2022-08-25 07:47:36
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
" ጾም ለጸሎት እናቷ፣ ለአርምሞ እኅቷ፣ ለአንብዕ(ለዕንባ) መፍለቂያዋ፣ ለበጎ ትሩፋት ሁሉ ጥንት መሠረት ናት"
ኮኲሐ ሃይማኖት ገጽ 318
✥●.......◉ ✞ ◉.......●✥
ብሂለ አበው
✥●.......◉ ✞ ◉.......●✥
"የሚያስደንቅ የሚያዋርድ ኃጢአት ከመስራት እድን ዘንድ የንስሐ አጋዥ የሚሆኑ አፍአዊ ትህትናን፣ ውስጣዊ ትህትናን፣ ጸሎት ዘወትር፣ ምሕረት ምፅዋትን፣ እንብዕ ዘወትርን መያዝ ይገባል"
ቅዱስ አፈወርቅ
"የአሁኑ ትውልድ ነገ በተሻለ መንገድ ሊራመድ የሚችለው ትናንት አባቶቹ የተራመዱበትን መንገድ ያውቅ እንደሆነ ብቻ ነው፤ ስለነገው በምናስብበት ጊዜ የትናንትናውን ማስታወስ አለብን፤ የትናንቱን ጊዜ ለዛሬም መማሪያ መጽሐፍ ነውና"
ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ
"ገንዘብ ቢኖርህ በአራጣ አታበድር ነገር ግን ለማይመልስልህ ስጠው"
ቅዱስ አግናጥዮስ
" እግዚአብሔር ተአምራት ባለማድረጋችን ወይም የተሰወረውን ምስጢር ባለማወቃችን ወይም የተራቀቀ ነገር ባለመማራችን አይወቅሰንም፤ ስለ ኃጢአታችን ባናለቅስና ንስሐ ባንገባ ግን ስለዚህ ይወቅሰናል"
አባ ወቅሪስን
"ከላይ ያለ ሰው አስተማሪ የሚሆነው በእውቀቱ ከሆነ ሊቅ ልትሆን ትችላለህ በህይወቱ ከሆነ ግን ክርስቲያን ትሆናለህ"
አቡነ ሺኖዳ
"የተቀደሰ ፀሎት ስትጀምር ወደ አንተ ለሚመጣው ነገር ሁሉ እራስህን አዘጋጅ"
ቅዱስ አጉሪክ
"ከሰዎች መካከል አንዱ እንደ ከንቱ እና እንደሌለህ አድርጎ ቢቆጥርህ ከአፈር እደተፈጠርህና ወደ እርሱም እንደምትመለሰ ተናገር አንተ ወራዳ ከንቱ ብሎ ቢሰድብህም አንተ ራስህን አፈርና አመድ ነኝ ብለህ ጥራ፤ እራሱን እንዲህ ብሎ ከጠራው ከተከበረው አባት ከአብሃም የበለጥህ አይደለህምና"
ባስልዮስ ዘቂሳርያ
"ሰውን ሊያድነው የሚችለው ብሕትውና ወይም ትጋሃ ሌሊት ወይም ማንኛውንም ዓይነት መከራ መቀበል ሳይሆን እውነተኛ ትህትና ብቻ ነው "
አረጋውያን አበው
"የሚያምነውን እምነት ምንነት ሳያውቅ የሚኖርን ሰው የጌታውን ቤት በማያውቅ፣ ከቤት እንስሳት በሚያንስ በዱር አውሬ ይመስሉታል"
ሊቃውንት
ምንጭ
ብሂለ አበው መፅሐፍ
ለሁሉም የተዋህዶ ልጆች
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
ለመቀላቀል
t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae
356 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 04:47