Get Mystery Box with random crypto!

Sheger Press️️

የሰርጥ አድራሻ: @sheger_press
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.08K
የሰርጥ መግለጫ

Official channel of sheger press
If you want to give a suggestion or comment, contact us 👉 @birukepromo

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-01-07 19:22:01 እንድታውቁት

ከቦሌ - በኦሎምፒያ - መስቀል አደባባይ - ብሔራዊ ቤተ -መንግሥት  እንዲሁም አራት ኪሎ በሁለቱም አቅጣጫ ከነገ ታህሳስ 29/2016 ጀምሮ ሞተር ሳይክሎችና ከሁለት ቶን በላይ የሆኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንደማይችሉ  የአዲስ አበባ ፖሊስ  አሳስቧል።

በመንግዶቹ ክልከላውን የሚገልፁ ምልክቶች መተከላቸውን ያስታወቀው ፖሊስ የተላለፈውን መልዕክት በማያከብሩ  አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ  እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
12.6K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-07 12:50:18 መረጃ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሰሞኑ ውዝግብ ካስነሳው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የወደብ እና የባህር በር መውጫ የመግባበቢያ ስምምነት በፊት ከኤርትራ ጋር በአራት አመራጮች ውይይቶች ሲደረጉ የነበረ መሆኑን አስታወቁ፡፡

አምባሰደር ሬድዋን ሁሴን በዚሁ ማብራሪያቸውም፤ ወደብ አጠቃቀመንን በተመለከተ ኢትዮጵያ ለኤርትራ አራት የመጠቀሚያ አመራጮን አቅርባ በዚህም  ነገሮች በሂደት ላይ ነበሩ ሲሉም አስታውቀዋል፡፡

አምበሳደር ሬድዋን ሁሴን ከኤርትራ ጋር የተጀመረው የወደብ አጠቃቀም ጅማሮ  እና እንቅስቃሴ ለምን መሀል ላይ ተቀርቅሮ እንደቀረ ግን ያሉት ነገር የለም፡፡ 

ሰሞኑን ከተፈጠረው ቀጠናዊ ትኩሳት ጋር በተያያዘ ሁኔታውን አስመልክቶ  አልጀዚራ በሰራው አንድ ዘገባ ውስጥ አስተያየታቸው እንዲካት የተደረጉት መቀመጫቸውን በኦስሎ ያደረጉት  ደራሲ እና  ተመራማሪ የሆኑት ሞሀመድ ኬር ኦማር፤ “ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በወደብ ጉዳይ ጀምረውት የነበረው እንቅስቃሴ እንዲቆም ያደረገው በፌደራሉ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የፕሪቶሪያው ስምምነት ነው፡፡ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
13.4K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-06 20:18:00
<< ዱላ በዝቶብናል >> - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ << እኛ እየደረሰብን ያለው ዱላ ብዙ ነው >> ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በአዲስ አበባ ከተማ < አዋሬ አካባቢ በ1523.3 ሜትር ካሬ ላይ የተገነባውን ተጨማሪ የአነስተኛ ወጪ ቤቶች ግንባታ > በመረቁበት ወቅት ነው።

ጠ/ሚንስትሩ መንግስታቸው ላይ በርካታ ጫና እየደረሰበት ስለመሆኑ ባመላከቱበት በዚህ መልዕክታቸው፤ ጫናው ግን ከስራ እንደማያግዳቸው አፅዕኖት ሰጥተው አሰገንዝበዋል።

<< ይህን ሁሉ ዱላ ተቋቁመን በነፃነት፤ እንደከዚህ ቀደም መሪዎች ተደብቀን አይደለም፤ በነፃነት እየዞርን እንድንሰራ ያደረገን የእናንተ ፀሎት ነው >> ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ << ይሄ ይቀጥላል፤ የሚቆም ነገር የለም፤ እንሰራለን >> ሲሉ አረጋግጠዋል።

አክለውም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ንግግሮቻቸው እንደሚሉት ሁሉ << ኢትዮጵያን እንቀይራለን፤ ኢትዮጵያን እናበለፅጋለን >> ሲሉ ተደምጠዋል።

በእርሳቸው የሚመራው መንግስት የሚያከናውነውን ተግባር በተመለከተ በሰጡት አስተያየት < ሕዝቡ በምልዓት እየተረዳቸው አለመሆኑን > አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ << ሕዝቦቿ አንዳንዶች ዛሬ፤ አንዳንዶቹ ነገ፤ አንዳንዶች ከነገ ወዲያ ይረዱ ይሆናል >> በማለት << እኛ [ግን] አናቋርጥም ስራችንን >> ሲሉ ተናግረዋል።

በዛሬው መርሐ ግብር የተመረቁት ሁለቱ ባለ 11 ወለል ህንፃዎች በሶስት ወራት ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁ መሆናቸውን የጠ/ሚ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

@sheger_press
@sheger_press
14.0K viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-14 14:18:18
የአቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲለቁ መታዘዛቸውን ተናገሩ!

መንግሥትን ለመጣል ከሚንቀሳቀስ አማጺ ቡድን ጋር በማሴር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ፣ ቤተሰቦች ከሚኖሩበት የመንግሥት ቤት እንዲለቁ መታዘዛቸውን ተናገሩ፡፡


አቶ ታዬ ባለፈው ሰኞ ምሽት በፀጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ተይዘው መወሰዳቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ፤ ማክሰኞ ጠዋት የመንግሥት ቤቶችን ከሚያስተዳድረው ተቋም፣ አስከ ሐሙስ ድረስ ቤቱን ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን ገልጸዋል።

የገዢው ፓርቲ ብልጽግና ከፍተኛ አባልና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት እንደራሴ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ፤ ባለፉት ጥቂት ወራት በግል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸውና በመገናኛ ብዙኃን ላይ ሲያንጸባርቁ በሰነበቷቸው መንግስትን የሚኮንኑና የሚቃረኑ አስተያየቶች ሳቢያ መነጋገሪያ ሆነው ነበር።

ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ስለተካሄደው ድርድር መክሸፍ፣ ስለሙስና፣ በኦሮሚያ ክልል ስላለው ግጭትና አዲስ አበባ ውስጥ ሊካሄድ ታቅዶ በተከለከለው ሰላማዊ ሰልፍ ዙሪያ መንግሥትን የሚተች ጠንካራ አቋም ማንጸባረቃቸውን ተከትሎ፣በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በጠ/ሚኒስትር ዐቢይ በተጻፈ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው መባረራቸው ይታወቃል።

@sheger_press
@sheger_press
12.7K viewsedited  11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-13 19:16:22
ህዝብን ሲያማርሩ የነበሩ ሿሿ የሚስሩ ሌቦች ተይዘዋል

ብስራት ገብርኤል አካባቢ በሞተር ሳይክል ስልኩን ነጥቀው ሲያመልጡ በህዝቡ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ህዝቡም እልል ብሎ እሽት አድርጎ ለፖሊስ አስረክቧቸዋል::ሌባ ስታገኙ ለፖሊስ ከማስረከባችሁ በፊት ትንሽ እሽት ማድረግ ግድ ይላል::

ሌብነትን ተፀየፉ

@sheger_press
@sheger_press
12.8K viewsedited  16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 16:17:55
ውጤት በተመለከተ

አሁንም አብዛኞች ውጤታቸውን ለማየት ተቸግረዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ምንም አይነት የሲስተም / ቴክኒካል ችግር የለም " ያለ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ዌብሳይቱም ይሁን የቴሌግራም ቦቱ በትክክል እየሰሩ አይደለም።

በዚህም የተነሳ በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች እንደተቸገሩ እንደሆነ ተመልክተናል።

ባፋጣኝ ቢስተካከል ባዮች ነን።

@sheger_press
@sheger_press
12.7K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 11:26:17
Hanan Naji

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በአዲስ አበባ  ተመዘገበ!

የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማረ የሆነችው ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡

የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ከ700 በማምጣት የተመዘገበ ሲሆን ፡በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 ከ600 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

ከተፈጥር ሳይንስ ተፈታኞች ውጥስ 205 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 15 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
13.3K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ