሱ ድክመት ( መንግስታዊ ሀላፊነት አለመወጣት ) መሆኑን እንኳ ማመን አይፈልጉም፡፡

የትግራዩን ኦሮሚያ ባለው የኦሮሚያን ትግራይ ባለው የሰበብ ማቀባበያ እያደረጉ ዝንተአለም በተመሳሳይ የልሽቀትና ጣት የመጠቋቆም የድካርት ፖለቲካ ውስጥ መጓዝ ብቻ! በነገራችን ላይ ይህ የልሽቀት ፖለቲካ ይትባህል - ከላይ ወርዶ እስከቀበሌ ባለው መንግስታዊ መዋቅር ቅርፅና መልኩ እየተቀያየረ የሚሠራበት ነው፡፡ አምስት አመት የህዝብን ችግር ከመፍታት ይልቅ አወሳስቦ የወረደ የአንድ ከተማ ከንቲባ በሌላኛው ሲተካ ፥ አዲሱ ከንቲባ 5 አመት የሚሠነብተው ዮደመውን ከንቲባ ሲያራክስና ድክመትና ልሽቀቱን በሱ ሲያመኻኝ ነው፡፡ ቀጥሎም ሌላው በተመሳሳይ ይቀጥላል፡፡ ይህ የሀገራችን ስርአታዊ ብልሽት መሠረታዊ ማሳያ ነው፡፡

አዳነች አቤቤ ትናንት የአዲስአበባ ተማሪዎች " ኦሮሚያ የመቶ አመት እድፍሽን በደማችን አጠብንልሽ" የሚልን አስነዋሪና ክልሉ ለትውልዱ የጥላቻ መርዝ ለመጋራት ሲጠቀምበት የኖረውን መዝሙር ተገደን ልንዘምርም ሆነ ፥ የኦሮሚያን ባንዲራ እንድንሰቅል ልንደረግ አይገባም ብለው ተቃውሞ ሲጀምሩ " ትክክል ናቸው!" ብላ አስተዳደሯን ከመፈተሽ ይልቅ << ..ይህ የአዲስአበባ ነዋሪዎች አጀንዳ ሳይሆን የፅንፈኛው ሸኔ ፤ የፅንፈኛው ፋኖና የምዕራባውያን አጀንዳ ነው!" ብላ ስትበጠረቅ ትንሽ ቅፍፍፍ..<< ‘ኦሮሚያ የመቶ አመት እድፍሽን በደማችን አጠብንልሽ’ የሚልን አስነዋሪና ክልሉ ለትውልዱ የጥላቻ መርዝ ለመጋት ሲጠቀምበት የኖረውን መዝሙር ተገደን ልንዘምርም ሆነ ፥ የኦሮሚያን ባንዲራ እንድንሰቅል ልንደረግ አይገባም!>> ብለው ተቃውሞ ሲጀምሩ " ትክክል ናቸው!" ብላ አስተዳደሯንና እየሄደች ያለበትን ሀገር አፍራሽ መንገድ ከመፈተሽ ይልቅ << ..ይህ የአዲስአበባ ነዋሪዎች አጀንዳ ሳይሆን የፅንፈኛው ሸኔ ፤ የፅንፈኛው ፋኖና የምዕራባውያን አጀንዳ ነው!" ብላ ስትበጠረቅ ትንሽ ቅፍፍፍ.. እንኳ አላደረጋትም፡፡ ደምና አጥንቱን ገብሮ ፥ ዛሬ ኬኒያ ስደት ላይ ከመገኘት የታደጋትን ፋኖ ፥ ራሳቸው ካቋቋሙት ጨፍጫፊ ሀይል ጋር እንዲሁም ከትህነግ/ህወሓት ጋር እጃቸውን ጠምዝዘው ካደራደሯቸው ምዕራባውያን ጋር ሰድራ ስትበጠረቅ "ሰው ምን ይለኛል!" እንኳ አላለችም፡፡ ምክንያቱም ይህ ብቸኛው የመርገምተ-ፖለቲካ እውቀታቸው ነዋ!

ሳጠቃልል ግን ፦ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በታሪክ ታይቶ ለማይታወቀው ሀገራዊ ምስቅልቅልና ስርአታዊ ብልሽት የዳረገን ግንባር ቀደሙ ተጠያቂ ፥ ከትህነግ መራሹ ኢህአዴግ አብራክ የተወለደውና ራሱን "ብልፅግና" ብሎ የሰየመው በኦሮሞ (ኦህዴድ/ኦነግ) ፅንፈኞች የሚመራው ስርአት ነው!
1.2K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 14:21:10
2.7K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 14:21:01 በወልንጭቲ ዙሪያ ቤቶች እየተቃጠሉ ነው!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በምትገኘዋ የወለንጭቲ ከተማ ዙሪያ ቤቶች እየተቃጠሉ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡በርካታ ህዝብ ከገጠር ቀበሌዎች ተፈናቅሎ ወደ ከተማዋ መግባቱን ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ዙሪያ በሚገኙ ቀበሌዎች የፀጥታ ችግር ከተከሰተ አምስት ቀን ሆኖታል ያሉት ነዋሪዎቹ፣ ቤቶች በሌሊት እየተቃጠሉ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የተከመረ የጤፍ ጭድ እየተቃጠለ እንደሆነና ከብቶችም እየተዘረፉ መሆኑን ጠቅሰው፣ ድርጊቱ ወደ ከተማው እየተጠጋ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
ከወለንጭቲ ከተማ በቅርብ እርቀት ከፍተኛ የጥይት ተኩስ ድምጽ እንደሚሰማቸው ነው የገለጹት፡፡

ወገሬ ማርያም፣ ቡታ ደንቆሬ እና ቡታ ኩርፋ ከሚባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተፈናቅሎ ወደ ከተማዋ መግባቱ የተነገረ ሲሆን፣ ተፈናቃዮች ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደነበር ተሰምቷል፡፡

ወደ አጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች የሄዱ መኖራቸውንም አዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እንዳለ በመጥቀስም በተለይ በከረዩ አካባቢ መንገድ ላይ ዘረፋና እገታ መባባሱን ተመላክቷል፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊትም በአካባቢው በሚሰራ የመንገድ ሥራ ላይ የነበሩ ከ25 በላይ ሠራተኞች በኦነግ ሸኔ ታግተው እንደተወሰዱም ተነግሯል፡፡ ነዋሪዎቹ ቤታችንን ዘግተን ነው ወደ ከተማ የገባነው ያሉ ሲሆን፣ እስካሁን መንግሥት ምንም ባለማድረጉ ሰላምና ደህንነታችንን ሊያስጠብቅልን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ 

Via Addis Maleda
2.7K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 22:35:44
3.8K views19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 22:35:36 የ3ቱን ክልሎች ክልላዊ የህዝብ መዝሙሮች - የአማርኛ ትርጓሜ አንብቡና - ፍርዱን ለህሊናችሁ ስጡት!

1. የትግራይ ክልል መዝሙር /የአማርኛ ትርጉም /

የማንወጣው ተራራ
የማንሻገረው ወንዝ የለም ፤
ፍፁም ወደኋላ የለም
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም!

በፀሀይ ሀሩር እና በቁር
ነፍሳችን ውሀ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን
ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም

ሆኖም መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም፤

በጅቦች እንከበብ መሬት ይክበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር!
ስጋችን ላሞራ ደማችን እንደ ጎርፍ ይፍሰስ፤
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን

መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በፍፁም አንሸነፍም፤

የጦር መሳሪያ መርዝ ፋሽስታዊ ንዳድ
ሚሊየን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት መቁሰል እና ኪሳራም እንከፍላለን፤
የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን

መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን፤
በዚህ ሁሉ ጉዞ ግን አሸናፊዎች እኛ ነን።

☞ በማለት የትግራይ ክልል መንግስት በትግራይ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስከአሁን ድረስ ያዘምራል።

2. የኦሮሚያ ክልል መዝሙር / የአማርኛ ትርጉም /

ኦሮሚያ //2// የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናት
የኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ
የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናት
የብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናት
የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
ሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብት
አስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማት
ከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅር
ለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገን
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!

☞ በማለት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፉት 30 ቅመታትን ጨምሮ እንከአሁን ድረስ በኦሮሚያ ክልል ይዘመራል። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ካልተዘመረ እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው።

3. የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መዝሙር

የታታሪ ህዝቦች የታሪክ ማህደር
የአኩሪ ባህል አምባ የድንግል ሀብት አፈር
የህዝቦችሽ ተስፋ ለሟ ክልላችን
በሰላም በፍቅር በልማት ጉዟችችን
ተባብረን በስራ እንገነባሻለን

የአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን ፥
ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን
በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን።

☞ በማለት የአማራ ክልል ህዝብ መዝሙር ይቋጫል፡፡ ይህ መዝሙርም ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስከአሁን ድረስ በክልሉ ይዘመራል።

ለትውልዱ የጥላቻና የክፋት መርዝ እየጋተ ፥ ሀገርን የሚያፈርሰው ማን እንደሆነ ፥ የህዝብ ህሊና ፍርዱን ይስጥ!

#ሼር
3.8K viewsedited  19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 22:13:03
የኦሮሞ ፖለቲከኞችኮ ኢትዮጵያን ገና በጠዋቱ በዚህ መዝሙር ውስጥ ገድለዋታል! የኦሮሞን ህዝብ አሳንሰውና አዋርደው ብሎም ከሌሎች ህዝቦች ነጥለው ቀብረውታል!

አዲስአበቤ እንዲዘምር እየተገደደ ያለው "የኦሮሚያ ክልላዊ መዝሙር" ትርጉም ይኸው ነው!

ኦሮሚያ //2// የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናት
የኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ
የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናት
የብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናት
የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
ሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብት
አስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማት
ከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅር
ለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገን
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!

በኦሮሚያ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚዘመረው መዝሙር ይዘት ደግሞ ከስር ያለው ነው

ነፍጠኛ የሰራውን ፥ ማሠብ ያንገበግባል
ታሪክ ኖሮን እንደሌለን
እናት ኖሮን እንደሌለን
እንደበግ ግልገል በየመንገዱ ታርደን
ያንን ያሰብን እለት ፥ ምሽግ ያዝን
ሌላ ማሠብ አንፈልግም
ከእናታችን ኦሮሚያ በቀር!



ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሆይ! "ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት" በእናንተ አንደበት ሲጠራ እጅግ አሳፋሪ ነገር ይሆናል!
3.5K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 19:54:23
"FANO INSIDE ADWA AND WOLLEGA"
(A New Fiction by Crime Bosses)

Yesuf Ibrahim
3.6K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ