DSTV ስንሠራ ሁሌ የሚያጋጥመን ችግር _ ከትች የምትመለከቱት ፎቶ DSTV ስትሠሩ ኳሊቲ ካመጣችሁ በዋላ በፋይንደር ነገር ግን ሪሲቨሩ ላይ Search ስታደርጉ እንዲህ ብሎ ይፅፋል። እናም በተደጋጋሚ እየደወላችሁ ለጠየቃችሁኝም መልስ ይሆናል። DSTV ለመስራት ፈጣን Transponder 12245 v/H 27500 ነው። Horizontal አድርጋችሁ የምትሠሩ ከሆነ የግድ የLNB አቀማመጥ (ገመድ የሚገባበት ቁልቁል ወደ መሬት ነው)። ይህ የመጀመርያው ሲሆን በመቀጠል DSTV የሚገኘው Eutelsat 36°B ነው። ይህ ሳተላይት ደግሞ ከናይል ሳት ወደ ግራ ከዲሹ ጀርባ በመሆን ቀና በማድረግ ወደ ግራ እጃችሁ መውሰድ ነው።ከዛን በዚህ ቁጥር እስከ 85 ድረስ በቀላሉ ይመጣል። በመቀጠል ሪሲቨራችን ላይ በ 11919V 27500 Free ቻናሎች ማለትም የሀገራችን ቻናሎች ከከፈቱ አልያም Search ስታደርጉ ከገቡ ትክክለኛ የDSTV ሳተላይትን ሠርተናል ማለት ይቻላል። ይህ ከላይ ያለው ፁፍ ከመጣላችሁ ግን 1 ትክክለኛ የDSTV ሳተላይት አልሠራችሁም በፋይንደር ኳሊቲ ቢመጣም ሌላ ሳተላይት ከሆነ 2 ገመዱ ችግር ካለበት 3Connector ስትገጥሙ ስህተት ካለው ብቻ ስለሆነ ከዚህ በዋላ ስትሠሩ ይህ ፁፍ ከመጣ ከላይ የሚገኙትን ነገሮች ተመልከቱ። DSTV ሪሲቨር እና የPackage አይነቶች __ DSTV ጎጆ በወር 220 ብር የምንከፍል ሲሆን ከ70 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ። DSTV ቤተሠብ በወር 380 ብር የምንከፍል ሲሆን ከ 100 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ። DSTV ሜዳ በወር 550ብር የምንከፍል ሲሆን ፕሪሜርሊግን ጨምሮ ከ 130 በላይ የተለያዩ ቻናሎችን ታገኛላችሁ ። DSTV ሜዳ ፕላስ ደግሞ በተሻለ ሁኔታ 160 ቻናሎችን የምታገኙ ሲሆን 1300 ብር በወር ትከፍላላችሁ። DSTV ፕሪሚየም በወር 2600ብር የምትከፍሉ ሲሆን ከ170 በላይ ቻናሎችን የምታገኙብ Package ነው። 482 viewsAdministrator, 14:35