Get Mystery Box with random crypto!

ሶሃቦች በቆሙበት ቁም!

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewuhidtewuhid — ሶሃቦች በቆሙበት ቁም!
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewuhidtewuhid — ሶሃቦች በቆሙበት ቁም!
የሰርጥ አድራሻ: @tewuhidtewuhid
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.60K
የሰርጥ መግለጫ

http://t.me/TewuhidTewuhid

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-15 17:19:42
‹‹ልጆቻችንን በማለዳ ማን እንደወሰደብን አናውቅም፡፡ እባካችሁ ልጆቻችንን አፋልጉን፡፡›› ወላጆች
(Please SHARE! Spread it.)
**********
በፎቶው ላይ የምታዩዋቸው ሁለት ሕጻናት አስማ ናስር እና ሐሰን ናስር ይባላሉ፡፡ ወንድምና እህት ናቸው፡፡ አስማ ዕድሜዋ 13 ሲኾን፣ ሐሰን የ10 ዓመት ሕጻን ነው፡፡ ሳዑዲ አረቢያ የተወለዱት እነዚህ ሕጻናት፣ ከወላጆቻቸው ጋር በቅርቡ ነው ወደ ኢትዮጵያ ተባረው የመጡት፡፡ በደንብ መናገር የሚችሉት ቋንቋም አረብኛ ነው፡፡

ትናንት ሐሙስ ማለዳ 11፡00 ገደማ አሸዋ ሜዳ፣ አብድ ኖኖ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ጀርባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው፣ ወላጅ አባታቸው አቶ ናስር ለሱብሒ ሶላት ወደ መስጊድ ሲወጣ በመኝታ ክፍላቸው ነበሩ፡፡ ነገር ግን አቶ ናስር ከሶላት ሲመለስ ሁለቱን ሕጻናት ልጆቹን ና ለጊዜው ፎቶዋ ያልተገኘ አብራቸው የምታድግ ፈትሂያ ኑራ የተባለች የ11 ዓመት ሕጻን በቤቱ ውስጥ አጥቷቸዋል፡፡

እናታቸው ተኝታ ስለነበር፣ ልጆቹ ወዴት እንደሄዱ፣ ምን እንዳገኛቸው፣ ማን እንደወሰዳቸው ያወቀችው ነገር የለም፡፡

እናም፣ "እባካችሁ ወገኖቻችን፣ ልጆቻችንን አፋልጉን" ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል፡፡

የአባታቸው ስልክ ቁጥር 0960-04 37 67 ነው።
***
እባካችሁ ይህን መልዕክት ሼር በማድረግ ሦስቱ ሕጻናት እንዲገኙ እንተባበር፡፡
181 views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 14:11:30 የሙዚቃ ሀራምነት

ገራዶ ቢላል መስጂድ

t.me/abumuazhusenedris
337 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 13:35:13 ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-
" ስራ የሚበላለጠው በብዛት አይደለም ነገር ግን ስራው በሚሰራበት ጊዜ ልብ ውስጥ በሚከሰተው ሁኔታ ነው "
መጅሙዕ አል ፈታዋ ( 25/282 )
http://t.me/TewuhidTewuhid
489 views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 10:46:16 ውሻታሞች ተረገሙ!!! ሰሞነኛ

አሏህ ሆይ!! እዚህ ፅሁፍ ላይ ከዋሸሁ ቁጣይ ይነፃፀርብኝ ግን ከውሸት ባንት እጠበቃለሁ ያረብ

قُتِلَ الْخَرَّاصُونَ

በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡

በሰሞኑ በተለያዩ የፊስቡክ ድረ ገፆች የሚናፈሱ የጥላቻና የውሼት ዜናዎች አሉና ለተመልካች ግራ እንዳያጋቡ በትንሹ ጥቆማ ልሰጥ ወደድኩ

ለአሉቧልታው መነሻ የሆነው ባለፈው ባለቤቶቼን የሚያመሰገን ፅሁፍ ፖስት ማድረጌ ነው አይዋ አሁንም የቀና ቢቀና የተመቀኘ ቢመቀኝ የኔ ባለቤቶች ድንን በቅጡ የተረዱ በትዕግስት የተሞሉ ናቸው የቀናም የተመቀኘም በጭንቅላቱ ይከስከስ

ውሸት ①

ሁለተኛዋን ሚስቱን ሲያገባ ከወለደች ነው ዘመዶቻ የሰሙት ለሚለው መልስ እሁድ ተጋብተን በቀጣዩ ሀሙስ ዚነት የምትባለው እህቷ መታ ያየቻት ተመልከቱ የውሸት ጥግ

ውሸት ②

ሴቶችን ስንት አመትሽ ነው ውጭ ከሄድሽ ስንት ብር አለሽ ይላል የሚል ክስ ተነስቷል

መልስ ወሏሂ ወቢላሂ ወተሏሂ በእድሜዬ አንድት እንስት ይሄን ጥያቄ ጠይቄ አላውቅም ሀታ ያክስት ያጎቶቼ ልጆች አረን አገር ናቸው ስንት ነው ደሞዛቹህ ብዬ አላውቅም

በዚህ ላይ የዋሸውን አካል አሏህ አይዘንለት እኔም ሆንኩ ያወራው አካል

ውሸት ③

መቅደላ ደዕዋ እናደርጋለን እያለ ግሩፕ ከፍቶ ብር ይሰበስባል የሚል ነው መልስ

አዎ ሀገሬ ልጆች ጋር ተወያይተን ለትራንስፖርትና እዚያ ተሂዶ ህዝቡ ሲሰበሰብ የምሳ የውሃ እንድንላቸው ተብሎ ግሩፕ ተከፍቷል

የተከፈተውም በወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን ኢስማዒል በሚል ስሙና በወንድም ኑሩ ከማል ነው እንደውም የሹታ አባሉ በማን እንደሚከፈት ሰው በሚመርጡ ጊዜ በአቡ ሙአዝ ካልሆነ አይሆንም ብለው ተንጫጭተው ነበር እኔ ነኝ እነኚህን ሁለት ወንድሞች የመረጥኩላቸው

እና በአካውንቱ ወደ አንድ መቶ አርባ ምናምን ሺ ብር ገብቷል ሁሉም እንደተከበረ አለ ወሏሂ የሚገርመው ነገር እዛ ውስጥ ለግል የሚላክ ብር አብሮ ገብቶ እኔ ከራሴ ብር ሰጥቼላቸው አውጥቼ እንኳ አልወሰድኩም ይሄንን ጓደኞቼ የሚያውቁት እውነታ ነው

ለምን ደእዋ አልተሄደም ለሚለው ቡዙ ጊዜ ሞክረን ያገራችን ሰዎች ድፍን የመቃ ውሃቢያ ሊመጣብን ነው ብለው ሲንጫጩ እስኪ ዘዴ እናመቻች እያልን እዚህ ደርሷል

ባለፈው ያገሪቱ ዋና ተጠሪ የቀድሞ ቃዲ የሆነው ያጎታችን ልጅ መሃቤ ዘይኑና ልጁ ኡስታዝ አህመድ መሃቤ በሸዋል ፆም ላይ እቤቴ መተው ነበር

እዛ ያመሱልኝ ሀሳብ ያስገርማል አገር ተሰብስቦ መሃቤ ዘይኑን ገና ልጄ ውሃቢያ ሆነ ብለህ እዚህ አካባቢ ውሃቢያ ብታመጣ እልቂት ይፈጠራል ብለው እንዳስፈራሩትና ቢሆንም እናሳካዋለን የሚል ሙሉ ተስፋ እንዳለው ነግረውኛል

ውሸት ④

ቢላል መርከዝ ብሎ ከፍቶ ብር በላ የሚል ነው መልስ

እዚህ አገር ሲያመጡኝ የተወሰነች ነገር ከመስጊዱ እርሻ ከምትገኘው ሊከፍሉኝ ሙሉ ቀን ላቀራ ነበር

ግን አህባሽ የመስጊዱን ኮሚቴ ከሶ የመስጊዱ ገቢ ለማንም እንዳይሷረፍ ሲታገድ ጧትና ማታ ብቻ እያቀራሁ ቀን ቀን ሪዝቅ ለመፈለግ መንቀሳቀስ ጀመርኩ

በዚህ መሃል ከወጣቱ ጋር ሹራ አርገን እርዳታ እንጠይቅና አንድ ኡስታዝ አምጥተን ሙሉ ቀን ይቀራ ተባባልን ወጣቱ እኔው ቁጭ ብዬ እንዳቀራ ቢፈልጉም እኔ ግን ሌላ ኡስታዝ መምጣት አለበት የሚለውን አተኮርኩና ዛሬ ኮምቦልቻ ኢማም የሆነውን ወንድም ኡስታዝ አህመድን አመጣሁላቸው

የግሩፑንም አካውንት በወንድም ኢስማኢል አራጋውና በወንድም ኡመር ሰይድ እንድከፈት አደረኩ ተከፈተም

ከሀምሳ ሺ ያነሰ ገባ ኡስታዙም ድሮ የነበራቸው ሰዎች ሲጨቀጭቁትና ልጆቼም ሙቀት ለምደው አልተመቻቸውም ብሎ አውፍ በሉኝ ብሎ ሄደ

ከዚያ ቀሪ ብሩ ሲፀና ወደ 29 ሺ ገደማ እንዳለ ታወቀ በዚያች ብር ቁርኣን አቅሪ የለንምና ለሱ መነሻ ደሞዝ ትሁነን ተብሎ እየተፈለገ ነው እንደውም ባለፈው ከነ ሸ አብደሰላም መስጊድ አንድ ልጅ ተገኝቶ በሆነ ኬዝ ሳይሳካ ቀርቷል አሁንም እየፈልግን ነው ያችን ብር ለመነሻ አስበን

ውሸት ⑤

አል ኢህሳን መርከዝ ብለ ከፈቶ የሚል ነው መልስ

አል ኢህሳንን ያመቻቸሁት እኔ አይደለሁም አመታቶችን አስቆጥሯል ይሁን እንጂ አብዛኞቹ መሪዎች ኢኽዋኖች ስለነበሩ ዋና ማናጀሩ ግን ስለፊያን እየተረዳ ሲመጣ ከጎኑ ሁነን እንድናግዘውና የሰለፊያ ተቋም እንድሆን ጥሪ አቅርቦልናል

እኛም ግራ ቀኝ በማየት ቡዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩብንም እሺ ብለን ሸይኽ ሙሀመድ መኪንን ይዘን ሀሳቡን ተጋርተን ተቀላቅለናል

ከዚያም ተሀድሶ ለማድረግ የንያ ፕሮግራም በላይቭ አካሂደናል

አካውንቱንም በወንድም አቡ ረይስ በወንድ አቡ ሂበቲላህ በወንድም ሶላሀድን ከፍተናል

እንደተባለውም የክረምት ኮርስ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነን ታዲያ የቱ ላይ ነው ጥፋቱ??

የመጨረሻ ማሳስበው ወሏሂ በውሸት ነገር መለጠፍ ሰውን ከመግደል አይተናነስም ከዚህ ቡሃላ የፈለጉትን ቢሉ መልስ አልሰጥም ምን አልባት ይህንኑ ሀሳቤን አንብበው ለማይረዱ ወገኖች በድምፅ ልገልፀው እችላለሁ።

አቡ ሀኒፋ ላይ አንድት ሴት አስገድዶ ሊደፍረኝ ብላ ካወራች ቡሃላ ሌላ ጊዜ ሰዎች በይ ስላሉኝ እንጂ አልደረሰብኝም እንዳለችው ሴት ለኔ ትልቅ ፈተና ቢሆንም ሞተን እንገናኛለን ባደባባዩ ሜዳ እድሜ ለሞት ሁሉም እዚያ ይገለፃል።

t.me/abumuazhusenedris
533 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:51:41 በዚህ ቻናል ፦

በ ❶- ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
❷- ኡስታዝ ኸድር አል-ኬሚሴ
❸- ኡስታዝ ሳዳት ከማል
❹- አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
❺- ዐብዱ ሽኩር አቡ ፈውዛን
❻- ኡስታዝ ሑሴን ዐሊይ
❼- ኡስታዝ አቡ ሙስሊም አል-አሩሲ
❽- ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
❾- አቡ ሙዓዊያ ሰዒድ ሙኑር
❿- አቡል ዐባስ ናስር ሙሐመድ
⓫- ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም
⓬- ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሐሰን ኢድሪስ
⓭- ኢብኑ ሙሐመድዘይን
⓮- ሸይኽ አወል አሕመድ አል-ኬሚሴ
⓯- አቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም
⓰- ዐብዱል ጀባር ሙኑር
⓱- አቡ ማሂር ሙባረክ ኢድሪስ
⓲- ዶ/ር ሰዒድ ሙሳ አቡል ቡኻሪ
⓳- አጫጭር የዐረብኛ ደርሶችን
እና ⑳- በሌሎች ኡስታዞችና ወንድሞች

ተቀርተው የተጠናቀቁ ኪታቦችን ፣ ሙሓዶራዎችን ፣ መፅሐፎችን ፣ ፈትዋዎችንና ፈዋኢዶችን ያገኛሉ።

“መገጠሜም በአላህ እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ፡፡ ወደእርሱም እመለሳለሁ።” [ሁድ: 88]


https://t.me/MOhamedAljawi
492 views20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:38:58 يقول الإمام الجليل الفضيل ابن عياض - رحمه الله تعالى  -
 " اتبع طرق الهدى ولا يضرك قلة السالكين ، وإياك وطرق الضلالة ، ولا تغتر بكثرة الهالكين "
 الإعتصام :(135/ 1)
ታላቁ ሊቅ ፉደይል ኢብኑ ዒያድ - ረሒመሁ ላሁ - እንዲህ ይላል
" ቀጥተኛውን መንገድ ተከተል የተከታዮቹ ማነስ አይጎዳህም
የጥመትን መንገድ ተጠንቀቅ በሚጠፉ ሰዎች ብዛት አትሸንገል "
አል ኢዕቲሳም: ( 1/135 )
http://t.me/TewuhidTewuhid
441 views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:42:52 ኢብኑልቀይም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ;-

ከሷሊሖች ጋር መቀማመጥ ከስድስት ሁኔታዎች ወደ ሌላ ስድስት ሁኔታዎች ይቀይሩሃል።

1-ከጥርጣሬ ወደ እርግጠኛነት
2-ከይዩልኝ ወደ ኢኽላስ
3-ከዝንጉነት ወደ አላህን ማስታወስ
4-ከዱንያ ውዴታ ወደ አኺራ ውዴታ
5-ከኩራተኝነት ወደ መተናነስ
6-ከመጥፎ ኒያ ወደ ነሲሓ

http://t.me/TewuhidTewuhid
450 views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:01:08 ሐሰን አልበስሪ [ረሂመሁላህ] እንዲ ይላሉ

" ለቢድዐ ሰው ሃሜት የለውም!!
አመፁንም ባደባባይ ለሚያወጣ አመፀኛም ሃሜት የለውም።"

[ሸረሑ ኡሱሉ ሱና ሳለካኢ 153]

http://t.me/TewuhidTewuhid
505 views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:00:06 የምንናገረው የምንፅፈው ሁሉ እየተመዘገበ ነው
~
ከዐርሹ በላይ የሆነው ጌታ እንዲህ ይላል:-
{ وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَـٰنَ وَنَعۡلَمُ مَا تُوَسۡوِسُ بِهِۦ نَفۡسُهُۥۖ وَنَحۡنُ أَقۡرَبُ إِلَیۡهِ مِنۡ حَبۡلِ ٱلۡوَرِیدِ (16) إِذۡ یَتَلَقَّى ٱلۡمُتَلَقِّیَانِ عَنِ ٱلۡیَمِینِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِیدࣱ (17) مَّا یَلۡفِظُ مِن قَوۡلٍ إِلَّا لَدَیۡهِ رَقِیبٌ عَتِیدࣱ (18) }

"ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታናግረውን የምናውቅ ስንሆን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡
ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ሆነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የሆኑ (መላእክት) ያሉበት ቢሆን እንጅ፡፡"
[ ቃፍ: 16-18]
=
https://t.me/IbnuMunewor
567 views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 00:39:10

ዓብደላህ ኢብን ዑመር [አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና] የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ አለ። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ። “ እስልምና አምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።”

ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።


http://t.me/TewuhidTewuhid
528 views21:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ