Get Mystery Box with random crypto!

ማርያም ያኔ ገና ድሮ ድሮ ድሮ ቴክታና ጴጥርቃ ህልም አይተው ነበረ ሰባቱ ግልገሎች ሲወልዱ ጨረቃ | የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

ማርያም

ያኔ ገና ድሮ
ድሮ ድሮ ቴክታና ጴጥርቃ
ህልም አይተው ነበረ
ሰባቱ ግልገሎች ሲወልዱ ጨረቃ
ቀንም ቀንን ወልዶ
ሳምንታትም ወራት ወራትም አመታት
ተወለደችልን ብላቴናይቱ የጌታዬ እናት

12 አመታት ከመቅደሱ ኖራ
ወደ እርሷ ቀረበ ገብርኤል ከራማ
ከሰማይ ሰማያት ሲመጣ መልአኩ
ብሎ መች ጠየቀ ማናት ድንግሊቱ
በሚካኤል ክንፎች ተስለሽ ስላየሽ
ከመቅደሱ ገብቶ ሰላም ለኪ አለሽ።

በአንድ እሺታ በአንድ ድምፅ
መለኮትን በሆዷ የሚያሰርፅ
የአርያም ንጉሥ ሊቀ ካህናት
ለፅላት ማደሪያ አ'ረገሽ ታቦት
ከፍጥረታት ማን ተገባ?
ከፍጥረታት ማንስ በቃ?
አምላክን ለማቀፍ ሀጥያትን ሳይሰራ

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ያወደሰሽ ያለሽ ብልጫ
የቅዱስ ያሬድ ውብ ዜማ
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ሚሠማ
የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴ
የአባ ኤፍሬም ውዳሴ
የያዕቆብ መሰላሉ
አንቺ እኮነሽ እናቲቱ።
እፀ ጳጦስ ሙሴ ያየሽ
ነበልባለ እሳት ሳይነድብሽ
አንቲ ውዕቱ መሶበ ወርቅ
በፍጥረታት ስምሽ ይርቀቅ
በሥላሴ ፊት ሞገስ ያለሽ
የገነት በር ቁልፋችን ነሽ።

አቤኔዘር በፍቃዱ
ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት

ለመቀላቀል

t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae