Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ werkamaa — ወርቃማዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ werkamaa — ወርቃማዎች
የሰርጥ አድራሻ: @werkamaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 351

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-01-12 22:20:45

አንተ ለሰዎች ያለህ አቀራረብ እነሱ ላንተ የሚኖራቸውን አቀራረብ ይወስነዋል።

አዎ ወዳጄ በጥሩ ባህሪ ቀርበን አናግረናቸው ንግግራችንን ሆነ ሀሣባችንን ይቀበሉናል ምናልባት ባይቀበሉን እንኳን ያከብሩልናል።

ለጥሩ ነገራቶች ምላሽ ምስጋና ሊሆን ይችላል።

ሌላው ደግሞ ወዳጄ ሰዎችን የምንቀርብበት ወይም የምናናግርበት መንገድ ከንግግራችን ጀምሮ አክብሮት ትህትና ከሌለው፤ ማንኛውንም ቃል የምንጠቀም ከሆነ ለኛም ክብር አይኖራቸውም በንግግራችን ይለኩናል

ማንኛውንም ነገር ስንጠቀም በጥበብ መሆን ይኖርበታል። ካልሆነ ግን ጋጥ ወጥ ሊያስብለንም ይችላል።

Share
መልካም ጊዜ
https://t.me/WERKAMAA
96 views@ñwăř, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 18:11:05 ጨለማውን ከመርገም ይልቅ ፋኖሱን አብራ።

ወዳጄ በዚች አለም እስካለን ድረ ስ ጨለማ እናያለን ፣
ጨለማ ውስጥ እንገባለን ፣
በጨለማ ውስጥ የቀሩ ሰዎችን እናያለን፣ በጨለማ ውስጥ የቀሩ ስዎችን እናገኛለንም

ግን ወዳጄ

በጨለማው ተቀምጦ ንጋትን ከመናፈቅ በጨለማው ውስጥ ለገቡት ብርሃንን ከመመኘት
በጨለማው ከመማረር ንጋት እንዲመስል
ጨለማውን በብርሃን እንለውጥ።

በየትኛውም አይነት ችግር ውስጥ ብንሆን ከመበሣጨት ከማዘን ይልቅ መፍትሄውን እንጠቀምበት!!


♡ Share&join
መልካም ጊዜ
https://t.me/Werkamaa
40 views@ñwăř, edited  15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 17:42:40 አዲስ ቤት ገዛህ? ዝም በል አታውራ

አዲስ መኪና ገዛ? አትናገር

ትዳር መሰረትክ? ብዙ አታውራለት

ለመዝናናት ከከተማ/ሀገር ወጣ ብለህ ነበር? ዝም በል

ንግድ ልትጀምር ነው? ድምፅህን አጥፋ

ኑሮ እየሰመረልህ ነው? ብዙ አታውራ

አብዛኛውን ጊዜ
ያሰብናቸው ህልሞች እና የወጠንናቸው ራእዮች የማይሳኩበት ዋነኛው ምክንያት ከመከናወናቸው በፊት ብዙ ስለምናወራ ነው -ገና እንቁላሉን ስንታቀፍ ማውራት እንጀምርና ብዙ ሸለምጥማጦችን እንጠራለን::

ወዳጅ እና የቅርብ ሰዎች የምንላቸው ሰዎች "ሰዋዊ ቅናት" እና "የጥሎ ማለፍ ውስጣዊ ትንቅንቅ" በጣም የሚጠበቅ ተፈጥሯዊ ሁነት ነው:: ስለዚህ ህልሞችህ መስመር ይዘው ፍሬ እስኪያፈራ ድረስ ዝም ብለህ መስራትን ምረጥ::

አብዛኛው ሰው
ቢያልፍልህ እና ህልምህ ቢሰምርልህ ደስ ይለዋል ሆኖም ግን ጥለኸው እንድትሄድ እና አንጋጦ ሊያይህ ይተናነቀዋል::

@WERKAMAA
48 views@ñwăř, 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 12:44:02 ጮማዬን ደብቄ ብቻዬን ልበላው
ጣፋጩን እርጎዬን ሸሽጌ ልጠጣው
ድርቡን ሸማዬን ደብቄ ልለብሰው
ድሃ ጎረቤቴን ምንም እንዳያምረው
"ቸግሮኛል" አልኩት "ለአፌም የምቀምሰው..."
ጮማዬን ሸሽጌ እጦቴን ስነግረው
ድሃ ጎረቤቴን እምባ ተናነቀው
"እኔ አለኝ!" እያለ ሄደ ከቤት ወጣ
ሽምብራውን ይዞም ሊያካፍለኝ መጣ
@Werkamaa
57 views@ñwăř, edited  09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 09:10:41 በህይወት እስካለህ ልትሳሳት፣ ልትወድቅ ትችላለህ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ወይም ሀሳብህን ላይረዱ እና ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ።

በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ፣ ሊያሙህ፣ ስም ሊያወጡልህ አሊያም ሊስቁብህ ይችላሉ።

በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው።

መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።
አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል።
ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞች ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል።
ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።

ምን አለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም ልትጠላም አትችልም።

#ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር።ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!
በህይወትህ ማንንም አትውቀስ! ጥሩ ሰዎች ደስታን፣ መጥፎ ሰዎች ልምድን፣ ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያን፣ ምርጥ ሰዎች ትዝታን ይሆንዃችኋል።
@Werkamaa
47 views@ñwăř, 06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 09:30:19

ህጻን ልጅ እንደ እርጥብ ሸክላ ነው።በፈለግነው መልኩ ልንቀርጸው እንችላለን።

ወዳጄ ልጅን የምናሣድግበት መንገድ ተጽኖ ከባድ ነው።በርግጥ እኛ ባሣየናቸው መንገድ ይጓዛሉ ።

እነሱ ከመጓዛቸው በፊት ግን ስለ መንገዱ ጥቅም ጉዳት አጠቃላይ ሁኔታ ማወቁ የእኛ ድርሻ ነው።
.
ስለዚህ የሂወት ተምሣሌት መስጠት፣ የተቃናውን መንገድ ማመላከት፣ መሰናክል ስለበዛባቸው መንገድ ፣ ውድቀት እና ውጤታቸው ማስተማር የኛ ሀላፊነት ነው።

በርግጥ ለልጅ የሚሆነን ታላቅ ተምሣሌት አለን ቢሆንም ማሣየቱ የኛ ድርሻ ነው!!


ሼር ለወዳጆ
መልካም ጊዜ
https://t.me/Werkamaa
69 views@ñwăř, 06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 21:49:19 << ረጅም ፅሁፍ ለሚመቸው ብቻ >>
==================
መልኩ ይለያይ እንጂ ሁላችንም ባዶነት እንዲሰማን የሚያደርጉን ክፍተቶች አሉን ።ምናልባት በጤናችን ሁኔታ ፣ በቤተሰብ situation ፣ አሊያም በባህሪያችን ፣ አድርገናቸው እንደ እግር እሳት በሚለበልቡን ድርጊቶች ፣ ወይ ደግሞ እንዲ ቢሆን እንንዲያ ቢሆን ኖሮ በምንላቸው ምኞቶቻችን ውስጥ .........።

ብቻ ስንኖር አለች የሆነች ስትነካ የምታመን ፣ትዝ ስትለን የምትሰቅዘን ፣ የዳነ እግራችን የሚያነክስባት ፣ የመኖርን ትርጉም የምናጣባት SPOT..... መኖር መተንፈስ ከሆነ አለሁ ብለን እጅ የምናወጣ እልፍ ሰዎች አለንኮ። የሚገርመው part ደግሞ ደስተኛ መስለን ለመታየት የምንጋጋጠው ነገርስ I think we are the kind of people who smiles the most when it hurts ተገልቦ አልታየልን እንጂ ስንቱ በፈገግታው ድንኳን ተከልሎ ታሞ ኖሯል።

ለነገሩ ይዘቱ ይለያይ ይሆናል እንጂ ሁሉም ሰው ከሰው ደብቆት ከህሊና ጓዳው ቀብሮት ያስቀመጠው የብሶት ቀን መዞ የሚያለቅስበት ህመም አይጠፋውም ። በሳቅ እንደ ቄብ ዶሮ የሚያስካካበት ትዝታዎችም አሉት። አይገርምም ወደፊት እየኖሩ የኀሊት መጓዝ አሜን ብሎ መቀበል ነው። its like የመኪናን የኃላ መስታወት(ስፖኪዮ) እያዪ ወደፊት እንደመንዳት ማለት ነው። its dangerous ግን ደግሞ ደስ ይላልም። በምግብ ብንመስለው ከትናንት ማዕዶቻችን ላይ በያይነት አኑረን እንደመመገብ ማለት ነው።

ከፍታው ይለያይ እንጂ ሁላችንም ከፍ ብለን የበረርንባቸው ፣ ዝቅ ብለን ከወለል ያደርንባቸው ቀናት አሉን። ሀ ሀ ሀ ብለን የሳቅንባቸው ቀናት እንዳሉ ሁሉ ፣ እህ ህ ህ ብለን ያለቀስንባቸው ግዜያትም ነበሩን። ድሮ ልጅ እያለን ቀና ብለን በኩራት ያለፍናቸው መንገዶች የሉንም ፣ እሺ በሰቀቀን የታጠፍናቸው የሰፈራችን ኩርባዎችስ የሉም??? አድገን ዛሬም ድረስ ኩርባዎቹ መልካቸውን ይቀይሩ እንጂ ሁሌም ለመታጠፍ የምንፈራው መንገድ አለ። ለመሻገር ፈርተን እጄን ያዙኝ የምንልበት ድልድዮችም አሉ ። (ብዙ ድልድይ ፊት ቆሞ አሻጋሪ እጅ ጠባቂም እንዲያው)። ወደድንም ጠላንም ፍርሀቶቻችን የመኖር የፊት ገፆች ናቸው ። እነርሱን ገልጦ የማለፍ ወኔው ከሌለን ሁሌም ከድልድዪ ወዲህ እንደቆምን መቅረት፣ ከኩርባው ወዲያ ያለውን ፀዳል ለማየት አለመታደል ፈንታችን ይሆናል።

ግን እነዛን ያለፈፍንባቸውን የማይረሱ እና ከባባድ ግዜያት ወደ ጎን ባላየ ትተናቸው መሄድ ከቻልን እና ይቺ አለም ለጠንካሮች እንጂ ፈርተው መንገድ ላይ ለቀሩት መቼም ቦታ ሰታ እንደማታውቅ ገብቶን እና ሁሉም ነገር ጊዜያዊ እንደሆነ ከባነንን(ህመሙም ቢሆን)
ያኔ....እንደኛ ጀግና አይኖርም ...እመነኝ
@WERKAMAA
60 views@ñwăř, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 19:59:13 አንድ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሚከተለውን ድንቅ ጥናት እንዳገኘ ይፋ አድርጎ ነበር።ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠ፦ A b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z የእነዚህን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል አስቀመጠ፦ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 በጥናቱም ለእያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሰጠ ለ A=1፣ ለ B=2......እያለ እስከ Z=26ን ሰጠ።
በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ።

1.ትጉ ስራ
( H+a+r+d+w+o+r+k )
( 8+1+18+4+23+15+18+11 )=98%

2.እውቀት
( K+n+o+w+l+e+d+g+e )
( 11+14+15+23+12+5+4+7+5 )=96%

3.ፍቅር
( L+o+v+e )
(12+15+22+5 )=54%

4.እድል
( L+u+c+k )
( 12+21+3+11 )=47%
በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸውን ቃላት አንዳቸውም 100% ለውጥ ሊሰጡ እንደማይችሉ አስቀመጠ።ታዲያ 100% ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድነው ? ገንዘብ ይሆን?

5.ገንዘብ
( M+o+n+e+y )
( 13+15+14+5+25 )=72%
አይደለም ምናልባት አመራር ይሆን?

6.አመራር
( L+e+a+d+e+r+s+h+i+p )
( 12+5+1+4+5+18+19+8+9+16 )=97%
አሁንም አይደለም ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው።አስተሳሰብ፣ አካሄድ፣ አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል።ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ።

7.አስተሳሰብ
( A+t+t+i+t+u+d+e )
( 1+20+20+9+20+21+4+5 )=100%
እናም ውጤትና የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው #የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አረጋገጠ።


@Werkamaa
61 views@ñwăř, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 00:17:56 #ለፈገግታ

በጀርመን ሀገር የሒትለር ልጅ አብሮ ከሚማርበት ክፍል አንድ መምህር "ተማሪዎች በክንፋቸው ከሚበሩ እንስሳት መሀል አንድ ጥቀሱ?"ብሎ ይጠይቃል።

በዚህ ቅፅበት የሒትለር ልጅ እጁን አውጥቶ "ዝሆን!"በማለት መለሰ።
መምህሩም "አጨብጭቡለት! ሞቅ አድርጋችሁ አጨብጭቡለት...የኔ አንበሳ!" ይላል።ክፍሉም በጭብጨባ ብዛት ቀውጢ ሲሆን ይሄን የሰማ ርዕሰ-መምህር ይመጣና "ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቅ አስተማሪው ጉዳዩን ሹክ ይለዋል።

ከዚያም ርዕሰ-መምህሩ "ደግማችሁ አጨብጭቡለት እንደዚ አይነት እሳት የሆነ ተማሪ ከየት ይገኛል!" እያለ ጠጋ ብሎ ለመምህሩ በጆሮው "ወንድሜ እኛ ከምንበር ዝሆኑ ቢበር ይሻላል" አለው።
@Werkamaa
50 views@ñwăř, 21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 21:10:36 ለወርቃማዎች


"………በየቀኑ ልብሶቻችንን እንደምንመርጥበት መንገድ ሀሳቦቻችን እንዴት እንደሚመረጥ መማር ያስፈልገናል ፡፡ ይህ ለማዳበር የሚያስችል ኃይል ነው ፡፡ በሕይወታችን ውስጥ በጣም መጥፎ ነገሮችን ለመቆጣጠር ከፈለግን በአዕምሮዕችን ላይ እንስራ፡፡ ለመቆጣጠር መሞከር ያለብን ያ ብቻ ነው………!"



ውብ አሁን

┄┉✽‌»‌ ‌ ‌»‌✽‌┉┄
@Werkamaa
@Werkamaa
┄┉✽‌»‌ ‌ ‌»‌✽‌┉┄
62 views@ñwăř, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ