Get Mystery Box with random crypto!

፨ሞቴን ናፈቅኹኝ፨ የነበረኝ ሰላም የነበረኝ ደስታ ዛሬ ተቀይሮ ሲተካ በዋይታ ያላሰብኩት ሲሆን ያ | የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

፨ሞቴን ናፈቅኹኝ፨
የነበረኝ ሰላም የነበረኝ ደስታ
ዛሬ ተቀይሮ ሲተካ በዋይታ
ያላሰብኩት ሲሆን ያሰብኩት ሲጠፋ
ህይወቴ ትርጉም አጥቶ ከኔ ሲርቅ ተስፋ

ሳቄን ተነጥቄ አይኔ እንባ ሲሞላ
የመኖሬ ነገር እያደር ሲላላ
ያኔ
ተማፅኜ ብዙ እድሜ ስጠኝ እንዳላልኩኝ
አሁን ግን መሞቴን እጅጉን ናፈቅኹኝ
ፈጣሪ ውሰደኝ ብዬ ተማፀንኩኝ።

ደግሞ መሞት ፈራው ፅድቅ የለም ከቤቴ
በሃጥያት ቆሽሿል ፈራሽ ሰውነቴ
ድንገት ይህን ሳስብ ውስጤ ተሸበረ
ለጠየቀው ነገር አንደበቴ አፈረ።

በእርግጥ ኖርኩኝ ብሎ እንዲሁከባዘነ
ደስታውን ተነጥቆ ሰው ልቡ ካዘነ
መኖሩ እያስጠላው ህይወቱ ካላማረ
ፅድቅ ሰርቶ መሞት መታደል ነበረ።

በ ቃልኪዳን ጎንፋ
ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

ለመቀላቀል

@zemaritnsae
@zemaritnsae