Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ werkamaa — ወርቃማዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ werkamaa — ወርቃማዎች
የሰርጥ አድራሻ: @werkamaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 351

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-06 19:28:20 I fall in love with people who are caring even if we don't talk.

I fall in love with people who checks on me even if I want to stay distant and away.

I fall in love with people who wants to reconnect after a long disconnection.

I fall in love with people over and over again when we're mad but we still manage it.

Life is short.
Maybe there is no tomorrow to sort things out.
@WERKAMAA
50 views@ñwăř, 16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 21:06:39 ተማሪዎች! ትልቅ ፊኛ (አፉፋ) ቢፈነዳ በ አሜሪካን ጭቃ በማጣበቅ ወደ አገልግሎት መመለስ ይቻላል? መልሱን ለመምህራችሁ ንገሯቸው።
እባክዎን መምህር መልሱን ከተማሪዎች ይቀበሉ። እናመሰግናለን!
@WERKAMAA
66 views@ñwăř, edited  18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 11:01:50 ስኬት የመልካም አስተሳሰብ የትክክለኛ ጥረት ውጤት እንጂ የዕድል ጥርቅም አይደለም።በጥረትና በትጋት የፈጠርከው እድል እንጂ በአጋጣሚ ውህደት የሚፈጠርልህ እድል ለመኖር ሞራል የገደለው ሰው ያደርግሀል።ሰው ከሰጠህ ነገር ይልቅ በጥረትህ አንተ ያመጣሀው ነገር እርካታ ይሰጥሀል።

መልካም እሁድ
@WERKAMAA
76 views@ñwăř, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 09:47:41 They got money for war
But they can’t feed the poor.
(2pac)
@Werkamaa
71 views@ñwăř, 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 09:06:56 ስንት ሃጢያተኛ በበዛበት ዓለም
ገዳይ ፈራጅ ቢሆን የሚገርም አይደለም
@Werkamaa
71 views@ñwăř, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 22:51:05 1 የታሸገ ግማሽ ሊትር ውሃ የሰፈር ሱቅ ውስጥ 10 ብር ይሸጣል።
ሱፐር ማርኬት ውስጥ 15 ብር ይሸጣል።
ባር ውስጥ 25 ብር ይሸጣል።
እራሱ ውሃ ቆንጆ ሬስቶራንት ወይም ሆቴል ውስጥ ደግሞ እስከ 50 ብር ይሸጣል።
ውሃው የታሸገበት የላስቲክ ጠርሙስ፣ የውሃው ስም አንዳይነት ነው።ለምን ዋጋው ተለያየ? ቦታው ነው የዋጋ ልዩነቱን ያመጣው።
ዋጋ እንደሌለህ ከተሰማህ ፣በአካባቢህ ያሉ ሰዎች የሚያሳንሱህ ከሆነ ቦታህን ቀይር፤ እዛው አትቅር!!
ለራስህ ዋጋ ስጥ!!
@WERKAMAA
74 views@ñwăř, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 13:15:18 የታክሲ ገጠመኜን እንኩማ

የው ሩቅ ተጓዥ ነኝ .... በቲኒሹ ታክሲ ውስጥ 1 ሰዓት እቀመጣለሁ .... ከዛም በላይ

አንዲት ጠይምዬ ቆንጅዬ ቲኒሽዬ/አስራዎቹ/ የሆነች ልጅ አጠገብ 3ተኛ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ .... በእጇ ፌስታል ምናምን ይዛለች

ወደ ጥግ አሳለፈችኝ

ቲኒሽ እንደተቀመጥን ስልኬን አውጥቼ ደዋወልኩና እዛው እጄ ላይ እንደያዝኩት ጉዞ ጀመርን

ስልክ አስደውዪኝ አለችኝ

እሺ እንኪ /ከፍቼ ሰጠኋት/

የደቡብ ልጅ መሰለችኝ ቋንቋዋን መለየት አልቻልኩም ደቡብዬ መሆኗ ግን እርግጥ ነው

ላውድ አድርጋ ደወለች ለአንድ 3 4 ደቂቃ አወራች ተዘጋ

እጄን ዘረጋሁ ስልኬን ልቀበል .... እሷ ወይ እቴ ሌላ ቁጥር መምታት ጀመረች ቅር አልተሰኘሁም አጠገቧ ነው ካርዱን የሞላሁት .... ካርድ አለው ብላ ስላሰበች ነው ፈታ ብላ ምትደውለው ብዬ ፊቴን አዞርኩላት

ከሁለተኛው ጋር የሚያወሩበት ደቂቃ ሲረዝም ቆይ ልደውልልሽ ብሏት መሰለኝ/የው ቋንቋውን ስለማይገባኝ ገምቼ ነው/ ዘጉ። አሁን ጨረሰች ስል መልሶ ደወለ እኔና ስልኬ ለረዥዥዥም ደቂቃዎች ተለያየን ..... አያልቅ የለ ተዘጋ

አሁን በቃሽ አይነት አስተያየት እያየኋት እጄን ዝርግት

ቆይ አንዴ አለችኝ የምታምረዋን ፈገግታዋን እያሳየችኝ በተሰባበረ አማርኛ

ፊቴን ወደ መስታወቱ አዙሬ ሳቅኩ .... ቲኒሿ እህቴን መሰለችኝ .... በቃ እኔን እህቷ አድርጋ በልበ ሙሉነት ስልኬን መያዟ .... ምንም አትለኝም የሚል እምነቷ እህቴ ናት ማለቷስ አይደል?

ነፃነቷ ገረመኝ .... የዋህነቷ አስቀናኝ .... የከተማ ሰው ልቡ በብዙ አጠራጣሪ ነገሮች መሞላቱን ያልተረዳች አዲስ አበባን በብዙ ያላወቀቻት መሆኗ ገባኝ ..... ለሶስተኛ ሰው ደወለች

ወላሂ ሳቋ ጨዋታዋ አይደለም የሰው ስልክ የያዘች .... በታክሲም የተሳፈረች አትመስልም .... ደስ አለችኝ ... ምን አባቱ ትጨርሰው ይሄን የዋህነቷን ልነጥቃት አልፈለግኩም .... ደስ እንዳላት እንድንለያይ አሰብኩ ... ስልኬን ረሳሁላት

አታምኑኝም አራተኛ ተደወለ

ይሄ ደውል የመጨረሻ ነበር .... እንኪ አናግሪያት አለችኝ

ሔለው
አቤት
እናት እንደው አደራ ጀሞ ሚካኤል ጋር ስትደርስ ንገሪያት .... እሷ ስለማታውቅ ነው .... አደራ እሺ ብረቱ ጋር ማደያው ጋር አውርጂያት
እሺ እማ እሺ ደርሰናል ቲኒሽ ነው የቀረን .... (መውረጃዋ ጋር ልትደርስ አንዲት ፌርማታ ሲቀራት ነበር ስልኬን የሰጠችኝም አሳያት የተባልኩትም)

አመሰግናለሁ አለችኝ .... ልብን ደስ ከሚያሰኝ ፈገግታዋ ጋር

የዋሆችን አኑርልን
@WERKAMAA
96 views@ñwăř, 10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 21:27:35 አንድ ሰው እባብ በእሳት ተቃጥሎ ሊሞት ሲል! ከእሳት ሊያወጣው ወሰነ! እያወጣው ባለ ግዜም ነደፈው በነደፈውም ጊዜ እራሱን ለማዳን ሲወራጭ እባቡ ተመልሶ እሳት ውስጥ ወደቀ ሰውዬው ለዛ አዘነ... እና እሳቱ ውስጥ የወደቀበት ምክንያት እሱ እንደሆነ አሰበ! እናም ሰውየው በቀኝ እና በግራ ዙርያውን ተመለከተ!

የብረት ዘንግ አግኝቶ ተጠቀመበት! እባቡን ከእሳቱ ለማውጣት እናም የእባቡን ህይወት አዳነው ይህን ሲያደርግ አንድ ሰው እያየ ነበር ከዚያም ወደ ሰውዬው ቀረበና፦ ይህ እባብ ነድፎሀል፣ ለምን ልታድነው ፈለክ? ብሎ ጠየቀው ሰውየውም መልሶ፦ የእባቡ ተፈጥሮ ቆሻሻ ነው! ይህ ግን ምህረት እና እርዳታ የሆነውን ተፈጥሮዬን አይለውጠውም!!! በማለት መለሰ!!

#አንድ_ሰው ስለ ጎዳህ ብቻ #ተፈጥሮህን እና #ሰብዐዊነትህን በቀላሉ አትቀይር! ሁል ግዜ ክፋትን በደግነት መልሰው!

@Werkamaa
@Werkamaa
@Werkamaa
120 views@ñwăř, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 20:22:40 ደስስስስ ይለኛል ..... ደግሞ ይቀጥልና ደስም አይለኝም .... እሰለቻለሁ .... በረታለሁ ..... አለቅስ አለቅስ .....አለቅስና እያለቀስኩ እስቃለሁ ..... ሳቄ አልቅሼ ማላውቅ ያህል እስኪሆን ..... ስከፋ ተደስቼም ስቄም ማላውቅ ያህል የሆነ !

ወዳለሁ ! ፍቅር ክንፍ እስኪያደርገኝ ..... እብድ ንድድ ጭስስ እስክል እወዳለሁ .... እማረካለሁ ስለ-ፍቅሬ ስለ-ውዴታዬ እዬዬን አክላለሁ ...... ማፍቀርን መውደድን የመሰለ ወይን እጎነጫለሁ ..... አጣጥማለሁም

ይደግም ይደግምና ....... ጥላቻ ይይዘኛ ..... የሚያስጠላኝ ያስጠላኛል ..... ጥልት ጥልትልትትትት አድርጌ ጠላለሁ ..... በልቤ ስር ፍቅር ዘሩን ዘርቶ ማያውቅ መስል እጠላለው ..... እስጥልት አድርጌ ጠላለሁ ...... መጠላላትን እስክጠላ ጠላለሁ .... ጥላቻዬንም ጠላዋለሁ

ሰው የመሆን ቅኔዬ .... በአንድ ዓለም ብዙነቴ ..... በአንድ ልብ ብዙ ማንነት .... የትናንት የዛሬ የነገ ሁነት .... ሁሉም እኔ'ነት ..... እኔም ሁሉነት .... ሰውነቴ
@WERKAMAA
152 views@ñwăř, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 11:39:54 #እኔ_ማን_ነኝ ?

" በህይወቴ መናገር ያቃተኝ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ። ይኸውም አንድ ሰው " አንተ ማነህ "? ብሎ የጠየቀኝ ጊዜ ነው " ይላል
ካህሊል ጂብራን

እኔ ማን ነኝ ? የሆነ ነገር ትርጉም ነኝ ? ወይስ በልባዊነትና በህላዌ የምገለጥ ማንነት ያለኝ ሰው ? ሰው ምንድነው ? ብንባል እንመልስ ይሆናል ። ሐይማኖታዊ ትንታኔውን ዶግማ አጣቅሰን ፣ ስነፍጥረት አዋዝተን እንተነትን ይሆናል ። ከሳይንሱም እየቀዳን ፣ ከፍልስፍናውም እያዳቀልን ሰው ይሔ ነው እንል ይሆናል ። ግን ጥያቄው ሌላ ነው ። ሰው የተባልከው አንተ ማነህ ? ማነኝ ብለህስ መልሰህ እየኖርክ ነው ? ማንነታቸውን ማነን ብለው ለማይጠይቁ ሰዎች ማንነትህን ማነኝ ብለህ አስረዳሀቸው ? እኔ ይሄንን ነኝ ያን አይደለሁም ያልካቸው ያን ስለምትወድ ፣ ይሔንን ስለምትጠላ ነው ወይስ አንተ ነኝ ያልከውን እውነት ያን ሆነህ ነው ? እኔ ይሄን ነኝ ብለህ ባስቀመጥከው ልክ ውስጥ እኔም ይሄን ነኝ ብሎ አንተን የመሰለ ስታገኝ ደስ እያለህ ትዘልቃለህ ወይስ እሱን ላለመምሰል ሌላ " ያን ነኝ " ትፈጥራለህ ?

ድክመትህን ከጥንካሬህ ፣ እውቀትህን ከስነ-ምግባርህ ፣ ኑሮህን ከማህበረሰብህ ፣ ሰላምህን ከሰው ሁሉ ጋር ፣ ደስታህን ከወዳጆችህ ፣ ሀዘንህን ከሰብአዊነትህ ጋር እኔ ብለህ በሳልከው ቋትህ ውስጥ ሆነህ እያት ። በምትጋራበት አውድ ሰው የምትለው በሩቅ ያስቀመጥከው ማህበራዊ ህይወት አስተሳስሮ ፣ የኑሮ እሴት ያዋቀረው የሩቅ ቅርብህ አንተን ምን ብሎ ያውቅሀል ? በጣም ቅርቤ ናቸው ስለኔ እነሱ ከተናገሩ ይበቃል የምትላቸው ሰዎች የትኛውን አንተን ነው የሚያውቁህ ? አነዛ ብለህ የምታርቃቸው በሩቅ የሚያውቁህ የኔ ካልካቸው አንተ በሰጠሀቸውና ባሳየሀቸው ማንነትህ የሚያውቁህ እኔ ማነኝ ብለህ ስትጠይቅና አንተ ለራስህ የምታውቀው ማንነትህ ስንት ናችሁ ?

ማነህ ሲሉህ ነኝ ያልካቸውን መሆን የምትፈልገውን ነው ? ፣ እየሆንክ ያለኸውን ነው ? ወይስ እንዲሆኑልህ የምትፈልገውን ነው ? ለዚህ ጥያቄ መልስ እኔ ይሄን ነኝ ብትል እንኳን መልስህን ተከትሎ እውን አንተ እሱን ነህን ? አሁን ያልከውን ይልሀል ። ስለዚህ ማንነት ሰፊ ነው አንድ መልስ የለውም ። እንደ ፍላጎታችን እና እንደሚያውቁን ሰዎች ብዛት ፣ የሚያውቁን እኛን እንደሚረዱበት ልክ ፣ ሌሎችም እኛን እንደሚያዩበት እይታ ብዛት ማንነታችንም ብዙ ነው ። እናም ሁሉንም ተወውና አንተ ማነህ ? ሲሉህ አትኩራ ፣ ደንገጥ በል ፣ እኔ ማነኝ ? በል ቢያንስ ጣት መጠቆምንና እሱኮ .. ማለትህን ይገታልሀል ።
@WERKAMAA
140 views@ñwăř, 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ