Get Mystery Box with random crypto!

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tsegaye_gebremedihen — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tsegaye_gebremedihen — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ
የሰርጥ አድራሻ: @tsegaye_gebremedihen
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.94K
የሰርጥ መግለጫ

ጥበብ ይናፍቀኛል፤ ተቻችሎ የሚኖር ህዝብ ያስቀናኛል፤ ድንቁርና ያስፈራኛል።
©ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
❤️JOIN (ተቀላቀሉን)

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-08 11:53:13 #ኑሮ_እና_ጣእሙ

ሙያዬን ታውቃለህ ፤ ማጀቴን ታያለህ ፤
"እንጀራሽ እንክርዳድ ፤ ገበታሽ ጣዕም-አልባ!"
ለምን ትለኛለህ ?

በል ዝም-ብለህ ብላ!!
ቸርቻሪ መንግስታት ፤
ሰነፍ ገበሬዎች ፤
በዝባዥ ነጋዴዎች ፤ በበዙበት ዓለም ፤
ጠንካራ ጥርስ እንጂ ፤ ቀማሽ ምላስ የለም !!

በረከት በላይነህ
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
7.9K viewsDave88, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-23 20:11:45 #ኢትዮጵያ

ከዝናው:ማማ:ላይ
ከአምባው:ራስ፡በላይ፤
ለእይታ:ማይጋርድ
ጎልቶ:ሚታይ:ቅላይ፤
ከአርያም:ዋልታ
ግብግቡን:አድፍጦ፤
በቃልኪዳን:እስር
ሰንደቅሽ:ይታያል:ከዳመናው:ጎልቶ፤

እናም.........

ወይ:ቅናት:አይሉት
ጠላትሽ:በርክቶ፤
እናልማሽ:በሚለው
የሚያጠፋሽ:በዝቶ፤
ከል:ይጥልብሻል፤
ማጥፋት:ባንችሉ:እንኳን:
ቢያንስ:ይጋርድሻል።


ሚኪያስ እንዳለው
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
8.0K viewsDave88, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 09:34:38 "ለቅርብ እሩቆቼ...."

ዙሪያዬን ስቃኘው ፤ ሰው ሞልቶ ተንጣልዋል
ይሄንን አይቼ ፤ ባለ ወገን ነኝ ስል
አይኖቼ እንባ ሞልተው ፤ ሲያንገላታኝ ችግር
ስጮህ የደረሰ ፤ ማነው ካአምላክ በቀር
ለካስ የከበበኝ
የኔ የመሰለኝ
እያየ ማያየኝ
አድምጦ ያልሰማኝ
ግን.መስሎ .. ደርሶ አዛኝ
አዝኖ አንገት ነቅናቂ
ዞር ብሎ ሳቂ
አካሉን አቅርቦኝ
ስሜቱን አራቂ
ብዙ፡ የቅርብ፡ እሩቅ
አለኝ...፡ የከበበኝ
በደስታዬ ፡ ማይሰቅ
በጭንቄ ፡ሚቦርቅ
ከኔው ፡ በሃሪ፡ ነው?
ወይስ ሰው ፡ እንዲ ነው ??
ቆይ
ቆይ...
ቆይ... ቆይ...
ለሰው ፡ መድሃኒቱ
ሰው ነው በምድሪቱ
ቢሉኝ ፡በተረቱ...
ያለኝን፡ እንኩ ፡እያልኩ
ከሰው ፡ብዙ ፡ጠበኩ
ተከብቤ ፡ እያየሁ
ሰው ፡በሚሉት ፡ከንቱ...
ያለ ሰው ፡ አይደምቅም
እያልኩ ፡ እደዋዛ
ነባር ፡ተረት ፡ስለቅም
ስሜቴን፡ ሳዋዛ
አሁኔ ፡ ተንዛዛ
***
ደግሞ፡ በሩቆቹ
የለኝም፡ ባልኳቸው ፡ ሩቅ ፡ ተመልካቾቹ
ጨለማው ፡ ተስፋዬን
አይን፡ ጆሮ፡ ሰተው ፤ ደግመው ፡ያበሩታል
የዛለ ፡ጉልበቴን
ሃሳብ፡ ጊዜ ፡ ሰተው፤ ብርታት ሆነውታል
ስቀው፡ አስቀውኝ
ፊቴን ፡ያፈኩታል።
ይህንን ፡ሳይ ፡ ደግሞ
ደሞ ፡ እደማለሁ....!!!!
ለካ :ሰው: እላለሁ
ባ'ልጠበኩት : መንገድ
ሞልቶ ይፈስና
የሰው ጥግ ፡አያለሁ
ሰው፡ አለ ፡እላለሁ
በአርያህ፡ የጸና ።
ጠማማ ውን ልቤን ፡ ደሞ እመለስና
ያለኝን :ሰጣለሁ
መልሼ እደገና ፡ ከሰው ጠብቃለሁ
ሰው እዲሁም ነውና!!

ሔለን አበራ
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
8.3K viewsDave88, 06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-16 23:26:12 #ልሂድ ካልሽኝማ

መከዳት አይገርምም
መረሳት ሲገጥም፤
በተስፋ ማሰብ ነው መጪው እንደሚጥም፤
ይሁና
ምን ልንል ከተደራረሰ፤
ይቅርታውም ፀፀት አንቺን ካልመለሰ፤
ልቤም
ባለበት ይሄዳል እያረሰረሰ፤
ሚሽር ቢጠፋ እንኳን
ከሰው ከተገኘ ሚገጥም የቀደሰ።

ሚኪያስ እንዳለው
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
6.7K viewsDave88, 20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-14 23:48:31 #አንቺ እና ግጥም

ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ዳጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ
ጠልቼ አልጠላችሁ!


ሚካኤል አስጨናቂ
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
6.7K viewsDave88, 20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 12:28:21 ተፈሪ አለሙ
አቅራብ አብረሃም ተክሉ

@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
5.8K viewsDave88, edited  09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 12:22:39 ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ pinned «@Dave88_Photography @Dave88_Photography @Dave88_Photography Join my photography channel https://t.me/joinchat/RuhCcg_NfjZ9xTDo»
09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 19:16:02 @Dave88_Photography
@Dave88_Photography
@Dave88_Photography

Join my photography channel
https://t.me/joinchat/RuhCcg_NfjZ9xTDo
6.0K viewsDave88, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-07 17:45:39 ትርጉም ፍለጋ
.
.
ከአራት ጸደይ፣ በፊት በማሰሮ ተክላ፤
ደጅ ያስቀመጠችው፣ ጽጌረዳ አበባ፤
እንቡጥ እንደጣለ፤
በረንዳው ላይ አለ፡፡

በእፍኙ የቋጠረው፤
የተንዘላዘለ
የተጠቀለለ
ትርጉም የቸገረው፤
አንድ ንግርት አለ፡፡

በድሉ ዋቅጅራ
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
6.3K viewsDave88, 14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-11 17:29:34 ግጥም**

የቃላት ድርደራ የፊደላት ውበት ፤
የሆሄያት ቀለም የቀለም አንድነት ፤
በትንሽ ስንኞች ባጭር መስመራት ፤
በአንድ በሁለት አልያም በሶስት ፤
በትንሽ አንጓ በጥቂት ፊደላት ፤
ግጥም የምትለው እጅግ ብዙ አላት ።

እናም ይቺ ግጥም ልብን ነቅናቂ ፤
የልብን ሀሳብም ናት አንጸባራቂ ።
ልብን የሚያሸፍት በደስታ ማዕበል ፤
እኔም ልሄድ አሰብኩ ከጥበቦች ዐለም ።

ጥበብ ተቀበይኝ እባክሽ ብያለሁ ፤
ሀሳቤን ለማቅለል አንችን መርጫለሁ ።

ሚካኤል ታምሬ
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
7.8K viewsDave88, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ