2023-02-10 21:38:37
ለመስቀል ይሰገዳልን?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ *"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ስገዱ ፡፡ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
በቁርኣን "ሡጁድ” سُّجُود የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለት “ሰገደ” ወይም “ታዘዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ስግደት” ወይም “መታዘዝ” ማለት ነው፤ ሡጁድ ደግሞ በሁለት ይከፈላል፦ አንዱ “ሡጁዱል ዒባዳ” سُّجُود العبادة ማለትም “የአምልኮ ስግደት” ሲሆን ሌላው “ሡጁዱ አተሒያ” سُّجُود التحيه ማለትም “የአክብሮት ስግደት” ነው፤ ነገር ግን ይህ አክብሮት አቅጣጫውን ቀይሮ አምልኮ እየሆነ ስላለ ከሰላምታ ውጪ በሱጁድ ለፍጡራን ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ ቁርአን ሲወርድ ቆሟል፤ የአክብሮት ስግደት ከአምልኮ ስግደት ጋር እንዳይደባለቅ የተከለከለው በነቢያችን”ﷺ” ጊዜ ነው፤ አላህም፦ "ሁሉን ለፈጠረው ለእርሱ እንጂ ለሌላ አትስገዱ" ብሎናል፤ ከአላህ ሌላ የሚገዙት ግዑዛን ነገር የገሀነም ማገዶዎች ናቸው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ *"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ስገዱ ፡፡ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
21፥8 እናንተ *"ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውም የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ*፡፡ እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ። إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ
ማገዶዎች በሚለው ቃላት “ማ” َمَا የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ-ስም አቅል የሌላቸውን ጣዖታት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ አቅል ያላቸውን ማንነቶች “መን” مَّن የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም የሚጠቀመው፤ ግን እዚህ አንቀፅ ላይ “ማ” የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም መጠቀሙ አቅል የሌላቸውን ጣዖታት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ “ጣጉት” لطَّاغُوتِ ማለትም "ጣዖት" ይባላል።
ወደ ባይብል ስንመጣ “ስግደት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሻቻህ” שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ፕሮስካኒኦ” προσκυνέω ይባላል፤ ይህም ለተለያየ ምንነት ሆነ ማንነት በኒያ”intention” የሚቀርብ አምልኮን”Adoration” ወይም አክብሮትን”prostration” ነው ለማመልከት በባይብል ተጠቅሞበታል፤ የአምልኮት ስግደት በባህርይ የአንድ አምላክ ሃቅና ገንዘብ ሲሆን የአክብሮት ስግደት ደግሞ በፀጋ ለህያዋን ማንነት ማክበርን ያመለክታል፤ ግን ለግዑዛን ነገሮች አምልኮም ይሁን ስግደት ተከልክሏል፤ በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት “ምስል”፣ “ቅርፅ”፣ “ጣዖት” ማለት ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ኤዶሎን” εἴδωλον ነው፤ ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው። የሙሴ አምላክ ለሙሴ “”ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”” ብሎ ተናግሯል፤ እንደውም ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ ይላል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ *”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”*፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 *”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ*”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።
መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው፤ ይህ ግዑዝ ነገር በአበይት ክርስቲያኖች ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ ደግሞ የዘወትር ፀሎት ላይ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”
ትርጉም፦
“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው”
ግዕዙ፦
“ስብሐት “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረቱ ይዘከረነ”
ትርጉም፦
” “ለ”ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባዋል”
“ለ”ተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ እየተባለ ለምንድን ነው ለግዑዝ ነገር የፀጋ ስግደት የሚሰገድለት? የሚሰማበት ዐቅል የት አለውና ነው ምስጋናስ የሚቅብለት? ይህንን ስንላቸው ለመስቀል ስግደት እንደሚገባው ይህ ጥቅስ ያሳያል ይላሉ፦
መዝሙር 132፥7 ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ *እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን*።
እዚህ አንቀጽ ላይ "መስቀል" የሚለው ቃል ይቅርና ስለ መስቀል እሳቤው እንኳን የለም። "እግሮቹ የቆሙበት በመስቀል ላይ ነው" የሚል ተልካሻ ምክንያት በማቅረብ ይዳዳሉ። ቅሉ ግን "እግሮቹ "በ"ሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን" አለ እንጂ "እግሮቹ "ለ"ሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን" አላለም፤ "ለ" እና "በ" የሚሉ በይዘትና በአይነት ሁለት መስተዋድዶች ናቸው። ሲቀጥል "በ"ሚቆሙበት "ስፍራ" አለ እንጂ "በ"ሚቆሙበት "መስቀል" መቼ አለ? አውዱ ላይ "ስፍራ" የሚለው ቦታን እንደሆነ ይናገራል፦
መዝሙር 132፥5 *ለእግዚአብሔር "ስፍራ"፥ ለያዕቆብ አምላክ "ማደሪያ" እስካገኝ ድረስ ብሎ*።
ምን ትፈልጋለህ? "ስፍራ" የተባለው መስቀል ሳይሆን "የቅድስናው ስፍራ" ነው፤ "በ"ዚህ ስፍራ "ለ"እግዚአብሔር ይሰገዳል ይላል፦
መዝሙር 96፥9 *"በ"ቅድስናው ስፍራ "ለ"እግዚአብሔር ስገዱ"*፤
አሁንም "ለ" እና "በ" የሚሉ ሁለት መስተዋድዶች ለዩ፤ "በ" ቦታን "ለ" ምነነትን ያመለክታል፤ በቅድስና ስፍራ ለእግዚአብሔር ይሰገዳል እንጂ ለስፍራ አይሰገድም። የእግሮቹ መቆሚያ ማለትም የእግሮቹ መረገጫ የቅድስናው ስፍራ እንጂ መስቀሉ አይደለም፦
ሕዝቅኤል 43፥7 እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት *የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው*።
ይህንን ጉድ እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ጾታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ። ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦
231 views18:38