Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopianss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.39K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-09-24 19:27:46
አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች !

ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም  ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ  ኡራኤል አደባባይ

• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ

• ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር  ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ

• ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር የሚሄዱ ጠማማ ፎቅ አካባቢ

•  ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር  የሚወስደው ሚክሲኮ አደባባይ

• ከተከለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ  ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚኒዬም አካባቢ

• ከጌጃ ሰፈር ፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ

• ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ

• ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

• ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል

• ከፒያሳ በቸርችር ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ

• በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት

• ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል

• ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ መታጠፊያ ላይ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፏል።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል ነው ተብሏል።

@tikvahethiopianss
1.1K viewsMintesinot Hemecha, edited  16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 21:54:16
የ6 ዓመት ሕፃን በማገት 200 ሺህ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የሸኔ አባል እንደሆነ የተጠረጠረው ግለሰቡ የ6 ዓመት ሕፃን በማገት 200 ሺ ብር ከሕጻኑ ወላጆች በመቀበል ልጁን ሆለታ ከተማ ጫካ ውስጥ ጥሎ መሄዱ ተገልጿል፡፡ ከዚያም ዘነበ ወርቅ መናኸሪያ በመሳፈር ወደ ጅማ ከተማ ሊያመልጥ ሲል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጅማ በር ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል
1.3K viewsMintesinot Hemecha, edited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 21:00:18
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ " SKYTRAX 2022 " የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ላይ በ4 ዘርፎች ተሸለመ።

አየር መንገዱ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተገልጿል። ደረጃው በዓለም ዙሪያ ባሉ የአየር መንገድ ደንበኞች በተሰጠ ድምጽ ነው።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሸለማቸው ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ?

የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ፤

  የ2022 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ ለ4 ተከታታይ ዓመታት

የ2022 የአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ ደረጃ ፤ ለ4 ተከታታይ ዓመታት

በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነትን ሽልማት አሸንፏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopianss
1.4K viewsMintesinot Hemecha, edited  18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 13:55:16
#መቀሌ!

ትግራይ ቴሌቪዥን የድሮን ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል። ዛሬ ከማለዳው 11፡00 አካባቢ በመቀሌ ከተማ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ተፈጽሟል። በጥቃቱ ህወሃት የሚገለገልባቸው የመሳሪያ ዲፖዎች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።

@tikvahethiopianss
1.5K viewsMintesinot Hemecha, edited  10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 13:52:17
#ብሔራዊ_ፈተና

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦

- ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።

- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚፈቀዱላቸው ፦

• መጽሐፍት፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦

• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።

- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

@tikvahethiopianss
1.5K viewsMintesinot Hemecha, edited  10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ