Get Mystery Box with random crypto!

ዮናስ ሳተላይት ዲሽና ኤሌክትሮኒስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yonsattech1 — ዮናስ ሳተላይት ዲሽና ኤሌክትሮኒስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yonsattech1 — ዮናስ ሳተላይት ዲሽና ኤሌክትሮኒስ
የሰርጥ አድራሻ: @yonsattech1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.96K
የሰርጥ መግለጫ

♨️ ስለ ዲሽ ስማርት ስልኮች ኮምፒውተርና ኤሌክትሮኒስ መረጃዎችን ያገኛሉ።
♨️ የሪሲቨር የስልክና የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን @software365
♨️ የመወያያ ግሩፕ @YONASDISH2
♨️3 ቪዲዮዎች በሳምንት በአማርኛ በHD ጥራት ለመመልከት ቤተሠብ ይሁኑ
https://www.youtube.com/YonsatTech
CREATOR YONAS GEREMEW
🔥Inbox @YONSAT

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-20 18:29:59 አንድ የዲሽ ባለሙያ በየቤቱ እየሄደ ሲሠራ በአብዛኛው የሪሲቨር መቃጠል እንዲሁም የቴሌቭዥን ብልሽት ያጋጥመዋል !
ስለሆነም ጥሩ የሆነ ስራ ለመስራት ቢያንስ ቲቪ ቀለል ያሉ ችግሮችን እንዲሁም የሪሲቨር
Power ችግር
Software ችግሮችን ሄደበት መስራት ተጨማሪየገቢ ምንጭ ነው።

በዚ ሀሳብ እስቲ የሚሠማችሁን አስተያየት comment ላይ አስቀምጡ በአይነቱ ለየት ያለ የጥገና ትምህርት በነፃ የምታገኙትን ነገር አቀርብላችዋለው።


ይህ ፕሮግራም ስልጠና ከምትከታተሉ ሠልጣኞች ጋር አይገናኝም ። እንረዳዳ ብለን ነው
500 viewsAdministrator, edited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 17:37:24
493 viewsYoN Sat Tech, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 17:36:29
454 viewsYoN Sat Tech, 14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 17:35:35

DSTV ስንሠራ ሁሌ የሚያጋጥመን ችግር
     _
  ከ
ትች  የምትመለከቱት ፎቶ DSTV ስትሠሩ ኳሊቲ ካመጣችሁ በዋላ በፋይንደር ነገር ግን ሪሲቨሩ ላይ Search ስታደርጉ እንዲህ ብሎ ይፅፋል። እናም በተደጋጋሚ እየደወላችሁ ለጠየቃችሁኝም መልስ ይሆናል።
DSTV ለመስራት ፈጣን Transponder  12245 v/H 27500 ነው። Horizontal አድርጋችሁ የምትሠሩ ከሆነ የግድ የLNB አቀማመጥ (ገመድ  የሚገባበት ቁልቁል ወደ መሬት ነው)። ይህ የመጀመርያው ሲሆን በመቀጠል DSTV የሚገኘው Eutelsat 36°B ነው። ይህ ሳተላይት ደግሞ ከናይል ሳት ወደ ግራ ከዲሹ ጀርባ በመሆን ቀና በማድረግ ወደ ግራ እጃችሁ መውሰድ ነው።ከዛን በዚህ ቁጥር  እስከ 85 ድረስ በቀላሉ ይመጣል።
  በመቀጠል ሪሲቨራችን ላይ በ 11919V 27500  Free ቻናሎች ማለትም የሀገራችን ቻናሎች ከከፈቱ አልያም Search ስታደርጉ ከገቡ ትክክለኛ የDSTV ሳተላይትን ሠርተናል ማለት ይቻላል።
  ይህ ከላይ ያለው ፁፍ ከመጣላችሁ ግን
1 ትክክለኛ የDSTV ሳተላይት አልሠራችሁም በፋይንደር ኳሊቲ ቢመጣም ሌላ ሳተላይት ከሆነ
2 ገመዱ ችግር ካለበት
3Connector  ስትገጥሙ ስህተት ካለው ብቻ ስለሆነ  ከዚህ በዋላ ስትሠሩ ይህ ፁፍ ከመጣ ከላይ የሚገኙትን ነገሮች ተመልከቱ።

                 DSTV ሪሲቨር እና የPackage አይነቶች
             __

DSTV ጎጆ  በወር 220 ብር የምንከፍል ሲሆን ከ70 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ።
DSTV ቤተሠብ በወር 380 ብር የምንከፍል ሲሆን ከ 100 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ።
DSTV ሜዳ በወር 550ብር የምንከፍል ሲሆን ፕሪሜርሊግን ጨምሮ ከ 130 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ።
DSTV ሜዳ ፕላስ ደግሞ በተሻለ ሁኔታ 160 ቻናሎችን የምታገኙ ሲሆን 1300 ብር በወር ትከፍላላችሁ።
DSTV ፕሪሚየም በወር 2600ብር የምትከፍሉ ሲሆን ከ170 በላይ ቻናሎችን የምታገኙብ Package ነው።
482 viewsAdministrator, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 17:07:03 በ YOUTUBE እንዴት ገንዘብ እንሠራለን ???
    ----------------------------------------
ሠላም ለናንተ ይሁን ውድ የቻናላችን ቤተሠቦች በዛሬው እለት ከYoutube እንዴት ገንዘብ እንሠራለን ? በምን አይነት መንገድ ገንዘባችንን መቀበል እንችላለን ? እንዲሁም ለመስራት ምን ምን ነገሮችን ማሟላት ይጠበቅብናል ለሚሉት ጥያቄዎች አጠር ያለ ፁፍ ይዤ መጥቻለው  መልካም ቆይታ !!!

Youtube ለመጀመር/ለመክፈት /

ማንኛውም ሠው ያለውን ተሠጦ ወደ ገንዘብ የሚቀይርበት ምርጥ የOnline ገንዘብ ማግኛ መንገድ Youtube ይባላል። በአሁኑ ሠአትም በሀገራችን ብዙ ሠዎች ቋሚ የገቢ ምንጫቸው አድርገውታል። ስለሆነም አንድ ሠው Youtube ቻናል ለመክፈት

1_ በቅድምያ Gmail አካውንት ያስፈልገናል። በተለምዶ Email የምንለው ሲሆን ብዙ የEmail አይነቶች የሚገኙ ሲሆን Youtube ለመክፈት ግን Gmail አካውንት ነው የሚያስፈልገው። በ Yahoo/Hotmail/ በመሣሠሉት መክፈት አንችልም ይህም Youtube አንዱ የGoogle መተግበርያ ስር የሚገኝ ስለሆነ ! ስለሆነም የግድ Gmail አካውንት ያስፈልገናል።
2_Email /Gmail እንዴት እንከፍታለን  ?
የgmail አካውንት ለመክፈት በመጀመርያ በስልካችን ከሆነ Google Chrome Browser በመጠቀም ወይም ስልካችን ላይ ባለ የInternet access በምናደርግበት ማንኛውም Browser መጠቀም ይቻላል። በመቀጠል www.google.com ብለን  search በማድረግ  ከዛን google ውስጥ ስንገባ ቀጥታ ከላይ Gmail የሚለውን በመንካት ወይንም sign up gmail account በማለት Search ማድረግ እንችላለን።

3_ ከዚህ በዋላ በሚመጣው ሳጥን ውስጥ የተለያዩ እኛን የሚገልፁ መረጃዎችን ካስገባን በዋላ  Create Account ብለነው Email አካውንት እንከፍታለን ማለት ነው።

Email አካውንት ስትከፍቱ የስልክ ቁጥራችሁን በማስገባት Verify ማድረግ አለብን። ሲቀጥል ደግሞ ይህን Email አድራሻ መርሳት የለብንም ምክንያቱም በዚህ Email አካውንት ነው ቀጥታ Youtube ላይ ገብተን Create Channel የምንለው። ስለዚህ Email አቹንና የምትጠቀሙትን የሚስጥር ቁጥር /Password / መዘንጋት የለብንም !
በስልካችን Google Chrome ስንጠቀም በቅድምያ  ከላይ የሚገኙትን 3 ነጥቦች በመንካት Desktop Mode ማድረግ አለብን።

በቀጣይ ከፍተን ማስተካከል ያለብን Setting ዎች እንዲሁም ምን ያህል ገንዘብ እንደምንሠራ ፖስት አደርጋለው
496 viewsYoN Sat Tech, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 08:56:28 ከዮናስ ሳተላይት ዲሽና ኤሌክትሮኒስ ጥገና ለቻናላችን ቤተሠቦች በሙሉ እንኳን ለአዲሱ አመት በሠላም አደረሳችሁ /ሰን

መልካም አዲስ አመት 2015
978 viewsYoN Sat Tech, edited  05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 00:20:48
Answer

ከላይ የምትመለከቱትን አይነት ችግር የምናገኘው

1 _ Horizontal Yoke cable ከቦርዱ ጋር ያለውን Connection ከተቋረጠ
2_ Horizontal Yoke Output በ Inductor አልፎ ወደ Yoke የሚሄድ ሲሆን inductor ሩ ከተቃጠለ /ከተቋረጠ /  የዚህን አይነት ምስል ይመጣል።

ስለሆነም በመጀመርያ 4ቱ የYoke connection መካከል ከላይ የሚገኙትን ገመዶች የሚሠኩበትን Service ማድረግ ሲቀጥል የተቋረጠ መስመር መመልክና እንዲሁም በአብዛኛው 37micro henry የሚለውን ትልቅ Inductor መቀየር ነው።
1.0K viewsYoN Sat Tech, 21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 18:31:49 እናመሠግናለን ተመልሷል Teme yegose lij

አሸናፊ ሆኗል መልሱን በተብራራ መልኩ ፖስት እናረጋለን
896 viewsYoN Sat Tech, 15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 18:13:27
Patters 17'' crt ቲቪ የዚን አይነት ምስል አመጣ

ምን ይሆን ችግሩ ? በደንብ አብራርቶ ለመለሠ የበአል ስጦታ አለው
887 viewsYoN Sat Tech, edited  15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 21:05:22 በአብዛኛው በግሩፕ ላይ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች እነኚን ቪዲዮዎች በመመልከት ሁሌም የትኛውንም የLifestar ሪሲቨር ችግር መፍታት ትችላላችሁ

⓵ ሪሲቨራችን On ወይም Boot ብሎ ሲቀር

⓶ ሪሲቨራችን ምንም አልበራ ካለ

⓷ ሪሲቨራችን Display ምንም አላመጣ ካለ

ከታች ያሉትን ቪዲዮዎች በመመልከት የምንጊዜም መፍትሄ ማግኘት ትችላላችሁ


1 ___

1.0K viewsYonsat Tech, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ