Get Mystery Box with random crypto!

'ለቅርብ እሩቆቼ....' ዙሪያዬን ስቃኘው ፤ ሰው ሞልቶ ተንጣልዋል ይሄንን አይቼ ፤ ባለ ወገን | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ

"ለቅርብ እሩቆቼ...."

ዙሪያዬን ስቃኘው ፤ ሰው ሞልቶ ተንጣልዋል
ይሄንን አይቼ ፤ ባለ ወገን ነኝ ስል
አይኖቼ እንባ ሞልተው ፤ ሲያንገላታኝ ችግር
ስጮህ የደረሰ ፤ ማነው ካአምላክ በቀር
ለካስ የከበበኝ
የኔ የመሰለኝ
እያየ ማያየኝ
አድምጦ ያልሰማኝ
ግን.መስሎ .. ደርሶ አዛኝ
አዝኖ አንገት ነቅናቂ
ዞር ብሎ ሳቂ
አካሉን አቅርቦኝ
ስሜቱን አራቂ
ብዙ፡ የቅርብ፡ እሩቅ
አለኝ...፡ የከበበኝ
በደስታዬ ፡ ማይሰቅ
በጭንቄ ፡ሚቦርቅ
ከኔው ፡ በሃሪ፡ ነው?
ወይስ ሰው ፡ እንዲ ነው ??
ቆይ
ቆይ...
ቆይ... ቆይ...
ለሰው ፡ መድሃኒቱ
ሰው ነው በምድሪቱ
ቢሉኝ ፡በተረቱ...
ያለኝን፡ እንኩ ፡እያልኩ
ከሰው ፡ብዙ ፡ጠበኩ
ተከብቤ ፡ እያየሁ
ሰው ፡በሚሉት ፡ከንቱ...
ያለ ሰው ፡ አይደምቅም
እያልኩ ፡ እደዋዛ
ነባር ፡ተረት ፡ስለቅም
ስሜቴን፡ ሳዋዛ
አሁኔ ፡ ተንዛዛ
***
ደግሞ፡ በሩቆቹ
የለኝም፡ ባልኳቸው ፡ ሩቅ ፡ ተመልካቾቹ
ጨለማው ፡ ተስፋዬን
አይን፡ ጆሮ፡ ሰተው ፤ ደግመው ፡ያበሩታል
የዛለ ፡ጉልበቴን
ሃሳብ፡ ጊዜ ፡ ሰተው፤ ብርታት ሆነውታል
ስቀው፡ አስቀውኝ
ፊቴን ፡ያፈኩታል።
ይህንን ፡ሳይ ፡ ደግሞ
ደሞ ፡ እደማለሁ....!!!!
ለካ :ሰው: እላለሁ
ባ'ልጠበኩት : መንገድ
ሞልቶ ይፈስና
የሰው ጥግ ፡አያለሁ
ሰው፡ አለ ፡እላለሁ
በአርያህ፡ የጸና ።
ጠማማ ውን ልቤን ፡ ደሞ እመለስና
ያለኝን :ሰጣለሁ
መልሼ እደገና ፡ ከሰው ጠብቃለሁ
ሰው እዲሁም ነውና!!

ሔለን አበራ
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen