Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ werkamaa — ወርቃማዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ werkamaa — ወርቃማዎች
የሰርጥ አድራሻ: @werkamaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 351

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2022-07-01 08:59:37 ​እንኳንም ተሳሳትክ!



በአንድ ወቅት አንዲት የሒሳብ መምህርት የሚከተለውን በሰሌዳ ላይ ጻፈች፦
9×1= 7
9×2= 18
9×3= 27
9×4= 36
9×5= 45
9×6= 54
9×7= 63
9×8= 72
9×9= 81
9×10= 90

ጽፋ እንደጨረሰችም ወደ ተማሪዎቿ ዞራ ስትመለከት ሁሉም እየሳቁባት ነው፣ የመጀመሪያውን እኩልታ (equation) ተሳስታለችና።

ይህን ጊዜ መምህርቷ እንዲህ አለች፦ "የመጀመሪያውን ስህተት የጻፍኩት በዐላማ ነው፤ ከነገሩ ጠቃሚ ትምህርትን እንድትወስዱ ስለፈለኩኝ። ይኸውም፥ በውጪ ያለው ዓለም እንዴት እንደሚቀበላችሁ ታውቁ ዘንድ ነው። 9 ጊዜ ትክክለኛ ነገር እንደጻፍኩ ማየት ትችላላችሁ ይሁንና አንዳችሁም ስለዛ አላበረታታችሁኝም፤ ነገር ግን ሁላችሁም ስለ ሠራሁት አንድ ስህተት ሳቃችሁብኝ፣ ነቀፋችሁኝም።

ትምህርቱም ይህ ነው፤

• ዓለሙ፥ ሚሊዮን መልካም ሥራን ብትሠሩ አያበረታታችሁም ግን አንድ የሠራችሁትን ስህተት ይዞ ይነቅፋችኋል። በዚህ ግን ተስፋ ልትቆርጡ አይገባም። ሁልጊዜም ቢሆን ከሳቅና ከነቀፋ በላይ ወጥታችሁ ቁሙ፣ ጽኑ፣ በርቱም!"

ልብ በል፤

• መሳሳትን ከፈራህ መሞከር አትችልም፤ መሳሳት ያንተ መጨረሻ አይደለም የማወቅ መነሻ እንጂ።

• ምናልባት የተማርከውን ትረሳ ይሆናል፣ የተሳሳትከውን ግን አትረሳም።

• ከብዙዎች የስንፍና ፍፁምነት ይልቅ ያንተ የመሥራት ስህተት እንደሚሻል አስብ።

• ከመሳሳትህ በላይ ሰው ምን ይለኛል? የሚለው ነገር ያስጨንቅህ ይሆናል፤ ሰው ግን እንዳንተው የሚሳሳት መሆኑን አትርሳ።

ኖረህ ስላልጨረስክ እንኳንም ተሳሳትክ!፤ ስህተትህ ላይ ከዘገየህ ብዙ ነገሮች ያልፉሃል፣ በቶሎ ከተማርክ ግን አዲስ ነገር ታውቃለህ፣ ትሠራለህ።

ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
t.me/Werkamaa
196 views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 08:57:43 Faith is taking the first step even when you can't see the whole staircase
145 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 19:09:07
This picture teaches us one important lesson. Today you are flying up the sky, tomorrow you will need someone on the ground to carry you. So be humble, love people and invest in people.

LESSONS: And remember no matter how big flying object you are something can carry you that can never fly, don't underestimate people below you, carry them above if you can but don’t push them down
@WERKAMAA
219 viewsedited  16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 10:24:04
የነብስ'ሽ ሽታ... የአካላት'ሽ ጠረን..የአይን'ሽ ማዕበል...የጨዋታ'ሽ ቅመም...የአነጋገር'ሽ ለዛ...የሳቅ'ሽ ስክነት ዉበት...የምግባር'ሽ ማማር ...የውበት'ሽ ሚስጥር...የሁለተና'ሽ ክምር.. የአይን አከፋፈት አከዳደን ቀመር'ሽ..የአካሄድ አረማመድ ስልት'ሽ..የቁጣ'ሽ ነበልባል..የልብ'ሽ ስፍት እንደ'ባህር እንደ'ምድር.....ሌት'ቀን ሚታወሰኝ እንዲህ ነው..ከሄድ'ሽ ቡኋላ ያዛነፍኩት ምኑን ከምን ነው...ከመሄድ'ሽ ጋ የወሰድሽው የቱን ነው...ሁሉን እዳልነበረ ሲሆን ሁሉ እንደነበረ የሚሆነው ከምኔው ቅፅበት ነው...መጥተ'ሽ ካረፍሽበት ያጠፋ'ሽ የምን ብልጭታ ነው... መ.ለ.የ.ት አልቻልኩም አለሜ!
@Werkamaa
236 views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 13:23:16 ... ....

አንተን ልክ እንደ መድሃኒት በሕመማቸው በችግራቸው ጊዜ ብቻ ሊጠቀሙብክ ወደ አንተ
የሚመጡ ከዛ በዃላ የማይመለሱ ብዙ አሉ

ቢሆንም አትዘን ውድ ነገር በውድ ቦታ ብቻ ነውና የሚገኘው::

  ይ ላ ሉን! ➢ @Werkamaa
... ...
212 views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:03:12 ሶስት ሰዎች በመንገድ ላይ ሲሄዱ አንድ ሰው መንገድ ዳር ላይ ሲቆፍር ተመለከቱና እያንዳንዳቸው ባዩት ነገር አስተያየታቸውን እንዲህ ሰጡ...

አንዱ እንዲህ በማለት ሀሳቡን ሰጠ:- "ሰው ገድሎ መቅበር ፈልጎ መሆን አለበት" አለ::

ሁለተኛው ሰው ደግሞ እንዲህ አለ:- "አይ አይሆንም አይደለም ገዳይ አይደለም ... ነገር ግን ሰውን በምንም ነገር የማያምን እና ገንዘቡን እዚህ የሚደብቅ ሰው ነው" አለ::

ሶስተኛው ተመለከታቸውና እንዲህ አላቸው፡-
"እኔ እንደምገምተው (እንደማስበው) ከሆነ ለውሃ ጉድጓድ እየቆፈረ ነው ጎበዝ ነው" አላቸው::

ስለሰው የምታስብበት መንገድ ለራስህ ባለህ አስተሳሰብ ልክ ነው::
ሁሉም ሰው ሰውን በአይኑ ያያል ጥሩው ሰውን ጥሩ አድርጎ ያያል መጥፎው ደግሞ በተቃራኒው ነው የሚያየው::
ስለዚህ፡ ለሰዎች መልካም ነገር እንዲያስቡልህ እንደምትመኘው ሁሉ መልካም አስብ።

ጥሩ እይታን (አመለካከትን) ይስጠን!
@WERKAMAA
244 views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 00:03:20 የምሽት ቅኔ
..
መሸ

ቀኑ
ኡኡታውን፣
ጫጫታውን፣
ኮሽታውን
ሽክፍ አርጎ
ክልፍልፉን
ጅልፍልፉን
ሁሉ ጠርጎ
ስለሼሸ
መሸ
ባለተራው
ባለ ጊዜው
ተገሰጠ
መንበሩ ላይ
ተቀመጠ
አንባቢውን
አፍቃሪውን
ባተሌውን
ሾተሌውን
ሚስጥረኛ
ደንበኛውን
ሊያስጋግረው
እያስሟሸ
ሊያስገብረው
እያስመሸ
መሸ
222 views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 12:51:47
<እንዲህ አትውደደኝ>>
<<እንደዛ አትበይኝ ካለ ፍቅርሽ እንዴት ኖራለሁ>>ምንም ፍርሃት አላስተዋልኩበትም ከፈገግታው የተደበቀ
<<ካለኔስ ? >>ለጥያቄ ፍራቻን አላውቅም ለራሴም ቢሆን መፍራቴ ለሱ ነው ያጣኝ ለት ምን እንደሚሆን ባሰብኩበት ቅፅበት አይኖቼ በዕምባ ይርሳሉ ልቤ ይታፈናል..እንደምንም ዋጥ ለማድረግ እሞክራለሁ።
<<አለሜ ነገን ፈርቼ ከዛሬ ፍቅርሽ መሸሽ እኮ መሞት ነው ለኔ>>ከአይኖቼ እንጥብጣቢ ስጠብቅ መስመር ሰርተው መውረድ ጀመሩ።
<<ታውቃለህ...>>ምን ልለው እንደፈለኩ በቅጡ ባይገባኝም ማውራት ግን እፈልጋለሁ።
<<እንደማፈቅርሽ አውቃለሁ...አለሜ ካንቺ ጋ ደማቅ እንደሆነች.. የምትወደድ..የማትሰለች..እነደሆነች..መኖር ካንቺ ጋ እንደሚያጓጓ አውቃለሁ...በይ ንገሪኝ አለሜ ማወቄ ላይ ልጨምር ህህ ከፍቅርሽ ጋ..!>> ፈገግታው ለብቻው ሳቅ ነው ያለመልመኛል..(አይኖቹ በየቅፅበታት ስለሚገሉኝ)
<<የኔ ቀውስ የምፈልገው አንተ ቀድመኸኝ እንድትሞት ነው ምርጫ ቢሰጠኝ እዝች ምድር ላይ ጥዬህ መሄድ አልፈቅድም፤ሸኝቼህ መች እንደምከተልህ እየቆጠርኩ መሞቱ ይቀለኛል፤ዕድል ቢቀናኝ ደግሞ ነብሶቻችን እኩል ቢያሸልቡ....ዝም አልኩ<<ያንቺ ነብስ ከሄደች ቡኋላ እንዴት ህያው እሆናለሁ..የኔ አለም የኔስ አለመኖር አንቺን ገድሎ ከመሄድ አይተናነስብኝም እኮ አለመኖሬ ከሚገልሽ አለመኖርሽ ይግደለኝ... >>አይኖቹ ጉም ጋረዳቸው።
<<በቃ ዝም በል! አልችልም እንዲህ አትውደደኝ...>>ፈገግ አለ <<አፈቅርሻለሁ>> ከተደባለቀው ሳቅና እምባ ጋ!
@Werkamaa
225 viewsedited  09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 13:49:22 ደሞ ስተመጣ ሰዐት አታውቅ፤ዕለት አትመርጥ፤ሁነቴን ሳታጣራ...ድንገት ፊቴ ድቅን ትልና ሁሉመናዬን አዘበራርቀህ ለቀናት ትከርማለህ...።


@Werkamaa
203 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 10:28:43 "…የምንኖርባት ጊዜ ከዘለዓለማዊ ህይወት ላይ ተቀንሳ በቅንፍ ውስጥ የተቀመጠች በጣም ትንሽ ጊዜ ናት። በዚህች ጊዜ ውስጥ በህይወታችን ስንኖር መረዳዳትን፤ መቀራረብን እና መተባበርን መልመድ አለብን።"

@WERKAMAA
373 views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ