Get Mystery Box with random crypto!

ከደቡብ ሱዳን ተሻግረዉ ወደ ጋምቤላ ክልል የመጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የሙርሌ ታጣቂዎችን ወደመጡበ | Sheger Press️️

ከደቡብ ሱዳን ተሻግረዉ ወደ ጋምቤላ ክልል የመጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የሙርሌ ታጣቂዎችን ወደመጡበት መመለስ ቢቻልም አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ይገኛሉ ተባለ

ከደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰዉ በመግባት በተከታታይ ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩት የሙርሌ ታጣቂዎች ከሰሞኑ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ጥቃት ፈጽመዉ እንደነበር ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ታጣቂዎቹ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጥቃቱን ፈጽመዋል የተባለ ሲሆን አሁንም በወረዳዉ ሁለት ቀበሌያት ላይ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ስማቸዉን የማንጠቅሳቸዉ የወረዳዉ አንድ ባለስልጣን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ በአኩላ እና አቻኛ ቀበሌዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በተለይም አኩላ በተሰኘዉ ቀበሌ በጸጥታ ሀይሎች ቅኝት እና ክትትል እየተረገ ነዉ ብለዉናል። አንዳንዶቹም በዚህ ክትትል ከመሸጉበት በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሯል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰዉ መግባታቸው ከተሰማ በኋላ እንዲመለሱ ቢደረግም አሁንም በሁለቱ ቀበሌያት እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ከደቡብ ሱዳን የሚሻገሩ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀዉ በመግባት በተለይም የዲማ ወረዳን ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ጥቃቶችን ፣ እገታ እና የእንስሳት ዘረፋ ሲፈጽሙ እንደነበር ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል።

@sheger_press
@sheger_press