Get Mystery Box with random crypto!

#በወለጋ እያለቁ ለሚገኙ አማሮች በጋራ እንዘን!#ድምፅ እንሆን! መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም | TIKVAH ETHIOPIA

#በወለጋ እያለቁ ለሚገኙ አማሮች በጋራ እንዘን!#ድምፅ እንሆን!

መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም #በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ወለጋ በኦነግ የተገደሉ አማሮች ቁጥር 200 ይደርሳል ሲሉ የአይን እማኞች ገለፁ።

እስካሁን ድረስ ከ100 በላይ አስክሬን ሰብስበው እንደቀበሩ ገልፀዋል።አብዛኛውን አስክሬን ግን እስካሁን ድረስ ከለላ የሚሰጥ ታጣቂ ኃይል በመጥፋቱ መሰብሰብ እና መቅበር አልተቻለም ብለዋል።ከስፍራው መረጃ ያደረሱን አካላት።

በወለጋ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ተልዕኮውን የጨረሰው የኦነግ ሰራዊት ወደ ሃሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ በስፋት እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ እዛ አካባቢ የሚኖሩ ንፁሃን አሁንም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።ተብሏል።

ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ባለፈው አመት ከኦነግ ጭፍጨፋ ተርፈው የተጠለሉ ከ50ሺህ በላይ አማሮች ይገኛሉ።

እነዚህ አማሮች የማበሉትም ሆነ የሚለብሱት ምንም ነገር አለመኖሩን በቅርቡ ገልፀው ነበረ።በተጨማሪም የቡሬ ወለጋ መንገድ በመዘጋቱ ወዴትም መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን አሳውቀዋል።

በወለጋ የአማሮች ጭፍጨፋ በየጊዜው ሆን ተብሎ እንዲለመድ በመደረጉ ሚዲያዎችም ይሁን ማህበረሰብ አንቂዎች ትኩረት እየሰጡት እንዳለሆነ ተገልጿል።ይህ ደግሞ ሀዘኑን የበለጠ ልብ ሰባሪ አድርጎታል ተብሏል።

በግፍ ለተጨፈጨፉ አማሮች ንፍስ ይማር!!

ወግደረስ ጤናው


#share #ሼር
@tikvahethiopianss