2022-07-11 00:15:45
አሰላም ዐለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱ ውድ የኢስላም ልጆች ኢንሻ አሏህ የተንቢሀት ሙስሊም (ሴቶችን የሚመለከቱ ህግጋቶች) የሚለው ተከታታይ ፅሁፍ ከባለፈው የቀጠለ ይዤላችሁ መጥቻለው ጠቃሚ እውቀትን እንዲሰጠን ጌታዬን እለምነዋለሁ።
(=================)
በሌሎችም የሴት ልጅ ውርስን አስመልክቶ በወረዱ የቁርአን አንቀፆች ሴት እናት፣ልጅ፣እህትና ሚስት ስትሆን የመውረስ መብቷ ተጠብቋል በትዳር መስክም አንድ ወንድ እስከ አራት ሚስቶችን ብቻ ማግባት እንደሚችል ከፍ ያለው አላህ ገደብ ጥሎበታል፤፡ይህም አቅም በሚፈቅደው ያህል ሚስቶቹን በእኩልነት ማሳደር የሚችል ከሆነ ብቻ ነው፤ ሚስቱን/ቶቹን በመልካም እንዲይዝም ግዴታ ተደርጎበታል። ከፍ ያለው አላህ እንዲሆ ይላል፡
<<…
በመልካም ተኗኗሯቸው……>> አን-ኒሳእ :19 የመህር ገንዘብ ማግኘትንም ከፍ ያለው አላህ የሴት ልጅ መብት አድርጓል፣ ደስ እያላት ካልፈቀደች በስተቀር ምንም ሳይጓደል በሙሉ እንዲሰጣትም አዟል፣ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፡
<<
ሴቶችንም መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፤ ለናንተም ከርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾኑ ብሉት።>>አን - ኒሳእ፡4በተጨማሪም ሴት ልጅ በባሏ ቤት አዛዥና የልጆቿ ተቆጣጣሪ አድርጓታል፣ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡
<<
ሴት በባሏ ቤት ኃላፊ ነች፣ ከኃላፊነቷም ተጠያቂ ነች ፡፡>>
ባል የሚስቱን አስፈላጊ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታም ተጥሎበታል።
የእስልምና ጠላቶች የሴትን ልጅ ክብርለመግፈፍ ያላቸው ፍላጎትከሓዲያን፣መናፍቃንና የስሜት በሽታ የተጠናወታቸው የዘመናችን የእስልምና ብሎም የሰው ልጅ ጠላቶች ሴት ልጅ በእስልምና አስተምህሮት ያገኘችው ክብርና ልዩ ጥበቃ አስቆጭቷቸዋል።
ምክንያቱም እነዚህ ከሓዲያን ፣መንፍቃንና በልባቸው የስሜት በሽታ ያለባቸው ብልሹዎች የሴት ልጅን ገላ ያለ አግባብ በመጠቀም የተቀጣጠለ ስሜታቸውን ካረኩ በኋላ ሴትን ልጅ እንደ ጥፋት መሣሪያ በመጠቀም እምነተ-ደካማና በስሜት የተወጠሩ ሰዎችን ለማጥመድ ስለሚፈልጉ ነው፤ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላላል፦
"አላህም በናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል። እንዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት( ከእውነት)ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ።"አን-ኒሳእ፡27
ይቀጥላል
HD
ወደ ቻናሉ
==
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
629 views21:15