Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም** የቃላት ድርደራ የፊደላት ውበት ፤ የሆሄያት ቀለም የቀለም አንድነት ፤ በትንሽ ስንኞች | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ

ግጥም**

የቃላት ድርደራ የፊደላት ውበት ፤
የሆሄያት ቀለም የቀለም አንድነት ፤
በትንሽ ስንኞች ባጭር መስመራት ፤
በአንድ በሁለት አልያም በሶስት ፤
በትንሽ አንጓ በጥቂት ፊደላት ፤
ግጥም የምትለው እጅግ ብዙ አላት ።

እናም ይቺ ግጥም ልብን ነቅናቂ ፤
የልብን ሀሳብም ናት አንጸባራቂ ።
ልብን የሚያሸፍት በደስታ ማዕበል ፤
እኔም ልሄድ አሰብኩ ከጥበቦች ዐለም ።

ጥበብ ተቀበይኝ እባክሽ ብያለሁ ፤
ሀሳቤን ለማቅለል አንችን መርጫለሁ ።

ሚካኤል ታምሬ
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen