Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopianss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.39K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-29 11:01:58
ራያ ግንባር!

የትግራይ ወራሪ ሃይል በደረሰበት አደገኛ በትር የራያ ተራሮችን እየተገረፈም ለቆ እየወጣ ነው። ትናንት ቁል ማንቁሉን ጥሎ የዞብል ተራራን ለቆ ወጥቷል።


@tikvahethiopianss
502 viewsMintesinot Hemecha, edited  08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 11:01:27
#Awaday #Gondar

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እያካሄደ የሚገኘውን የሙከራ ኔትዎርክ አገልግሎቱን እያስፋፋ ይገኛል።

ዛሬ በተላከልን መልዕክት ፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች አስጀምሯል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር 10 አድርሶታል። ከዚህ በፊት በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ላይ ሙከራ መጀመሩ ይታወቃል።

የአወዳይ እና ጎንደር ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በአወዳይ አንድ በቀበሌ ዐ1 የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር እና በጎንደር አራት (በፒያሳ፣ አራዳ፣ አዘዞ እና ኮሌጅ) የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው ሲል በላከልን መልዕክት አሳውቋል።

@tikvahethiopianss
489 viewsMintesinot Hemecha, edited  08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 09:39:56
አታለልከኝ…
*
" ማዲንጎ ልጄ ፣ ተስፋዬ ነበርክ። ጋሼ መሄዴ ነው ፀልይልኝ ብሎ ስልክ ደወለልኝ ሄደ ፣ ከሄደበት ደግሞ ሲመጣ መጥቻለሁ አለኝ።

መጥቻለሁ ድኛለሁ እግዚአብሔር ይመስገን አለኝ።

ግን አታለልኸኝ… መጣሁኝ ጠብቀኝ… እከተልሃለሁ…"

አንጋፋው ድምፃዊ ጋሽ መሀሙድ አህመድ በተሰበረ ልብ እና በለቅሶ ስለ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ…

ልባዊ መፅናናትን ለወዳጅ ቤተሰቦቹ፣ አድናቂዎቹ ይስጥልን

@tikvahethiopianss
@tikvahethiopianss
553 viewsMintesinot Hemecha, edited  06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 09:33:53
"ግብፅና ሱዳን ኢትዮጵያን በመበተን የሚረዱን ከሆነ ከእነሱ ጋር መስራት አለብን።"

በአማርኛ መግለጫቸው አማራ ዘመዴ ነው፣ ኦሮሞ ወገኔ ነው፣ አፋር ጋር ጠብ የለንም የሚሉት ለፕሮፖጋንዳ ብቻ ነው። የውስጣቸውን ስሜት የሚፅፉት በትግርኛ ነው። ይህ የህወሓት ሰው ኢትዮጵያን በትነን መዳን አለብን እያለ ነው። ኢትዮጵያን ለመበተንም ከግብፅና ሱዳን ጋር መስራት እንዳለባቸው ያሳስባል። ኢትዮጵያን ለመበተን የትኛውንም ስልት መጠቀም፣ የትኛውም ኃይል ጋር መስራት አለብን እያሉ ነው። ግልፅ አላማቸው ይሄ ነው።

ኢትዮጵያን በትኖ አማራ ዘመዴ፣ ኦሮሞ ወገኔ ነን ማለት አይችልም። ኢትዮጵያን በትኖ አፋር ጋር ጠብ የለኝም ማለት አይችልም።

@tikvahethiopianss
@tikvahethiopianss
536 viewsMintesinot Hemecha, edited  06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 08:48:45
የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በዩኒቨርስቲው በገንዘብ ዲግሪ ይሸጣል የሚለው መረጃ በመጀመሪያ ባደረኩት ማጣራት ሀሰት ነው አለ

አዲስ ማለዳ መስከረም 14/2015ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አስመልክቶ ካወጣው ዘገባ ጋር በተያያዘ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተገቢውን የማጣራት ስራ በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ኮሚቴ ተዋቅሮ በ18/01/2015 ዓ.ም ስራውን ሲያጣራ ውሏል።በማጣራት ስራው ሂደት ላይ ከዩኒቨርሲቲው Student Information Management System (SIMS) የመረጃ ቋት ላይ በሁሉም ኮሌጆች በመደበኛው፣ በሳምንት መጨረሻ፣ በክረምትና  በማታው የትምህርት መርሀ-ግብር የተመረቁትን ተማሪዎች መረጃ ከመረጃ ቋቱ ላይ በማውረድ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ካጸደቀው የተመራቂዎች ዝርዝር ቃለ-ጉባኤ ጋር የማነጻጸር ሥራ ሰርቷል፡፡

በዚህም መሰረት አዲስ ማለዳ ባወጣው ጋዜጣ የገለፀው እና ምክትል ዋና አዘጋጇ ወ/ሪት ሊዲያ ተስፋዬ በ18/01/2015 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል የሠጡት መረጃ መነሻ ተደርጎ ማጣራቱ ተጀምሯል፡፡ ምንም እንኳ ምክትል አዘጋጇ በ18/01/2015 ዓ.ም  በስልክ በሰጡት መረጃ ‹‹የ2014 ዓም  በማኔጅመንት የትምህርት ክፍል  የተመረቁትን አጣሩ›› ያሉ ቢሆንም ባለፉት አራት አመታት በሀገራችን የስርዓተ-ትምህርት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ በ2014ዓ.ም በመደበኛው መርሃ-ግብር በማኔጅመንት ፕሮግራም የተመረቁ ተመራቂዎች አለመኖራቸውን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡ በአንጻሩ አዲስ ማለዳ ‹‹ሁለት ወራት አጣርቼ አረጋግጫለሁ›› ብሎ ያወጣው ዘገባ እውነት ስለመሆኑ አንድም ፍንጭ አልተገኘም፡፡


#ወልቂጤ ዩንቨርሲቲ

@tikvahethiopianss
@tikvahethiopianss
582 viewsMintesinot Hemecha, edited  05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 21:41:15
የማዲንጎ ውንድም ያሬድ አፈወርቅ ከካናዳ የማዲንጎ ወዳጆችና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት ወደ ኢትዮጵያ ሸኝተውታል::


@tikvahethiopianss
393 viewsMintesinot Hemecha, edited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:36:45
ነዳጅ

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ፦

- ቤንዚን በሊትር 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ማስተከከያ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ሌሎች የነዳጅ ውጤቶች ማለትም የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣና ከባድ ጥቁር ናፍጣ ባሉበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።

ሚኒስቴሩ እነዚህ ተሽከርካሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ፦
- ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር
- ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ብሏል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

@tikvahethiopianss
542 viewsMintesinot Hemecha, edited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 15:38:55 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገለፀ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስታውቋል ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የመፈተኛ ተቋማት በማዘጋጀት በኩል ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መመሪያ ሀላፊ አ/ቶ ጌታሁን ፈንቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በዞኑ ተማሪዎች የሚፈተኑባቸው አምስት ተቋማት እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል ።


#ዳጉ_ጆርናል
80 viewsMintesinot Hemecha, edited  12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 11:06:33 #MadingoAfework

የተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት የፊታችን ሐሙስ እንደሚፈጸም ተገለጸ

ዕረቡ መስከረም 18 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት የፊታችን ሐሙስ መስከረም 19 ቀን 2015 አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል።

ለዚሁ የቀብር ሥነ ስርዓት የተቋቋመው ኮሚቴ ቃል አቀባይ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ (ቪ ኦ ኤ) እንደገለጸው ከሆነ፤ የድምጻዊው የቀብር ሥነ ስርዓት የፊታችን ሐሙስ በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል የሚፈጸም ይሆናል። ከቀብር ሥነ ስርዓቱ አስቀድሞም የሽኝት ፕሮግራም እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህን በተመለከተም ዝርዝሩን ኮሚቴው በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ተጠቅሷል።

ማዲንጎ አፈወርቅ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 17 ቀን 2015 ጠዋት 1፡30 አካባቢ፤ ለሐኪሙ ስልክ በመደወል ወደ ክሊኒክ እንደሄደና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ የግል ክሊኒክ የህመም ማስታገሻዎችን እና ሌሎች መድኃኒቶችን ወስዶ እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን፤ ማዲንጎ ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል።

የድምጻዊው አስክሬን ሕይወቱ ካለፈበት የግል ክሊኒክ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ በቀረበለት አቤቱታ መሠረት የድምጻዊውን ሞት መንስኤ ለማወቅ የአስክሬን ምርመራ ውጤቱን እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በደብረታቦር ከተማ የተወለደውና ከ 1980ዎቹ አጋማሽ አንስቶ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጉዞ ከተቀላቀሉ ድምፃውያን መካከል በቀዳሚኒት የሚጠቀሰው ማዲንጎ አፈወርቅ፤ በ1987 “ስያሜ አጣሁላት” በተሰኘው ቀዳሚ የአልበም ሥራው ከሙዚቃ አፍቃሪያን የተዋወቀ ሲሆን፤ በ1990ዎቹ ‹‹አይደረግም›› እንዲሁም ከቅርብ ዓመታት በፊት ‹‹ስወድላት›› የተሰኙ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን ወደ አድማጮች አድርሷል።

በተጨማሪም በበርካታ ነጠላ ዜማዎቹ በመስራት በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊ ማዲንጎ፤ አራተኛ አልበሙን ለአድማጮች ለማድረስ በመስራት ላይ እንደነበርም አዲስ ማለዳ ለማወቅ ችላለች።
504 viewsMintesinot Hemecha, edited  08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 10:44:36
#Somalia #Ethiopia

የሶማሊያ ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሶማሊያ ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር ) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሃሰን ሼክ መሃሙድ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱ ሃገራት እና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሼክ መሃሙድ ከስስት ወራት በፊት በተደረገ ምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን በወቅቱ የደስታ መልዕክት ከላኩ መሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በቀዳሚነት ተጠቃሽ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ፕሬዜዳንቱ ምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ በተለያዩ ሀገራት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

Photo Credit : የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopianss
480 viewsMintesinot Hemecha, edited  07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ