Get Mystery Box with random crypto!

#ሶማሊያ በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ለ13 ዓመታት አልሸባብ ሲቆጣጠረው የነበረው ዋና መንገድ ነፃ መ | TIKVAH ETHIOPIA

#ሶማሊያ

በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ለ13 ዓመታት አልሸባብ ሲቆጣጠረው የነበረው ዋና መንገድ ነፃ መደረጉ ተገለፀ።

ለ13 አመታት በአልሸባብ ቁጥጥር ስር የነበረው በሂራን ክልል ቡልቡርዴ እና በለድዌይን ወረዳዎች መካከል ያለው ዋና መንገድ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር በአካባቢው ነዋሪዎች እገዛ ነፃ ማድረጉን አሳውቋል።

የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ አስተዳደር በአልሸባብ ይዞታዎች ላይ እያካሄደ ያለውን እጅግ መጠነ ሰፊ ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን በተለይም በሂራን ክልል በርካታ ቦታዎችን ከአልሸባብ ነፃ ማድረግ ተችሏል።

በዚህ የፀረ ሽብር ዘመቻ ላይ አሜሪካም በአየር የአልሸባብ ይዞታዎችን በመደብደብ እገዛ እያደረገች መሆኑን ከሀገሪቱ መንግስት የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

የአፍሪካ ህብረት ኃይልም ለፀረ ሽብር ዘመቻው የአየር ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopianss