Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopianss — TIKVAH ETHIOPIA
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopianss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.39K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-09-26 20:07:02
የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እና ሚድያዎች ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ፒኤችዲ) ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በተለያዩ ወቅታዊ የዘርፉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂዷል፡፡

መድረኩ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና፣ የተማሪዎች ምዝገባ የምገባ እና በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶች በሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተግባቦት ላይ ያተኮረ ነው ።

ከ12ኛ ክፍል ፈተና በተመለከተ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ ፈተናውን ለመፈተን ሲመጡ ማድረግ ያለባቸውንና የሌለባቸውን የተከለከሉ ጉዳዮች እና አጠቃላይ ዝግጅቶችን በሚመለከት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በውጤታማነት እንዲጠናቀቀቅ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ለሚድያዎች ትክክለኛውን መረጃ ለህበረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፤
261 viewsMintesinot Hemecha, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 09:47:00 #መልዕክት

የ " መስቀል ደመራ በዓል " አከባበርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት ፦

- ሁከት ቀስሰቃሽ መልዕክቶችን በቲሸረሰቶች ላይም ሆነ በባነሮች ላይ በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ይዞ መገኘት በፍፁም አይፈቀድም።

- በበዓሉ ላይ ህገ መንግስቱ የደነገገውን የኢትዮጵያን የፌዴራል ሰንደቅ ዓላማ #ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የፀደቀውን የቤተክርስቲያን ዓርማን ብቻ መጠቀም ይገባል። ከዚህ ውጪ የሆነ ምንም ዓይነት አርማም ሆነ ሰንደቅ አላማ መያዝ በጥብቅ የተከለከለ ነው። የምንጠቀመው ሰንደቅ ዓላማ ሆነ የቤተክርስቲያን አርማ በግልፅ የሚታዩ በሁለቱም ፊት ዓርማዎቹ በትክክል የተቀመጡ መሆን አለባቸው።

- በቲሸርቶች ፣ በባነሮች እንዲሁም በትርኢቶች ላይ ሁሉ ሌሎች ወገኖችን የሚያስከፉ፣ መብትን የሚጋፉ ሁከት ቀስቃሽ የሆኑ ጥቅሶችን መጠቀም ከሥነ ምግባር ውጪ ከመሆኑም በላይ ለሁከትና ግርግር መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

- ወደ መስቀል አደባባይ በሚደረግ ጉዞ #ተደጋጋሚ ፍተሻ ይደረጋል፤ የሚደረገው ፍተሻ ለደህንነታችን ተብሎ የሚደረግ ፍተሻ መሆኑን በመገንዘብ መላው ህዝበ ክርሰቲያን ራሱን ለፍተሻ ዝግጁ ማድረግና ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ለፍተሻ መተባበር እንደሚገባው በመረዳት የጸጥታ አካላትን መተባበር አለበት።

- በመስቀል አደባባይ እንዲሁም ደብረ ዕንቁ ቅድስት ልደታ ማርያም ጉዳይ የሚመለከተውን አካል በሕግ አግባብ መጠየቅ የሚገባና እና በጉዳዩ ዙሪያ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ያከናውናሉ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ሊደረግ አይገባም።

- በቤተክርስቲያን ማዕከላዊ አስተዳደርና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቶ ከሚሰራጨው መጽሔት እና ብሮሸር ውጪ ምንም ዓይነት የህትመት ውጤት ስለማይሰራጭ ከእነዚህ ውጪ የሆኑ የህትመት ውጤቶችንና በራሪ ወረቀቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይዞ የተገኘም በህግ ተጠያቂ ይሆናል።

- ከመስቀል አደባባይ ውጪ በአድባራትና ገዳማት በሚከበሩ የመስቀል ደመራ በዓላት ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እና በመረዳዳት መሥራት የሚገባ ሲሆን ሁከት ቀስቃሽ ከሆኑ መልዕክቶች በመታቀብና ህጋዊ ያልሆኑ ሰንደቅ ዓላማዎችን ባለመጠቀም የበዓሉን ሰላማዊነትና የመስቀሉን ዓላማ መሰረት ያደረጉ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሱ እንቅስቃሴዎች ሊደረጉ ይገባል።

- ማንኛውም አጠራጣሪ እና ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች ሲያጋጥም በቦታው ለተመደቡ የሥነሥርዓትና የጸጥታ አስከባሪ አባላት / ለፖሊስ አካላት መጠቆም ይገባል።

(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን)

@tikvahethiopianss
235 viewsMintesinot Hemecha, edited  06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 19:17:53 የወሎ ግንባር አሁናዊ መረጃ

በግዳን ፣በቀሊም ፣ በላጎ እና በአላውሃ በግራ በኩል ወጊያው ውሎውን አሁን ድረስ እንደቀጠለ ነው

ከውጤት አኳዬ፦

በግዳን ግንባር ፦ ቀይ አፈር ላይ የነበረው የወገን ጦር ተኩለሽን ፣ ሸዊ ማርያምን ተቆጣጥሮ ገደባ ላይ ደርሷል። ትናንት በበቅሎ ማነቂያ በኩል ያለው ግንባር ከአራዶም በ5 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ አረፋ ጊዮርጊስ ደርሶ ወደ ፊት እያጠቃ ነው።

በቃሊም በላጎ ግንባር ፦ በአስሜላ በኩል ቆርጦ የገባው የወገን ጦር አእጅግ ገዥ የሆነውን ጤፍ ውኃን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ቆላ በላጎ ላይ እየተፋለመ ይገኛል።

የአላውሃ ግንባር፦ በግራ በኩል የገባው የወገን ጦር ፊት ለፊት አሰፍስፎ የነበረውን ጠላት እየጠረገ ዱር ለበስ አድርሶታል።

በአጠቃላይ አሁናዊ የወገን ጦር እንቅስቃሴ እጅግ የተናበበ መከላከያም በአካባቢውን ኅብረተሰብ እና በሚመለከታቸው አመራሮች የሚሰጠውን መረጃና ጥቆማ በተገቢው እየተጠቀመበት ይገኛል። የህዝቡ ደጀንነት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

@tikvahethiopianss
837 viewsMintesinot Hemecha, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 18:28:35
" ዘገባው ታርሞ እና ተስተካክሎ ይውጣ " - የፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባ ታርሞና ተስተካክሎ እንዲወጣ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ጠይቋል።

ኮሚሽኑ ፤ ሪፖርተር ጋዜጣ መስከረም 14/2015 ዓ.ም በእንግሊዘኛ እና መስከረም 15/2015 ዓ.ም በአማርኛ እትሙ " የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ስራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሣይ ሪፖርት ቀረበ " በሚል ርዕስ ያወጣው ዘገባ የፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በትምህርት ዘርፍ ካስጠናው ጥናት ሪፖርት ጋር የማይጣጣም ነው ሲል አሳውቋል።

" ሙስናን ለመከላከል የሚዲያ ሚና የጎላ ነው " ያለው ኮሚሽኑ " ሪፖርተር ጋዜጣ ትክክለኛውን መረጃና ጥናት ከኮሚሽናችን በማግኘት የማስተካከያ ዘገባ እንዲሰራ እንጠይቃለን " ብሏል።

ምንም እንኳን ኮሚሽኑ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ጥናት በትምህርት ዘርፉ ላይ በኮሚሽኑ ከተደረገው ጥናት ጋር የማይጣጣም መሆኑን ቢገልፅም አድርጌዋለሁ ያለውን ጥናት (ትክክለኛውን ማለት ነው) በይፋ አላሰራጨውም።

@tikvahethiopianss
847 viewsMintesinot Hemecha, edited  15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 17:43:28
የፌደራል ስነምግባርና ጸረሙስና ኮሚሽን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባ ታርሞና ተስተካክሎ ይወጣ ዘንድ ጠየቀ


" ሪፖርተር ጋዜጣ በትምህርት ዘርፍ የሙስና ሥጋት የሆኑ ጉዳዮችን የሚለይ ጥናት ሪፖርት፣ በአግባቡ ሳይገነዘብ የጥናቱ ይዘትም ሆነ ውጤት የማይዳስሰውን ያወጣው ሪፖርት፣ የኮሚሽኑን እና የተቋማትን ዕውነታ ስለማይወክል ተገቢውንና ተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሠረተ ማድረግ ያስፈልጋል። በሙስና መከላከል የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን እየተገነዘብን፣ በቀጣይም በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረተ የሚዲያ ሥራ በቅንጅት እንሥራ!"

ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ)
የፌደራል ስነምግባርና ጸረሙስና ኮሚሽነር
837 viewsMintesinot Hemecha, edited  14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:45:29 #ETHIOPIA

ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው ተልዕኮ ውጪ ለሆነ #የፖለቲካ_ሥራ እንደሚውል በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተጠና ጥናት ላይ መገለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ኮሚሽኑ ጥናቱን ያከናወነው በፌዴራል ደረጃ በሚገኙ የመንግሥትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የጥናቱ ትኩረት ሙስናና ብልሹ አሠራር በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርሰውን የሙስና ሥጋት ለመለየት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከምንጮቼ አገኘሁት ያለውና ኮሚሽኑ በተመረጡ 61 ተቋማት ላይ ያደረገው የጥናት ሪፖርት እንደሚያሳየው ፦

- በተቋማቱ፤ ከመምህራን ልማት እና ከአሠልጣኞች ምልመላ ጋር በተገናኘ፣ የዘመድና የፓርቲ አሠራር፣ እንዲሁም አድልኦና ጉቦ የመቀበል አዝማሚያ በስፋት ይስተዋላል።

- በመምህራንና ሠራተኞች አስተዳደር ክፍል ሕገወጥ ቅጥርና ዝውውር መኖር፣ መምህራን ተማሪዎችን ለይቶ ለመጥቀም የሚደረግ ዝንባሌ መኖር፣ ለመምህራን ቅጥር ውድድር ተፈልጎ እኩል ውጤት ሲመጣ፣ አንዱን በትውውቅ ብቻ የመምረጥ አሠራር እንደሚስተዋል ተገልጿል፡፡

- ከሐሰተኛ የትምህርት ሰነድ ጋር በተያያዘ የብቃት ማረጋገጥና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ መሥፈርት ሳያሟሉ፣ ለተቋማት ፈቃድ መስጠት እና የፈቃድ ዕድሳት እንደሚከናወን ተግልጿል።

- መምህራንና በትምህርት አስተዳደር አመራር ላይ ያሉ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች እንደተገኘባቸው ፤ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት ሲሞከር ደግሞ ሠራተኞች ከሥራ ቀድመው የመልቀቅ እንቅስቃሴ እንዳለ ተገልጿል።

- በግል ኮሌጆች የሲኦሲ ምዘና ሳያልፉና ትምህርት አጠናቀው ሳይጨርሱ፣ እንዲሁም ፈጽሞ ያልተማሩ ሰዎች የትምህርት ማስረጃ አትሞ መስጠትና በኮሌጆች ሽያጭ የመፈጸም ድርጊት መኖሩን ሪፖርቱ ገልጿል።

- በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች ሬጅስትራሮች ውስጥ የተማሪዎችን ውጤት የማሳሳትና የማጭበርበር ድርጊት እንዳለ ተጠቅሷሳ።

- በግል ትምህርት ተቋማት ውሳኔዎች የሚተላለፉት ለተቋማቸው መልካም ስም ቅድሚያ በመስጠት እንደሆነ፣ በመንግሥት ተቋማት ደግሞ ሰነድ ማዘጋጀት እንጂ ትግበራ ላይ እምብዛም እንደሌሉበት ተገልጿል።

- በተደረገው ጥናት በተቋማቸው ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ ወይ ተብለው ከተጠየቁት ውስጥ 65 በመቶ የሚሆኑት " አዎ " የሚል መልስ መስጠታቸውን፣ 35 በመቶ የሚሆኑት " የለም " የሚል መልስ ሲሰጡ፣ በተመሳሳይ የሙስና ችግሮች መኖራቸውን 66 በመቶ መናገራቸውና 47 በመቶ ደግሞ ለሚቀርቡ ጥቆማዎች ከተቋማቱ መልስ እንደማይሰጥ ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

- በትምህርት ተቋማቱ የመምህራን በተደጋጋሚ ወደ ክፍል አለመግባት፣ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መስጠት፣ በአመራር የሚከናወን ስርቆት፣ ሕገወጥ ዝውውርና የደረጃ ዕድገት፣ ሕግና ደንብን ተከትሎ የማይከናወን ግዥ፣ የመረጃና ማስረጃ ማጭበርበር፣ ግልጽነት የሌለው አሠራር መብዛት፣ በሬጅስትራር የሚፈጸም ብልሹ አሠራር ተቋማቱን ለከባድ ሙስና አደጋ ጥሏቸዋል፡፡

- በግዥ ወቅት ለተቋም የማያስፈልግ ንብረት እንዲገዛ ተጨማሪ በጀት ማስያዝ፣ በጨረታ ወቅት የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ እንዲጋብዝ አድርጎ ሰነድ ማዘጋጀት፣ ወቅቱንና ጥራቱን ያልጠበቀ ግንባታ እንዲከናወን ማድረግ፣ በሕንፃ ርክክብ ጥራቱን ያልጠበቀ ሕንፃ እንዲገነባ ማድረግና ያልተጠናቀቀ ሕንፃ መረከብ ተቋማቱን ለከባድ ሙስና እንዳጋለጣቸው ሪፖርቱ ያሳያል።

እንደ ምክንያት የተጠቀሱት ችግሮች ምንድናቸው ?

• የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ፣
• የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት አለመኖር፣
• የሞራል መላሸቅ፣
• የተጠያቂነት ማነስ፣
• የላላ የአመራር ቁጥጥርና ከፍተኛ የሆነ የበጀት ምደባ የሚሉት ይገኙበታል።

ጥናቱ በሚደረግበት ወቅት ምን ችግሮች አጋጠሙ ?

➤ የተቋማት አመራሮች በቦታው ላይ አለመገኘት፣
➤ ተቋማት መረጃ ለመሥጠት ፈቃደኛ አለመሆን፣
➤ የተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች መረጃዎችን በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመሥርቶ አለመስጠት ... መሰል ዓይነት ችግሮች ነበሩ።

ሪፖርተር
https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-09-25

@tikvahethiopianss
1.0K viewsMintesinot Hemecha, edited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:45:29
* አዲስ አበባ

ከመስቀል በዓል ጋር በተያያዘ ከዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 17/2015 ዓ.ም ማታ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ ሲሆን  ይሄንን ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopianss
869 viewsMintesinot Hemecha, edited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:45:28
" የቀድሞ የአቅራቢነት ምዝገባ ከህዳር 30 በኃላ አገልግሎት አይሰጥም " - የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመንግስት ግዥ ለሚሳተፉ አቅራቢዎች ባሰራጨው ደብዳቤ የቀድሞው የአቅራቢነት ምዝገባ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በኋላ አገልግሎት እንደማይሰጥ አሳውቋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ፤ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓትን (e-GP) ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑና በአሁን ወቅት 73 የፌዴራል ተቋማት በሲስተሙ ተጠቅመው ግዥ መፈፀም መጀመራቸው ገልጿል።

በአጭር ጊዜ ውስጥም የተቀሩት የፌዴራል ተቋማት ሙሉ በሙሉ የሲስተሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው ብሏል።

በሥራ ላይ የዋለው የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሲስተም ለመንግስት ተቋማት አመታዊ የግዥ ዕቅድን ከማዘጋጀት ጀምሮ፣ ጨረታን የማውጣት ፣ የመገምገምና አሸናፊ የመለየትና ውል የማስተዳደር ሥራዎችን እንዲያከናውኑ የሚያስችል መሆኑን አመልክቷል።

በተጨማሪ ሲስተሙ ለአቅራቢው ማህበረሰብ በአቅራቢነት እንዲመዘገቡና ለጨረታ የመወዳደር ሂደታቸው ሙሉ ለሙሉ በሲስተም የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል ሲል አስረድቷል።

በዚህም ፤ ከዚህ በፊት በባለስልጣን መ/ቤቱ ድረ-ገጽ (https://www.ppa.gov.et/) ላይ የተመዘገቡ አቅራቢዎች ምዝገባቸው ተቀባይነት የሚኖረው የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓትን (e-GP) መጠቀም ባልጀመሩ ተቋማት ብቻ እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አስገንዝቧል።

በመሆኑም በ https://egp.ppa.gov.et/ ላይ በመግባት ተገቢውን ምዝገባ በማከናወን በመንግስት ግዥ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ አሳውቋል።

@tikvahethiopianss
869 viewsMintesinot Hemecha, edited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 09:48:52
#UNGA

የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት #በአፍሪካ_ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

አቶ ደመቀ ፤ ይህንን የገለፁት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ ነው ያሉ ሲሆን " ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ የሚደረግ ሌላ አካሄድ ተቀባይነት አይኖረውም። " ሲሉ ተናገረዋል።

በሌላ በኩል በንግግራቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ #በአፍሪካ_ህብረት ማዕቀፍ ስር በሚደረግ የሶስትዮሽ ድርድር ጉልህ ተፅዕኖ በማያደርስ እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ልዩነቶችን ለመፍታት አሁንም ፅኑ አቋም አላት ሲሉ ለጉባኤው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በንግግራቸው አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ውስጥ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጠይቀዋል።

" እኛ አፍሪካውያን ይህ ጥያቄያችን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ይህን ጥያቄ መጠየቃችንን እንቀጥላለን። " ብለዋል።

ምትክል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን የሚችለው ፤ የሚሰጠውም ጭምር በፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ተገቢው ውክልና ሲኖራት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ምሽት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ ያሰሙት ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል (40 MB)።

@tikvahethiopianss
903 viewsMintesinot Hemecha, edited  06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 22:38:48
#ሶማሊያ

በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ለ13 ዓመታት አልሸባብ ሲቆጣጠረው የነበረው ዋና መንገድ ነፃ መደረጉ ተገለፀ።

ለ13 አመታት በአልሸባብ ቁጥጥር ስር የነበረው በሂራን ክልል ቡልቡርዴ እና በለድዌይን ወረዳዎች መካከል ያለው ዋና መንገድ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር በአካባቢው ነዋሪዎች እገዛ ነፃ ማድረጉን አሳውቋል።

የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ አስተዳደር በአልሸባብ ይዞታዎች ላይ እያካሄደ ያለውን እጅግ መጠነ ሰፊ ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን በተለይም በሂራን ክልል በርካታ ቦታዎችን ከአልሸባብ ነፃ ማድረግ ተችሏል።

በዚህ የፀረ ሽብር ዘመቻ ላይ አሜሪካም በአየር የአልሸባብ ይዞታዎችን በመደብደብ እገዛ እያደረገች መሆኑን ከሀገሪቱ መንግስት የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

የአፍሪካ ህብረት ኃይልም ለፀረ ሽብር ዘመቻው የአየር ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopianss
1.0K viewsMintesinot Hemecha, edited  19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ