Get Mystery Box with random crypto!

ውሻታሞች ተረገሙ!!! ሰሞነኛ አሏህ ሆይ!! እዚህ ፅሁፍ ላይ ከዋሸሁ ቁጣይ ይነፃፀርብኝ ግን ከው | ሶሃቦች በቆሙበት ቁም!

ውሻታሞች ተረገሙ!!! ሰሞነኛ

አሏህ ሆይ!! እዚህ ፅሁፍ ላይ ከዋሸሁ ቁጣይ ይነፃፀርብኝ ግን ከውሸት ባንት እጠበቃለሁ ያረብ

قُتِلَ الْخَرَّاصُونَ

በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡

በሰሞኑ በተለያዩ የፊስቡክ ድረ ገፆች የሚናፈሱ የጥላቻና የውሼት ዜናዎች አሉና ለተመልካች ግራ እንዳያጋቡ በትንሹ ጥቆማ ልሰጥ ወደድኩ

ለአሉቧልታው መነሻ የሆነው ባለፈው ባለቤቶቼን የሚያመሰገን ፅሁፍ ፖስት ማድረጌ ነው አይዋ አሁንም የቀና ቢቀና የተመቀኘ ቢመቀኝ የኔ ባለቤቶች ድንን በቅጡ የተረዱ በትዕግስት የተሞሉ ናቸው የቀናም የተመቀኘም በጭንቅላቱ ይከስከስ

ውሸት ①

ሁለተኛዋን ሚስቱን ሲያገባ ከወለደች ነው ዘመዶቻ የሰሙት ለሚለው መልስ እሁድ ተጋብተን በቀጣዩ ሀሙስ ዚነት የምትባለው እህቷ መታ ያየቻት ተመልከቱ የውሸት ጥግ

ውሸት ②

ሴቶችን ስንት አመትሽ ነው ውጭ ከሄድሽ ስንት ብር አለሽ ይላል የሚል ክስ ተነስቷል

መልስ ወሏሂ ወቢላሂ ወተሏሂ በእድሜዬ አንድት እንስት ይሄን ጥያቄ ጠይቄ አላውቅም ሀታ ያክስት ያጎቶቼ ልጆች አረን አገር ናቸው ስንት ነው ደሞዛቹህ ብዬ አላውቅም

በዚህ ላይ የዋሸውን አካል አሏህ አይዘንለት እኔም ሆንኩ ያወራው አካል

ውሸት ③

መቅደላ ደዕዋ እናደርጋለን እያለ ግሩፕ ከፍቶ ብር ይሰበስባል የሚል ነው መልስ

አዎ ሀገሬ ልጆች ጋር ተወያይተን ለትራንስፖርትና እዚያ ተሂዶ ህዝቡ ሲሰበሰብ የምሳ የውሃ እንድንላቸው ተብሎ ግሩፕ ተከፍቷል

የተከፈተውም በወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን ኢስማዒል በሚል ስሙና በወንድም ኑሩ ከማል ነው እንደውም የሹታ አባሉ በማን እንደሚከፈት ሰው በሚመርጡ ጊዜ በአቡ ሙአዝ ካልሆነ አይሆንም ብለው ተንጫጭተው ነበር እኔ ነኝ እነኚህን ሁለት ወንድሞች የመረጥኩላቸው

እና በአካውንቱ ወደ አንድ መቶ አርባ ምናምን ሺ ብር ገብቷል ሁሉም እንደተከበረ አለ ወሏሂ የሚገርመው ነገር እዛ ውስጥ ለግል የሚላክ ብር አብሮ ገብቶ እኔ ከራሴ ብር ሰጥቼላቸው አውጥቼ እንኳ አልወሰድኩም ይሄንን ጓደኞቼ የሚያውቁት እውነታ ነው

ለምን ደእዋ አልተሄደም ለሚለው ቡዙ ጊዜ ሞክረን ያገራችን ሰዎች ድፍን የመቃ ውሃቢያ ሊመጣብን ነው ብለው ሲንጫጩ እስኪ ዘዴ እናመቻች እያልን እዚህ ደርሷል

ባለፈው ያገሪቱ ዋና ተጠሪ የቀድሞ ቃዲ የሆነው ያጎታችን ልጅ መሃቤ ዘይኑና ልጁ ኡስታዝ አህመድ መሃቤ በሸዋል ፆም ላይ እቤቴ መተው ነበር

እዛ ያመሱልኝ ሀሳብ ያስገርማል አገር ተሰብስቦ መሃቤ ዘይኑን ገና ልጄ ውሃቢያ ሆነ ብለህ እዚህ አካባቢ ውሃቢያ ብታመጣ እልቂት ይፈጠራል ብለው እንዳስፈራሩትና ቢሆንም እናሳካዋለን የሚል ሙሉ ተስፋ እንዳለው ነግረውኛል

ውሸት ④

ቢላል መርከዝ ብሎ ከፍቶ ብር በላ የሚል ነው መልስ

እዚህ አገር ሲያመጡኝ የተወሰነች ነገር ከመስጊዱ እርሻ ከምትገኘው ሊከፍሉኝ ሙሉ ቀን ላቀራ ነበር

ግን አህባሽ የመስጊዱን ኮሚቴ ከሶ የመስጊዱ ገቢ ለማንም እንዳይሷረፍ ሲታገድ ጧትና ማታ ብቻ እያቀራሁ ቀን ቀን ሪዝቅ ለመፈለግ መንቀሳቀስ ጀመርኩ

በዚህ መሃል ከወጣቱ ጋር ሹራ አርገን እርዳታ እንጠይቅና አንድ ኡስታዝ አምጥተን ሙሉ ቀን ይቀራ ተባባልን ወጣቱ እኔው ቁጭ ብዬ እንዳቀራ ቢፈልጉም እኔ ግን ሌላ ኡስታዝ መምጣት አለበት የሚለውን አተኮርኩና ዛሬ ኮምቦልቻ ኢማም የሆነውን ወንድም ኡስታዝ አህመድን አመጣሁላቸው

የግሩፑንም አካውንት በወንድም ኢስማኢል አራጋውና በወንድም ኡመር ሰይድ እንድከፈት አደረኩ ተከፈተም

ከሀምሳ ሺ ያነሰ ገባ ኡስታዙም ድሮ የነበራቸው ሰዎች ሲጨቀጭቁትና ልጆቼም ሙቀት ለምደው አልተመቻቸውም ብሎ አውፍ በሉኝ ብሎ ሄደ

ከዚያ ቀሪ ብሩ ሲፀና ወደ 29 ሺ ገደማ እንዳለ ታወቀ በዚያች ብር ቁርኣን አቅሪ የለንምና ለሱ መነሻ ደሞዝ ትሁነን ተብሎ እየተፈለገ ነው እንደውም ባለፈው ከነ ሸ አብደሰላም መስጊድ አንድ ልጅ ተገኝቶ በሆነ ኬዝ ሳይሳካ ቀርቷል አሁንም እየፈልግን ነው ያችን ብር ለመነሻ አስበን

ውሸት ⑤

አል ኢህሳን መርከዝ ብለ ከፈቶ የሚል ነው መልስ

አል ኢህሳንን ያመቻቸሁት እኔ አይደለሁም አመታቶችን አስቆጥሯል ይሁን እንጂ አብዛኞቹ መሪዎች ኢኽዋኖች ስለነበሩ ዋና ማናጀሩ ግን ስለፊያን እየተረዳ ሲመጣ ከጎኑ ሁነን እንድናግዘውና የሰለፊያ ተቋም እንድሆን ጥሪ አቅርቦልናል

እኛም ግራ ቀኝ በማየት ቡዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩብንም እሺ ብለን ሸይኽ ሙሀመድ መኪንን ይዘን ሀሳቡን ተጋርተን ተቀላቅለናል

ከዚያም ተሀድሶ ለማድረግ የንያ ፕሮግራም በላይቭ አካሂደናል

አካውንቱንም በወንድም አቡ ረይስ በወንድ አቡ ሂበቲላህ በወንድም ሶላሀድን ከፍተናል

እንደተባለውም የክረምት ኮርስ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነን ታዲያ የቱ ላይ ነው ጥፋቱ??

የመጨረሻ ማሳስበው ወሏሂ በውሸት ነገር መለጠፍ ሰውን ከመግደል አይተናነስም ከዚህ ቡሃላ የፈለጉትን ቢሉ መልስ አልሰጥም ምን አልባት ይህንኑ ሀሳቤን አንብበው ለማይረዱ ወገኖች በድምፅ ልገልፀው እችላለሁ።

አቡ ሀኒፋ ላይ አንድት ሴት አስገድዶ ሊደፍረኝ ብላ ካወራች ቡሃላ ሌላ ጊዜ ሰዎች በይ ስላሉኝ እንጂ አልደረሰብኝም እንዳለችው ሴት ለኔ ትልቅ ፈተና ቢሆንም ሞተን እንገናኛለን ባደባባዩ ሜዳ እድሜ ለሞት ሁሉም እዚያ ይገለፃል።

t.me/abumuazhusenedris