Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopianss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.39K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-28 10:27:06
ፍሪላንስ ኢትዮጵያ በአዲሱ አመት እጅግ በተሻሻለ መልኩ የስራ ፈላጊ እና ድርጅቶች  ቀጥታ የመገናኛ ፕላትፎርም ለመሆን የሚያስችለውን አዲስ የቴሌግራም ቦት ይዞ መጥቷል፣ ከቅጥር ጋር ለተያያዘ ፍላጎታችሁ ሁሉ እንድትጠቀሙበትም ይጋብዛችኋል !                           
አዲሱ አመት በጋራ በመስራት አፍሪ የምንሆንበት እንዲሆን እንመኛለን!
469 viewsMintesinot Hemecha, 07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 20:38:18
#በወለጋ እያለቁ ለሚገኙ አማሮች በጋራ እንዘን!#ድምፅ እንሆን!

መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም #በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ወለጋ በኦነግ የተገደሉ አማሮች ቁጥር 200 ይደርሳል ሲሉ የአይን እማኞች ገለፁ።

እስካሁን ድረስ ከ100 በላይ አስክሬን ሰብስበው እንደቀበሩ ገልፀዋል።አብዛኛውን አስክሬን ግን እስካሁን ድረስ ከለላ የሚሰጥ ታጣቂ ኃይል በመጥፋቱ መሰብሰብ እና መቅበር አልተቻለም ብለዋል።ከስፍራው መረጃ ያደረሱን አካላት።

በወለጋ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ተልዕኮውን የጨረሰው የኦነግ ሰራዊት ወደ ሃሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ በስፋት እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ እዛ አካባቢ የሚኖሩ ንፁሃን አሁንም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።ተብሏል።

ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ባለፈው አመት ከኦነግ ጭፍጨፋ ተርፈው የተጠለሉ ከ50ሺህ በላይ አማሮች ይገኛሉ።

እነዚህ አማሮች የማበሉትም ሆነ የሚለብሱት ምንም ነገር አለመኖሩን በቅርቡ ገልፀው ነበረ።በተጨማሪም የቡሬ ወለጋ መንገድ በመዘጋቱ ወዴትም መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን አሳውቀዋል።

በወለጋ የአማሮች ጭፍጨፋ በየጊዜው ሆን ተብሎ እንዲለመድ በመደረጉ ሚዲያዎችም ይሁን ማህበረሰብ አንቂዎች ትኩረት እየሰጡት እንዳለሆነ ተገልጿል።ይህ ደግሞ ሀዘኑን የበለጠ ልብ ሰባሪ አድርጎታል ተብሏል።

በግፍ ለተጨፈጨፉ አማሮች ንፍስ ይማር!!

ወግደረስ ጤናው


#share #ሼር
@tikvahethiopianss
917 viewsMintesinot Hemecha, edited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 20:38:18
“ፊደል ተሳስተሃል” ብሎ ተማሪውን የገደለው መምህር

በሀገረ ሕንድ “ፊደል (ስፔሊንግ) ተሳስተሃል” በሚል ምክንያት መምህር ተማሪውን መግደሉ ተሰማ፡፡

የሕንድ ፖሊስ÷ “ሶሻል (social) የሚለውን ቃል ፊደላት በትክክል አልፃፍክም” በሚል ታዳጊ ተማሪውን በመደብደብ ገድሏል የተባለውን መምህር በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

የ15 ዓመቱ ታዳጊ ኒኪል ዶህሪ በዚህ ወር መጀመሪያ ፈተና ላይ “social” የሚለውን ቃል ሲጽፍ ፊደላትን በመሳሳቱ÷ ራሱን ስቶ እስከሚወድቅ ድረስ በአስተማሪው ድብደባ እንደተፈጸመበት የሟች አባት ለፖሊስ ተናግረዋል፡፡

ታዳጊው በመምህሩ በደረሰበት ድብደባ በሰሜናዊ ዑታር ፕራዴሽ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ላይ እያለ ሕይወቱ ማለፉ ተዘግቧል፡፡

ይህን ተከትሎም ተከሳሹ ከአካባቢው መሰወሩን ፖሊስ ገልጿል ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል፡፡

የሕንድ ፖሊስ እንደገለጸው ተጠርጣሪው ለጊዜ ከአካባቢው ቢሰወርም በቅርቡ በቁጥጥር መዋሉ እንደማይቀር ገልጿል፡፡

ክስተቱ በሀገሪቱ ተቃውሞ ብሎም ሁከት እና ብጥብጥ ማስነሳቱ ነው የተጠቆመው፡፡(FBC)

@tikvahethiopianss
806 viewsMintesinot Hemecha, edited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 20:38:18
" አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል " - ፖሊስ

ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ከሆነ ፤ ድምፃዊው ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወደ ሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ለሕክምና መሄዱና ሕክምና ማድረጉን ከቆይታ በኋላም ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ማዲንጎ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።

የድምፃዊው ወዳጆች በበኩላቸው ፤ ማዲንጎ ህመም ተሰምቶት እራሱ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ህክምና ስፍራ መሄዱን ከዛ በኃላ ህይወቱ እንዳለፈ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopianss
747 viewsMintesinot Hemecha, edited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 20:38:17
#ለማምለጥ_ሲሞክር_ተቃጠለ

በነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ጨጨሆ መናፈሻ ከወደ ገረገራ ተነስቶ የኮንትሮባንድ እቃ ጭኖ ነፋስ መውጫ ከተማ ለመግባት በመገስገስ ላይ የነበረ ታርጋው 20682 የሆነ መኪና የኬላ  ፍተሻ መኖሩን  ሲያውቅ ወደመጣበት በመዞር ለማምለጥ ሲሞክር ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል።

@tikvahethiopianss
747 viewsMintesinot Hemecha, edited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 18:25:20
ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ?

- ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 ወሩ ወላጆቹ ደብረ ታቦር መግባታቸውን ተከትሎ በደ/ታቦር ነው ያደገው።

- ማዲንጎ አፈወርቅ ያደገው በጦር ቤት ውስጥ ነው፤ እናት እና አባቱ "ተገኔ" /የኔ ጠበቃ/ ነበር የሚሉት፤ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ተገኔ" ነው። ማዲንጎ የሚለውን ስም ያገኘው በወታደር ቤት ውስጥ እየሰራ እያለ ነው፤ ከዛ በኃላ መጠሪያው ሆኖ ቀጥሏል።

- በልጅነቱ የሙዚቃ ፍቅር ያደረገበት ማዲንጎ ከደብረ ታቦር ወደ አዘዞ በተመለሰበት ወቅት በ7ኛ ክፍለ ጦር ካምፕ ውስጥ በ603ኛ ኮር ውስጥ ያለ የሙዚቃ ቡድን ልምምድ ሲያደርግ በመግባት ዘፈን እንደሚችል በመግለፅ እድል እንዲሰጠው ይጠይቃል፤በኃላም እድል ተሰጥቶ የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃ ከተጫወተ በኃላ አድናቆት በማግኘቱ ተቀባይነት አግኝቶ በዛው ሊቀጥል ችሏል።

- ማዲንጎ ከጦሩ ከወጣ በኃላ በ1982 ዓ/ም አካባቢ ገና በ12 ዓመቱ በባህር ዳር የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አንድም ድምፃዊ የመሆን ህልሙን መስመር ያስያዘበት በሌላ በኩል ገቢ በማግኘት እራሱንና ቤተሰቦቹን ማገዝ የቻለበትን ሁኔታ መፍጠር ችሏል።

- ማዲንጎ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኃላ በተለያዩ የሙዚቃ ክበቦች የተለያዩ አንጋፋ ድምፃዊያንን ስራዎች ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን በኃላም የራሱን ስራዎች (ነጠላና የአልበም ስራዎች) ለአድናቂዎቹ አቅርቧል።

- ማዲንጎን በስራዎቹ የሚያውቁት ወዳጆቹ ዜማ በመያዝ ችሎታ፣ ሙዚቃን አሳምሮ በመጫወትና የአድናቂዎቹን ቀልብ በመሳብ የተካነ በማህበራዊ ህይወቱም ተግባቢ፣ ቅንና ተጫዋች እንደሆነ ይመሰክሩለታል።

(ከጨዋታ እንግዳ ፕሮግራም/ከቅርብ ወዳጆቹ የተገኘ መረጃ)

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

@tikvahethiopianss
930 viewsMintesinot Hemecha, edited  15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 11:55:28
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ሥጋቶች በመኖራቸው በታጠቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ተጨማሪ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰቡን ይታወሳል።

ኢሰመኮ በአካባቢው ሲቪል ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች አሁንም ተሰፋፍተው መቀጠላቸው ገልጾ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አስገንዝቧል።

በዞኑ በአሙሩ፣ በሆሮ ቡልቅ እና በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ከነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሽኔ)፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎች እና ግለሰቦች በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች የተገደሉ መሆኑ ታወቋል ሲል ኢስመኮ ገልጿል።

እንዲሁም የግል ንበረት እና የቁም ከብቶች መዘረፋቸውን ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ያለበቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ኮሚሽኑ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአካባቢው የፍትሕና የአስተዳደር አካላት እንዲሁም በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ድርጅቶች ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች እና ማስረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ " የክልሉ አና የፌዴራል መንግሥታት በአካባቢው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚፈጸመው ጥቃቶችን ለመከላከል በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃ ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል" ሲሉ በድጋሚ አሳስበዋል።

@tikvahethiopianss
157 viewsMintesinot Hemecha, edited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 11:11:13
#DrAlQaradawi

የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን መስራችና ፌዴሬሽኑን ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት እውቁ የእስልምና ምሁር ግብፃዊ ዶክተር ሼክ ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።

ህልፈታቸውን ልጃቸው አብዱል ራህማን ዩሱፍ አል ቃራዳዊ አረጋግጠዋል።

ዶ/ር አልቃራዳዊ ህይወታቸው ያለፈው ኳታር፤ ዶሃ ውስጥ ነው።

እኤአ 2004 የተቋቋመውን (እሳቸው መስራች ነበሩ) ዓለም አቀፉ የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን ከተቋቋመበተ ጊዜ አንስቶ ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል።

ዶ/ር አልቃራዳዊ ከሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን የኳታር ዜግነት ተሰጥቷቸው ህይወታቸው እስክታለፍ ድረስ ኑሯቸውን በኳታር፣ዶሃ አድርገው ነበር።

አልቃራዳዊ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ወቅት በግብፅ በ1926 ነበር የተወለዱት።

ገና በለጋ እድሜያቸው እስላማዊ ትምህርትን መከታተል የጀመሩት አልቃራዳዊ በፀረ ቅኝ አገዛዛ ላይ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። በ1950 ዎቹ ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴና ከሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ጋር በተገናኘ ብዙ ጊዜ ለእስር ተዳርገው ነበር።

ከ120 በላይ መፅሀፍትን ያሳተሙት ዶ/ር አል ቃራዳዊ ለእስልምና ባበረከቱት አስተዋፆ 8 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን መሸለም እንደቻሉ ተገልጿል።

ዶ/ር አል ቃራዳዊ በክፈለ ዘመኑ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የእስልምና ሊቃውንት አንዱ እንደነበሩ ተዘግቧል።

በህይወት በነበሩበት ወቅት በተለያዩ ሚዲያዎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አመለካከታቸውን ሲያጋሩ የነበረ ሲሆን በሚያነሷቸው ሀሳቦች የሚደግፏቸው እንዳሉ ሁሉ ሀሳባቸውን የሚቃወሙም ነበሩ።

የዶ/ር አልቃራዳዊን ህልፈት ተከትሎ ፤ የተርክዬ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን  ለልጃቸው አብዱል ራህማን በመደወል የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው አፅናንተዋል።

@tikvahethiopianss
224 viewsMintesinot Hemecha, edited  08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 22:39:45
ቅዱስ ፓትርያርኩ ምን አሉ ?

" አለመግባባትን በዕርቅ ዘግቶ በፍቅርና በሰላም ከመኖር የተሻለ ሌላ አማራጭ የለም። " ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ገለጹ፡፡

ቅዱስነታቸው የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በተከበረበት ወቅት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት " የምናከናውነው ተግባር በሙሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድና የመስቀሉን ምሥጢር የጠበቀ ሊሆን ይገባል " ብለዋል።

ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ፍጥረታት በሙሉ እርስ በእርስ ሲጣሉና ሲተረማመሱ ማየት ቀዋሚ ትዕይንት ሆኖ እንደሚገኝ  የገለጹት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳ ችግሩ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ሰፍኖ ቢገኝም መፍትሔ የሌለው ችግር ግን አይደለም  ብለዋል።

" በየጊዜው በተግባር የተፈተነ ጠንካራና የማያወላውል መፍትሔው ይቅርታና ዕርቅ ነው " ያሉት ቅዱስ ፓትርፓርኩ " የሰው ልጅ አለመግባባትን በዕርቅ ዘግቶ ሰላምንና አንድነትን መሥርቶ በመከባበርና በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና በመተጋገዝ፣ በመረዳዳትና በመቻቻል፣ በፍቅርና በሰላም ከመኖር የተሻለ ሌላ አማራጭ የለውም ብለዋል። "

ይህም እውን ሊሆን የሚችለው፥ ለወንድሜና ለእኅቴ የሚል ቅን ሀሳብና  ለሁላችንም የሚል የጋራ አስተሳሰብ በሰዎች ልቡና የበላይነት ሲያገኝ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ " እግዚአብሔር ግጭቱን አስወግዶ ሰላሙን ፍቅሩን፣ አንድነቱንና ስምምነቱን እንዲያመጣልን፤ እኛም የዕርቅና የይቅርታ ሰዎች ሆነን እንገኝ ዘንድ በርትተን እንፀልይ " ሲሉ አባታዊና መንፈሳዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ telegra.ph/EOTC-09-26

@tikvahethiopianss
611 viewsMintesinot Hemecha, edited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 22:39:15
" በዓሉ በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል "

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ፣ ትውፊቱንና እሴቱን ጠብቆ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቋል።

ከተማ አስተዳደሩ ለአዲስ አበባ ህዝብ ፣ ለእምነት አባቶች ፣ ምእመናን ፣ ወጣቶች፣ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ ለከተማው የሰላም ሰራዊት አባላት እና የደንብ ማስከበር አገልግሎት ምስጋና አቅርቧል።

Video : Hena (Tikvah Family)

@tikvahethiopianss
531 viewsMintesinot Hemecha, edited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ