Get Mystery Box with random crypto!

የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemaritnsae — የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemaritnsae — የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zemaritnsae
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.81K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መረጃ ትምህርት መዝሙር ግጥም ይገኝበታል በተጨማሪም
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
🙏1) የመዝሙር ግጥምና ዜማ ለምትፈልጉ በፈለጉት አይነት እና ቋንቋ
2) ቪዲዮ ክሊፕ መስራት ለምትፈልጉ (የመ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-24 20:43:13 ህብረ ቃል ስታወጡ አንድ አንድ ቃል ብቻ ላይሆን ይችላል አንድ ሀረግም ህብረ ቃል ሊሆን ይችላል
406 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:36:34 ሰላም እንዴት ናችሁ እረስቼው አብዛኛው ግጥሞችህ ቅኔ ናቸው ብላችኋል እና ስለዚህ ዛሬ ከለቀቅኩላችሁ "ምንደኛ " ከሚለው ግጥሜ ውስጥ ቢያንስ አራት "ህብረቃል" አውጥቶ ሰም እና ወርቁን ከሁሉም በተሻለ ለይቶ ላብራራ አንድ ሰው የ100 ብር ካርድ ሽልማት አለው እግዚአብሔር ይግለጽላችሁ መልሱን በእዚህ ላኩ @Tins7 መልሶቻችሁ ከስማችሁ ጋር ይፖሰታል
402 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:44:37 ቃልኪዳን ጎንፋ በጣም ጥሩ ግጥም ነው ሀሳቡም መልእክቱም ቃላቱም ደስ ይላል የተሻለ እንጠብቃለን

ሙሉ ውጤት ሐምሌ 13
የዳኛ ውጤት 55/50
የlike ?
371 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:42:21 ፨ሞቴን ናፈቅኹኝ፨
የነበረኝ ሰላም የነበረኝ ደስታ
ዛሬ ተቀይሮ ሲተካ በዋይታ
ያላሰብኩት ሲሆን ያሰብኩት ሲጠፋ
ህይወቴ ትርጉም አጥቶ ከኔ ሲርቅ ተስፋ

ሳቄን ተነጥቄ አይኔ እንባ ሲሞላ
የመኖሬ ነገር እያደር ሲላላ
ያኔ
ተማፅኜ ብዙ እድሜ ስጠኝ እንዳላልኩኝ
አሁን ግን መሞቴን እጅጉን ናፈቅኹኝ
ፈጣሪ ውሰደኝ ብዬ ተማፀንኩኝ።

ደግሞ መሞት ፈራው ፅድቅ የለም ከቤቴ
በሃጥያት ቆሽሿል ፈራሽ ሰውነቴ
ድንገት ይህን ሳስብ ውስጤ ተሸበረ
ለጠየቀው ነገር አንደበቴ አፈረ።

በእርግጥ ኖርኩኝ ብሎ እንዲሁከባዘነ
ደስታውን ተነጥቆ ሰው ልቡ ካዘነ
መኖሩ እያስጠላው ህይወቱ ካላማረ
ፅድቅ ሰርቶ መሞት መታደል ነበረ።

በ ቃልኪዳን ጎንፋ
ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

ለመቀላቀል

@zemaritnsae
@zemaritnsae

604 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 19:00:45
384 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 18:30:36 ሰላም ቤዛ እንደ መጀመሪያሽ ጥሩ ነው በርቺ
ስህተት
1) አንዳንድ ቦታ ምጣኔ ይጎድለዋል
2) አብዛኛው ቤት መምቻ ፊደል ሳድስ ሆነ
3) የተለመደ ቃል አታብዢ
4) ሀሳብ እና ቃላት አትደጋግሚ

ሙሉ ውጤት ሐምሌ 13
የዳኛ ውጤት 42/50
የlike ?
368 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 18:27:44 የመነኑት
አለም ሰልችቷቸው የሰው ግርግር
ተሰደው ቢሄዱ ከገዳሙ መንደር
መች ሆነ እና ለ'ራሳቸው ብቻ
ለ'ኛ ላሃጥያተኞች ለሆንን
ለዳቢሎስ መጫወቻ
በአለም እየኖርን ለሆን' አስመሳዮች
ሊጸልዩልን ነው ለ'ኛ እድለቢሶች
የመነኑትማ እንዴት ታድለዋል
ይህን አለም ንቀው መንግስቱን ናፍቀዋል
በአለም እየኖሩ
በክርስቶስ ፍቅር ልባቸው ታውሯል
እንዴት መባረክ ነው እንዴትስ መታደል
'ራስን ዝቅ አ'ርጎ ክርስቶስን መምሰል
መሆን ባይቻለን
ምን አለ ሕጉን ብንጠብቅ
ምንስ ይጎድለናል ከአምላክ ብንታረቅ
በአለም እየኖርን ሰክረን በንዋይ
ልባችን ደንድኖ ጠፍቶ አስተዋይ
መሆናችን ሳይታወቀን እንደ ትዕቢተኛ
ተዋርደን ሆነናል እኛስ ሀጥያተኛ
ሳጥናኤልም ቢሆን ክብሩን የተቀማው
በትዕቢቱ ነው ከጥልቁ የወደቀው
አለምንም ትተው ገዳም የመነኑ
ስለሀጥያተኞች አምላክን የሚለምኑ
በነሱ ፀሎት ነው እስካሁን ያለነው
እንደ ሀጥያታችን ዋጋ ያልከፈልነው
የላመ የጣመ ምግብ ሳያምራቸው
ቤት ገንዘብ መኪና ምቾት ሳያሳስባቸው
እፍኟን ባቄላ እሷኑ ቀማምሰው
በመሬት ተኝተው ድንጋይ ተንተርሰው
ዘውትር ሳይሰለቹ በሚፀልዩት
በእነርሱ ሀይል ነው በእነርሱ ፀሎት
አለም የቆመችው በመነኮሱት

ሰላም ቤዛ
ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

ለመቀላቀል

@zemaritnsae
@zemaritnsae

389 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:24:08
(ጼና አልባሲሁ/2/
ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ከመ ጼና ስሂን)2x
(አልባሲሁ ዘሜላት/2/
ዘወረደ እምሰማያት)2x


@zemaritnsae
@zemaritnsae
@zemaritnsae
ዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ
463 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, edited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:10:57 https://vm.tiktok.com/ZMNPMLUJU/?k=1
447 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:54:38 ገጣሚ ጽዮን አሪፍ ወቅታዊ ግጥም ነው

ስህተት
1) ርዕሱ ግን ከግጥሙ ጋር አይገናኝም ግጥምሽ ነጭ ነጯን ነው በግልጽ የጻፍሺው
2) መጨረሻው ቃላቱ ቀለለ በጋራ ሆነን ብለሽ እንሁን በአንድነት ማለትሽ ልክ አይደለም ቃላት እና ሃሳብ አይጠፋም እና ፈልጊለት ምረጪ

ሙሉ ውጤት ሐምሌ 13
የዳኛ ውጤት 45/50
የlike ?
539 viewsዘማሪ ትንሳኤ ፍቃዱ Josi, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ