Get Mystery Box with random crypto!

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ? - ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 | TIKVAH ETHIOPIA

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ?

- ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 ወሩ ወላጆቹ ደብረ ታቦር መግባታቸውን ተከትሎ በደ/ታቦር ነው ያደገው።

- ማዲንጎ አፈወርቅ ያደገው በጦር ቤት ውስጥ ነው፤ እናት እና አባቱ "ተገኔ" /የኔ ጠበቃ/ ነበር የሚሉት፤ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ተገኔ" ነው። ማዲንጎ የሚለውን ስም ያገኘው በወታደር ቤት ውስጥ እየሰራ እያለ ነው፤ ከዛ በኃላ መጠሪያው ሆኖ ቀጥሏል።

- በልጅነቱ የሙዚቃ ፍቅር ያደረገበት ማዲንጎ ከደብረ ታቦር ወደ አዘዞ በተመለሰበት ወቅት በ7ኛ ክፍለ ጦር ካምፕ ውስጥ በ603ኛ ኮር ውስጥ ያለ የሙዚቃ ቡድን ልምምድ ሲያደርግ በመግባት ዘፈን እንደሚችል በመግለፅ እድል እንዲሰጠው ይጠይቃል፤በኃላም እድል ተሰጥቶ የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃ ከተጫወተ በኃላ አድናቆት በማግኘቱ ተቀባይነት አግኝቶ በዛው ሊቀጥል ችሏል።

- ማዲንጎ ከጦሩ ከወጣ በኃላ በ1982 ዓ/ም አካባቢ ገና በ12 ዓመቱ በባህር ዳር የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አንድም ድምፃዊ የመሆን ህልሙን መስመር ያስያዘበት በሌላ በኩል ገቢ በማግኘት እራሱንና ቤተሰቦቹን ማገዝ የቻለበትን ሁኔታ መፍጠር ችሏል።

- ማዲንጎ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኃላ በተለያዩ የሙዚቃ ክበቦች የተለያዩ አንጋፋ ድምፃዊያንን ስራዎች ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን በኃላም የራሱን ስራዎች (ነጠላና የአልበም ስራዎች) ለአድናቂዎቹ አቅርቧል።

- ማዲንጎን በስራዎቹ የሚያውቁት ወዳጆቹ ዜማ በመያዝ ችሎታ፣ ሙዚቃን አሳምሮ በመጫወትና የአድናቂዎቹን ቀልብ በመሳብ የተካነ በማህበራዊ ህይወቱም ተግባቢ፣ ቅንና ተጫዋች እንደሆነ ይመሰክሩለታል።

(ከጨዋታ እንግዳ ፕሮግራም/ከቅርብ ወዳጆቹ የተገኘ መረጃ)

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

@tikvahethiopianss