2023-03-12 21:46:00
ምኞት
ክፍል 40
ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
.
ስለናቱ እያወጋት ድንገት በመሀል " እባክሽ የኔ ፍቅር እሄን
ካጠገቤ ተኝቶ እኔ አንቺን ሳወራሽ የሚያገጠውን ጥርሳም ሰውዬ
ከዚህ ቤት አስወጭልኝ አላት •••
ምኛት ቀደም ብሎ ብቻውን ተቀምጦ አጠገቡ ሰው ያለ
እስኪመስል ድሩስ ሲከራከርና ሲጨቃጨቅ ስትሰማው ብትቆይም
ፈራች በቀስታ ቤቱን ከዳር እስከዳር ቃኘት አደረገችና በእንባ
የረጠበ ፉቷን ሽቅብ መልሳ ለሷ እና አጠገባ ላለው ሚስኪን
እብድ ፀለየች።
እናቴ ደስ ይበልሽ ልክ ነበርሽ አለና መሳቅ ጀመረ በሳቁ መሀል
እሄው ትመጣለች ባንተ አትጨክንም ከሀዲ አይደለችም ትይኝ
አለነበርሽ ። እንዳልሽው ተመልሳ መጥታለች ተመልሳም
አትሄድም ደስ አለሽ እናቴ? ክዳኛለች ካሀዲ ነች ብዬ ሰድቤሽ
ነበርኮ ይቅር በይኝ እሺ ፍቅሬ እናቴ ግን ሁሌ
ተው እንደሱ አትሁን ሰው እሚያጋጥመው አይታወቅም ቀድሞ
ማመስገንም ቀድሞ መኮነንም ደግ አደለም።
"እኔ እናትህ ጠፋች ጥላኝ ሄደች ስትለኝ ውስጤ አልደነገጠም
እናቴ ምን አለች ትለኛለህ ተመልሳ መምጣቷ አይቀርም ብቻ
አንተ በርታ በልልኝ። ልጄ ለኔ ለናትህ አታዝንልኝም አንድ ልጄ
እንዲህ ስትሆን ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ ልጄ ተው እሺ
በለኝ።ትልና ጎንበስ ብላ እንደ ህፃን ልጅ ጉንጮቼን ትስመኛለች።
እኔ አንቺን ፍቅሬን ሳጣሽ ህይወት አስጠልቶኝ የተመኘሁት ሞት
በምድር ላይ አንድ አለችኝ የምላትን እናቴን ነጠቀኝ ። እሂ ክፉ
ሞት የለመንኩትን እኔን ትቶ የምወዳትን ነጠቀኝ።
ግን መሞቷን ሰምተሻል የኔ ፍቅር እሄን እማ ይነግሩሻል ደና ነገር
አያወሩም እንጂ የሰውን ውድቀትና መርዶ ለማውራት ማን
ይቀድማቸውና! አላት ድክም ባለና የሀዘን ሲቃ ባዘለ ድምፅ።
ምኛት የመሳይ ንግግር ከራሷ እናት እና አባት በሞት መነጠቅ
መራር ሀዘን ጋር ተደምሮ አብራት የነበረውን ድምፅ አልባ ለቅሶ
ያለመንሰቅሰቅ ያለመጮህ ትግሏን አሸንፎ ያነፋርቃት ጀመር በልቧ
አዝላ የምትኖረውን የተጠራቀመ የመገፋት እና የብቸኝነት ብሶት
ከተቀበረበት ፈነቃቅሎ እየወጣ እየዬ አስባላት።
ጮኸች እስኪወጣላት ተንሰቀሰቀች።መሳይ ግን የመጨረሻዋን
ንግግሩን እንደተናገረ መዳኒቱ አሸንፎት ነበርና ስታለቅስ ሳይሰማት
እንቅልፍ ጥሎቷል ።
አልቅሳ ሲወጣላት የታጠፈውን የመሳይን እጅ አስተካክላ አንሶላ
አለበሰችው እንዳይበርደውም ብርድልብሱን ደረበችለት።
አጠገቡ ቁጭ ብላ የተኛውን መሳይ ቁልቁል እየተመለከተችው
ስለ ፍቅር ሀያልነት ማሰላሰል ጀመረች።
ፍቅር ግን ምንድን ነው?
ትልቅ አይል ትንሽ፣ሀብታም አይል ደሀ፣የተማረ አይል
ያልተማረ፣ያበደ አይል ያላበደ
ጤነኛውን የማሳበድ ያበደውን ጤነኛ የማረግ ሀይል ያለው
ማንም ላይ ለመንገስ ከልካይ የሌለው ሁሉን የሚያንበረክክ
በስቃይ ውስጥ በችግር ውስጥ በረሀብ ውስጥ በእብደት ውስጥ
ቦታውን የማይለቅ ግዛቱን የማያስደፍር የማይለዋወጥ ጣፋጭ
ስቃይ።ለነገሩ ፍቅር ከፈጣሪ ነውና እሱን የሚቋቋም ሀይል
አለመኖሩ አይገርምም።
አብዶም ስለሷ ሲያወራ ለሷ ያለው ፍቅር ትዝታ የሷ ናፍቆት
ሁሌም አንድ መሆኑ ይገርማል አለችና በተኛበት ደና እደር ብላው
ወደ መደበቂያ ዋሻዋ ወደ እቃ ቤቷ ገብታ በሯን ዘጋግታ ተኛች።
የመሳይ እህት ትንቢተ ለመሳይ ከቁርስ እስከ እራት የተለያየ እና
የሚወደውን ምግብ ለማዘጋጀት ሌሊት 11:30 ላይ ነበር
ከእንቅልፏ የተነሳችው ። አዘጋጅታ እንደጨረሰች ወደ አባቷ ክፍል
ሄደች ዝግ ነው።ተኝተዋል። የንጀራ እናቷ ስላለች መቀስቀስ
አልፈለገችም። ኮንትራት ይዛ ወደ መሳይ ጋር ሄደች።ምኛት እና
መሳይ በሂወት አጋጣሚ በተለያየ ምክንያት እቃቤትና ሳሎን ቤት
ሳይፈልጉ ወደ ተጣሉበት ኮንደሚንየም እስክትደርስ ስለ ወንድሟ
መሳይና ወንድማን ወስዶ ስለደበቀው አባቷ ጭካኔ እያሰላሰለች
ትብሰከሰካለች።
አባቷ መሳይን እዛ እንዳስቀመጠው የሙት እናቷ ዘመዶች
እንዳይሰሙ የሚያደርገው
ጥንቃቄ ጭራሽ የተበዳይነት ስሜት እንዲሰማት በማድረጉ እልህ
ይዟት አባቷ ወንድማ የንጀራ እናታቸው እቤታቸው እንድትገባ
ስለማይፈልግ ብቻ አንድ ኮንዶሚንየም ወደ ሚባል የከተማ
ውስጥ ምሽግ አስገብቶ ከውጪ በመቆለፍ ብቻውን
እንዳስቀመጠው ለመናገር ጫፍ ላይ ደርሳለች።
"እርግጠኛ ነኝ እንኳን የማሚ ዘመዶች የራሱ ዘመዶች እንኳን
ቢሰሙ አባቢ ላይ ያዝኑበታል ግን ደሞ ሲሰሙ መሳይን እኛ ጋር
ይሁን ማለታቸው አይቀርም በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ደሞ ወንድሜ
የሰው ፊት እንዲያይ አልፈልግም።"እያለች ከራሷ ጋር ታወራለች።
"ለማሚ ዘመዶች ግን አሁን ቁርሱን አብልቼው እንደወጣሁ ነው
ሄጄ ሁሉንም አንድ በአንድ የምነግርለት ። አሁን እማሚ ብትሆን
እንደዚህ ታደርግ ነበር?በፍፁም አታደርግም!!"
አለችና እምባ ሲተናነቃት እፉፉፉ ብላ በመተንፈስ እንባዋን
ለመቆጣጠር መከረች"
"በሰላም ነው?ችግር አለ እህቴ?" አላት ሹፌሩ።
መልስ ሳትሰጠው እንዳቀረቀረች ደርሳ ወረደችና አይናን
እየጠራረገች ደረጃውን ቶሎ ቶሎ ወጥታ የኮንደሚንየሙን በር
ከፍታ ገባች።እዚህ ኮንደሚንየም ተደብቃ መኖር ከጀመረች ጀምሮ
እንቅልፏ ሁሉ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት እና እሷ ብትተኛም
ጆሮዋ የማይተኛው ምኛት ትምቢተ በሩን ከፍታ እንደገባች
ወድያው ነበር ከንቅልፋ በመንቃት ተነስታ ቁጭ ያለችው።
ትንቢተ ወደ ሳሎኑ ስትዘልቅ መሳይ የሞት ያህል በጥልቅ
እንቅልፍ ውስጥ ነበር።
ጠጋ ብላ እንደ እባብ ጥቅልል ብሎ የተኛውን መሳይ ሀዝንና
ስስት በተሞላ ስሜት ቁልቁል ታየው ጀመር።
ፍራሹ ላይ በጉልበቷ ሸብረክ አለችና በዝግታ እያንቃነቀችው
"ወንድሜ መስ አንተ መሳይ"
እያለች ስትቀሰው ፍንጥር ብሎ ተነሳና ሲሮጥ የመጣ ያክል
ዙርያውን እየቃኘ ያለከልካል ።
ትንሽ እስኪረጋጋ ግዜ ሰጠችውና "ምንድን ነው ምትፈልገው ምን
ሆነካል ወንድሜ?"
አለችው።
ምንም ሳያወራ ተወርውሮ አንገቷ ላይ ተጠመጠመና...
"ማታ መጥታ ነበር እህት አለም :ማታ አብራኝ ነበረች :እውነቴን
ነው እህቴ ማታ በትክክል ነክታኛለች አብራኝ አምሽታለች
መዳኒቴንም አውጣኛለች።
እህቴ ማታኮ መጥታ አብራኝ ፍራሹ ላይ ነበረች ስትገቢ
አላገኘሻትም? መጣሁ ብላሽ ሄዳ ነው? ንገሪኝ እህቴ?
ትመለሳለች አደል ? ጥላኝ አልሄደችም አደል እህት አለም?"
አላት በማልቀስ እና በመሳቅ መሀከል ሆኖ ድብልቅልቅ ባለ
ስሜት ።
አንገቷን ከመጠን በላይ ጥብቅ አርጎ ስለአቅፏት ትንፋሽ ያጠራት
ትንቢተ
" ማን ....ነች እ.....ሷ ? ወንድሜ! ማነች ማታ የመጣችው
ስትለው........
.............ይቀጥላል............
140 ከገባ#ክፍል 41 ዛሬ ይለቀቃል
ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥልLike ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
1.3K viewsflawoless , 18:46