2023-02-21 10:50:50
«ምንም ስህተት አልሰራንም ነገር ግን በሆነ መንገድ ተሸንፈናል»
――«――――――――――――――»――
የNOKIA ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሁሉም የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን ለብዙ አመታት የለፉበት ድርጅት በማይክሮሶፍት መጠቅለሉን ለማሳወቅ እና ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት አዳራሽ ውስጥ ተሰይመዋል። ከብዙ በሃዘን የታጀቡ ንግግሮች በኋላ ንግግራቸውን እንዲህ በማለት ቋጩ፦ «ምንም ስህተት አልሰራንም፤ ነገርግን በሆነ መንገድ ተሸንፈናል»
ኖኪያ የተከበረ ኩባንያ ነው። በንግድ ስራቸው ውስጥ ምንም ስህተት አላደረጉም። ሆኖም ግን ተፍካካሪያቸው በጣም ኃይለኛ ስለነበሩ ዓለም ጥሏቸው ሄደ።
ተምሮ የመስተካከል፤ ተስተካክሎ የመለወጥ እድል በማሳለፋቸው ትልቅ የመሆን የማደግ እድሉን ለሌሎች አሳልፈው ሰጥተዋል። ብዙ ገንዘብ የማፍራት ብሎም የማትረፍ እድል ብቻ ሳይሆን የመትረፍ እና በሕይወት የመቀጠል እድላቸውን አጥተዋል።
«በቶሎ ካልተቀየርክ፤ ከፉክክሩ ትወጣለህ» የታሪኩ መልእክት ነው። አዳዲስ ነገሮችን መማር አለመፈለግ ስህተት አይደለም። ነገር ግን ሃሳብህ እና አስተሳሰብህ ከጊዜን ጋር ካልናኘ ከውድድር አለም ትወገዳለህ። ከውድድር አለም መወገድ ብቻ ሳይሆን በሕይወት የመቆየት እድልህ የተመናመነ ይሆናል።
∴ ሲጠቃለል፦
① ትላንትና የነበርክበት የተጠቃሚነት ደረጃ ነገ በሚፈጠሩ የተለዩ ዝንባሌዎች ይተካሉ። ተፎካካሪዎችህ ማዕበሉን እስኪይዙና በትክክለኛው መንገድ እስኪያስኬዱት የመሸነፍ እና የመውደቅቅ አዝማሚያ ልታሳይ አትችልም። እነዚህ አዳዲስ ዝንባሌዎች እስኪፈጠሩ የሰራሃው ስህተት ፍንትው ብሎ አይታይህም።
② ራስህን ለመለወጥ እና ለማሻሻል ለራስህ ሁለተኛ እድል ስጥ። በሁኔታዎች ተገዶ መለወጥ እንደ መወገድ ይቆጠራል። ለመማር ብሎም ራስን ለማሻሻል አሻፈረኝ ያሉ፣ በእርግጠኝነት አንድ ቀን ራሳቸውን ከኢንዱስትሪው ውጪ ያያሉ። ውድ እና ከባድ በሆነ መንገድም ትምህርት ይወስዳሉ።
መልካም ቀን
@WERKAMAA
11 views@ñwăř, 07:50