Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.26K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2022-11-02 18:51:06 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጎፋ ሳውላ ስለሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ምን አሉ?

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ አቀባበል ለማድረግ ለተሰባሰቡ የከተማይቱ ነዋሪዎች ንግግር አሰምተዋል፡፡ በዚሁ ንግግራቸው በስም ያልጠቀሷቸው አገራትና ተቋማት በሰው ልጆች መብት አጠባበቅ ላይ ያቀርባሉ ያሏቸውን ክሶች አጣጥለዋል።

‹‹ አንዳንድ አገራት የሰው ልጅ መብት መከበር አለበት ›› የሚሉ ወቀሳና ክሶች ይቀርባሉ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ‹‹ ለእነኝህ ወዳጆቼ ያለኝ መልዕክት መጥታችሁ በጎፋና አካባቢው የሚገኘውን የማዜ ፓርክን ተመልከቱ። እኛ ኢትዮጲያን የሰው ልጆች መብት ቀርቶ የዝሆንና የአንበሳ መብቶችን የምንጠብቅ ሰዎች ነን ›› በማለት በሳውላ ከተማ ስታዲየም ለተሰበሰቡ ተዳሚዎች ንግግራቸውን አሰምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በደቡባዊ የአገሪቱ ክልል የሚጎበኙት መንግሥታቸው ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ጋር እያካሄደ በሚገኘው ጦርነት ዋና ዋና የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን እየገለፁ ባለበት ወቅት ነው፡፡ በጦርነት የተገኘውን ድል በሰላም መድገም አለብን የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳውላ ንግግር መንግሥታቸው በጦርነቱ የበላይነቱን እየያዘ ስለመምጣቱ ይበልጥ ያረጋገጡበት ይመስላል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚሁ ንግግራቸው ‹‹ከእናንተ ጋር ሆነን በጦርነት ያገኘነውን ድል በሰላም መድገም ይኖርብናል፡፡ በጦርነት የተገኘ ድል በሰላም ፣ በሰላም የተገኘ ድል ደግሞ በብልፅግና ካልተደገመ የኢትዮጲያ ህልውና በአንድ ወይም በሌላ መልኩ መደፈሩ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በአንዱ ድል ሳንኩራራ በጦርነት ያገኘነውን ድል በሰላም በመድገም የማትደፈር ፣ የተከበረችና ለልጆቿ ምቹ የሆነች ኢትዮጲያን በጋራ እንድንፈጥር አደራ እላለሁ ›› ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እየተጎበኘ የሚገኘው የደቡብ ክልል በመዋቅር አደረጃጀት ፣ በወሰን ይገባኛልና የማንነት ጥያቄዎችን መሠረት ያደረጉና ሄድ መለስ የሚሉ ግጭቶች የሚስተዋሉበት ነው፡፡

ያም ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አካባቢው ያለውን የመልማት እድል ከመጥቀስ ባለፈ በክልል የአደረጃጀት ጥያቄም ሆነ በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ያሉት ነገር የለም፡፡

የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር እንድምታ የፖለቲካ ሳይንስ አጥኚውና የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን የሥራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ደያሞ ዳሌ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለ ሰብአዊ መብት አያያዝ ያደረጉት ንግግር የራሱ እንድምታ አለው ይላሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንና በሰብአዊ መብት ተቋማት ሥም የሚወጡት መግለጫዎች የማሸማቀቅና የማስጨነቅ ዘመቻ አይነት ባህሪ አላቸው፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው አነኝህ መግለጫዎች ተጨባጭ ሁኔታዎችን የሚገልጹ እንዳልሆኑ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ አኛ ሰብአዊ መብት የመጣስ ባህሪያችንና ባህላችን አይፈቅድልንም። ትክክለኛ ባህሪያችን እንደውም ለእንሰሳት ጭምር ማዘንና መብታቸውን ማክበር ነው የሚል መልዕክት ያስተላለፉበት ነው ›› ብለዋል ‹‹በጦርነት የተገኘውን ድል በሰላምም መድገም›› በሚል የጠቀሱት ሀሳብ የመንግስታቸውን ቀጣይ አቅጣጫ የሚያመላክት መሆኑን አቶ ደያሞ ተናግረዋል፡፡

‹‹ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጦርነት ድል አድረገናል የሚሉት የፌዴራሉ ምንግሥት ቀደምሲል በአፋርና በአማራ ክልሎች በትግራይ ተዋጊዎች ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን ከማስለቀቁም በላይ ትግራይ ክልል ውስጥ ተጨማሪ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡ በንግግራቸው ማሳየት የፈለጉት ባሸነፉባቸው የትግራይ አካባቢዎችም ሆነ በተቀሩት የኢትዮጲያ አካባቢዎች ሰላም መስፈን አንዳለበት የጠቆሙበት ነው›› ብለዋል አቶ ደያሞ ለዶቼ ቬለ።https://wolaitatimes.com/ጠቅላይ-ሚንስትሩ-በጎፋ-ሳውላ-ስለ-ወቅታዊ/
3.6K viewsNatnael Gecho, 15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 13:58:51 “በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት ወደ መቋጫ እየተቃረበ በመሆኑ በጦርነቱ ያሳየነው ድል በሠላም እንዲደገም መስራት ይኖርብናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የጎፋ ዞን ጉብኝት አድርገዋል። ተጨማሪ ያንብቡ
https://wolaitatimes.com/ጦርነቱ-ወደ-መቋጫ-እየተቃረበ-በመሆኑ-በጦ/
4.9K viewsNatnael Gecho, 10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 06:02:20
6.4K viewsAnteneh Babanto, 03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 05:59:34 Channel photo updated
02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 20:36:05 በትግራይ ክልል ያሉ ባንኮች አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት ኦዲት መደረግ እንዳለባቸው ተገለፀ

የፌዴራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው የትግራይ ክልል ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ባንኮች አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት፣ በክልሉ የሚገኙ ቅርንጫፎቻቸውን ኦዲት ማድረግ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

የፌዴራል መንግሥት ዳግም በተቆጣጠራቸው ሽሬ፣ ኮረምና አላማጣ ከተሞችን መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን ይታወቃል፡፡

ከእነዚህ መሠረታዊ አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን የባንክ አገልግሎት የመጀመር ጉዳይ በአካባቢው ሰላም መረጋገጥና የባንኮቹ አገልግሎት ለመጀመር የሚያሳልፉት ውሳኔ ላይ እንደሚመሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡

በባንኩ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ "ሥራ ሲጀመር ጦርነቱ ምን ያህል ውድመት አድርሷል? በቅርንጫፉ ላይ ምን አለን? ምን የለንም? የሚለውን ኦዲት ካደረጉ በኋላ ነው የሚጀምሩት" ሲሉ ባንኮቹ ቀጥታ አገልግሎት ወደ መስጠት እንደማይገቡ አስረድተዋል፡፡

እንደ ምክትል ገዥው ገለጻ፤ ብሔራዊ ባንክ ተቋማቱ በቶሎ ወደ ክልሉ በመግባት አገልግሎት እንዲሰጡ ፍላጎት ያለው ቢሆንም ተቋማቸው ስለሚገባበት “የአደጋ ሥጋት” ውሳኔ የሚያሳልፉት ባንኮቹ ራሳቸው ናቸው፡፡

ባንኮቹ በአካባቢዎቹ ላይ ሥራ ለመጀመር ያላቸው አቅም፣ የኦዲት ሥራውን ለማከናወን ያላቸው ዝግጅት፣ እንዲሁም የአካባቢዎቹ ደኅንነት አገልግሎት የመጀመር ሁኔታን የሚወስኑ ጉዳዮች እንደሆኑ ምክትል ገዢው መግለፃቸውን #ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
6.7K viewsAnteneh Babanto, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 17:44:53 በቦክስ ስፓርት ከ62 በላይ ወርቅ ተሸላሚ የሆነች ብርቱዋ ሴት https://wolaitatimes.com/በቦክስ-ስፓርት-ከ62-በላይ-ወርቅ-ተሸላሚ-የሆ/
6.4K viewsNatnael Gecho, 14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 07:11:00
አቢይን ለምን ይጠሉታል?
https://t.me/Skyline7777
6.9K views@A, 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 00:01:17 በአሜሪካና ካናዳ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ወገኖቻችን ከዚህ በታች በተመለከቱት የስልጠና ሙያ መስኮች በመሰልጠን በርካታ ወገኖች በቀላሉ እስከ$159k አመታዊ ደሞዝ የሚያገኙበት አስተማማኝ የስራ እድሎች ያሉት ስልጠናዎች በእውቅና ስመጥር የኢትዮጵያ እና ህንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ተዘጋጅቷል።
በሳምንት በሶስት ቀናት በበይነመረብ ሰልጥነው። የሙያ ስራ ባለቤት እንዲሆኑ ከወዲሁ ይጋበዛሉ። ክፍያው እጅግ ተመጣጣኝ ነው። በቴክስት መልዕክት +12026029333 ላይ ይላኩልን። ለአንድ ኮርስ ከ15 ሰው በላይ አንቀበልም። ፈጥናችሁ በእድሉ ተጠቀሙ።

We appreciate to your references to families and friends who want to involve in trainings or do marketing with Fortech professionals

The trainings we planned to execute for next semester includes:

1. Mulesoft Developer training -

2. DBA (Database Administration) --

3. Power BI (Microsoft) -

Course will Begin - November 2022

Send us text message if you are interested
+1 202 602 9333.

We do Marketing for the following IT fields:

1. DBA

2. SharePoint

3. PowerBI

4. Mulesoft

Thanks & Regards,
8.6K viewsAnteneh Babanto, 21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 22:43:23 https://fb.watch/gphScMyaZd/
8.7K viewsAnteneh Babanto, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 17:24:24 በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት በፌደራሉ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር በዛሬው ዕለት ተጀምሯል

ዛሬ የተጀመረው የሰላም ንግግር እስከ የፊታችን እሁድ ድረስ እንደሚዘልቅ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ስሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ነግረውኛል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ቃል አቀባዩ ቪንሰንት ማግዌኛ በሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት እየተፋለሙ ያሉት ኃይሎች በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ፑምዚሌ ማላምቦ-ናኩክ እንደሚያስተባብሩት ተናግረዋል።

የሰላም ንግግሩ ፍሬ እንዲያፈራ ለአስተባባሪዎቹ መልካም ምኞታቸውን የገለፁት ቃል አቀባዩ፤ “የድርድሩ ውጤት ለመላው ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ሰላም እንዲያመጣ ደቡብ አፍሪካ ምኞቷን ትገልጻለች” ብለዋል።

ከተጀመረ ሁለት ዓመት ሊሞላው ቀናት የቀሩትን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለመቋጨት፤ ይህ በፕሪቶሪያ የሚካሄደው የሰላም ንግግር የመጀመሪያው ይፋዊ የንግግር መድረክ ሲሆን፤ የውይይቱ በሰላም መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ወሳኝ መሆኑ እየተነገረ ያገኛል።

በዚህ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍም የፌደራል መንግሥት እና በህወሓት ተወካዮች ትናንት እና ከትናንት በስቲያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ይታወሳል። ተጨማሪ ዝርዝር ዘገባ ከታች በተቀመጠው WT Official Website ያንብቡ
https://wolaitatimes.com/በፌደራሉ-መንግስት-እና-በህወሓት-መካከል/
10.3K viewsNatnael Gecho, 14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ