Get Mystery Box with random crypto!

በ YOUTUBE እንዴት ገንዘብ እንሠራለን ???     ------------------------- | ዮናስ ሳተላይት ዲሽና ኤሌክትሮኒስ

በ YOUTUBE እንዴት ገንዘብ እንሠራለን ???
    ----------------------------------------
ሠላም ለናንተ ይሁን ውድ የቻናላችን ቤተሠቦች በዛሬው እለት ከYoutube እንዴት ገንዘብ እንሠራለን ? በምን አይነት መንገድ ገንዘባችንን መቀበል እንችላለን ? እንዲሁም ለመስራት ምን ምን ነገሮችን ማሟላት ይጠበቅብናል ለሚሉት ጥያቄዎች አጠር ያለ ፁፍ ይዤ መጥቻለው  መልካም ቆይታ !!!

Youtube ለመጀመር/ለመክፈት /

ማንኛውም ሠው ያለውን ተሠጦ ወደ ገንዘብ የሚቀይርበት ምርጥ የOnline ገንዘብ ማግኛ መንገድ Youtube ይባላል። በአሁኑ ሠአትም በሀገራችን ብዙ ሠዎች ቋሚ የገቢ ምንጫቸው አድርገውታል። ስለሆነም አንድ ሠው Youtube ቻናል ለመክፈት

1_ በቅድምያ Gmail አካውንት ያስፈልገናል። በተለምዶ Email የምንለው ሲሆን ብዙ የEmail አይነቶች የሚገኙ ሲሆን Youtube ለመክፈት ግን Gmail አካውንት ነው የሚያስፈልገው። በ Yahoo/Hotmail/ በመሣሠሉት መክፈት አንችልም ይህም Youtube አንዱ የGoogle መተግበርያ ስር የሚገኝ ስለሆነ ! ስለሆነም የግድ Gmail አካውንት ያስፈልገናል።
2_Email /Gmail እንዴት እንከፍታለን  ?
የgmail አካውንት ለመክፈት በመጀመርያ በስልካችን ከሆነ Google Chrome Browser በመጠቀም ወይም ስልካችን ላይ ባለ የInternet access በምናደርግበት ማንኛውም Browser መጠቀም ይቻላል። በመቀጠል www.google.com ብለን  search በማድረግ  ከዛን google ውስጥ ስንገባ ቀጥታ ከላይ Gmail የሚለውን በመንካት ወይንም sign up gmail account በማለት Search ማድረግ እንችላለን።

3_ ከዚህ በዋላ በሚመጣው ሳጥን ውስጥ የተለያዩ እኛን የሚገልፁ መረጃዎችን ካስገባን በዋላ  Create Account ብለነው Email አካውንት እንከፍታለን ማለት ነው።

Email አካውንት ስትከፍቱ የስልክ ቁጥራችሁን በማስገባት Verify ማድረግ አለብን። ሲቀጥል ደግሞ ይህን Email አድራሻ መርሳት የለብንም ምክንያቱም በዚህ Email አካውንት ነው ቀጥታ Youtube ላይ ገብተን Create Channel የምንለው። ስለዚህ Email አቹንና የምትጠቀሙትን የሚስጥር ቁጥር /Password / መዘንጋት የለብንም !
በስልካችን Google Chrome ስንጠቀም በቅድምያ  ከላይ የሚገኙትን 3 ነጥቦች በመንካት Desktop Mode ማድረግ አለብን።

በቀጣይ ከፍተን ማስተካከል ያለብን Setting ዎች እንዲሁም ምን ያህል ገንዘብ እንደምንሠራ ፖስት አደርጋለው