2022-07-20 20:23:45
ጎንደር የአሸባሪዎች ሃገር
===================
ተበዳይ ካሳ ከፋይ የሆነበት "ፍትሕ"
የጎንደር ከተማ ሙስሊም ተዘርፎ ለወደመበት ንብረት ካሳ ማግኘት ሲገባው ስለምን መልሶ ካሳ ሰጭ እንዲሆን ይገደዳል!?
በመርህና በፍልስፍና ደረጃ የህዝብን አደራ የተቀበለ መንግስት በአመራርነት የሚሾማቸው ግለሰቦች በዕውቀታቸው፣ በስራ ልምዳቸውና ችሎታቸው ነፃ ገለልተኛና ፍትሐዊ አስተሳሰብን መነሻ በማድረግ ከአድሎ፣ ከወገንተኝነት፣ ከጥላቻ፣ ከቡድንተኝነት እና ከጎጠኝነት በፀዳ አግባብ የተወከሉበትን የማህበረሰቡን ችግር በአግባቡ አዳምጦ በእኩልነትና በነፃነት መንፈስ መፍትሄ በመስጠት የማገለግል ግዴታ እንዳለበት እሙን ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ኢትዮጲያ በተለይም በአማራ ክልል ጎንደር እና አካባቢዋ እየተስተዋለ የመጣው አብሮነትን እና የመቻቻልን እሴት ገፊ የሆኑ ኃይማኖታዊ ፅንፈኛነት ተበራክተዋል። እነኝህ የፅንፈኛ እሳቦቶች እና ኃይሎች የአንድን ኃይማኖት የበላይነትን ለመጫን በማሰብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ለዘመናት ተዋዶ እና ተከባብሮ የኖረውን ሙስሊም ማህበረሰብ በተለያዩ ወቅቶች ዘርፈ ብዙ ጥቃቶችን ሲያደርሱበትና ሲገፉት በተደጋጋሚ አስተውለናል።
ባለፉት ዓመታት እነኚህ ፀረ-ብዙሀን ፅንፈኛ ኃይሎች በአካባቢው ሙስሊም ላይ ጥቃት በማድረስ ላጠፉት ተደጋጋሚ ጥፋት የክልሉ መንግስት ጊዜውን እና ወቅቱን በጠበቀ መልኩ አጥፊዎችን ተገቢውን ጥያቄ ጠይቆ ፍትሕን የማስፈን ህጋዊ እርምጃ ባለመውሰዱ ምክንያት አላባራ ያለ ተደጋጋሚ ጥቃቶች በሙስሊሙ ምዕመን ላይ እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል።
ከነዚህም ጥቃቶች መካከል (ምንም እንኳ የጥቃቱ ምልክቶች አሁንም ድረስ ባያቆሙም) ከሚያዚያ 18 እስከ 20/2014 ዓ.ኢ ባሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በጎንደር ሙስሊሞች ላይ በታሰበበት እና በተቀናጀ መልኩ የሽብር ጥቃት ደርሶባቸዋል። በጥቃቱም በርካታ ንፁሃኖች ተጨፍጭፈው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት ከባድና ቀላል የአካል ጉዳትን አስተናግደው፣ ከ12 በላይ መስጅዶች የሽብር ጥቃቱ ሰላባ ሆነው በርካታ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ንብረቶች ተዘርፈው የቀሩት ንብረቶችም እየተቃጠሉ እንዲወድሙ ተደርገዋል።
በጎንደር ሶስት ወራትን እያስቆጠረ ያለው ይህ ሙስሊሞችን ብቻ በዕምነታቸው ለይቶ የደረሰ የሽብር ጥቃት አሁንም ድረስ በፍትሕ እጦት ሳቢያ የከተማው ህዝበ ሙስሊም መሰደድና መፈናቀልን ዕጣ ፋንታው አድርጎ በመሸሸት ላይ ይገኛል።
ከዝርፊያ እና ከውድመት ተርፈው ያለስራ ተዘግተው የሰነበቱት የሙስሊም ድርጅት ባለቤቶች የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ እህት ወንድሞቻቸው ያለፉትን ሶስት ወራት በሚችሉት አቅም ካላቸው የተዳከመ የኢኮኖሚ ጥሪት ቀንሰው በመርዳት ሲያፅናኑ መሰንበታቸውን ታዝበናል።
በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት የከተማው አስተዳደር ለጠፋው የንፁሀን ነብስ፣ በሽብር ጥቃቱ አካላቸው ለጎደለው ምዕመኖች እንዲሁም ለወደሙት መስጅዶች፣ ለተዘረፉት እና ለተቃጠሉት የምዕመኖች ንብረት ካሳ መክፈልና ለተጎጅዎችም ፍትሕን አስፍኖ ወደነበሩበት መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የከተማ አስተዳደሩ መደበኛ ስራው መሆኑ ቢታወቅም ይህንን ማድረግ ተስኖት በእነኚህ ፅንፈኛ ቡድኖች ተጠልፎ አሁንም ድረስ በከተማው ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው በደል አላባራ ብሏል።
በሚያሳዝን መልኩ በከተማው አስተዳደር ፍትሕ እጦት ሳቢያ ተስፋ ቆርጠው ከተማዋን ለቀው ለመውጣት የማጣሪያ ገበያ ላይ ያሉትን ሙስሊም ነጋዴዎች አይዟችሁ ተብለው እንዳይሰደዱ ማድረግ ሽሽታቸውን ማስቆም ሲገባ ጭራሹን ጫና ፈጥሮ በማስገደድ የሽብር ጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ሙስሊሞች <<የካሳ ክፍያ መዋጮ>> በሚል አስገዳጅ ምክንያት በተደጋጋሚ ያለአቅማቸው ላልተገባ ብዝበዛ እየዳረጋቸው እንደሚገኝ የከተማው ሙስሊም ነጋዴ ማህበረሰብ ቅሬታቸውን አሳውቀዋል።
ለዚህም ማሳያው ከሰሞኑ የከተማው አስተዳደር ጉዳዩን በተመለከተ እየሄደባቸው ያለውን አካሄዶች አይቶ መገንዘብ እንደሚቻል አረጋግጠናል።
በመሆኑም ይህንን የከተማውን አስተዳደር የተዛባ የፍትሕ አካሄድ የሚመለከተው የበላይ አካል ተገንዝቦ ተገቢውን ህጋዊ እርማት በማድረግ ፍትሕን እንዲያሰፍን እናስታውሳለን!!
300 views17:23