Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ relationship4christ — ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ relationship4christ — ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ
የሰርጥ አድራሻ: @relationship4christ
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.90K
የሰርጥ መግለጫ

፦ እንዴት relationship ን ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር እናስኪድ💏💏
💑ተከታታይ ጾታዊ ትምህርቶች
💑ማንን ላግባ?
💑 እንዴት r/ship በቅድስና እንያዝ
💑 pornography እና ሴጋ ጉዳቶቹ
በሌሎችም ወሳኝ ርዕሶች ላይ እንማማራለን
for any comment
@edbornagain

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 15:15:52 ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ያድናል።

አንድ አጭር ታርክ ላጋራችሁ። ታርኩ ምናልባት ይጠቅማችሁ ይሆናልና፣ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም የሚጠቅማችሁን አጋራቹዋለሁ።
ባለታርኳ የዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ ስትሆን ዩኒቨርሲቲ አንደኛ አመት ተማሪ እያለች ከአንድ ተማሪ ጋር ፍቅር ይጀምራሉ። ብዙም ሳይቆዩ ከሁለተኛ አመት ጀምሮ ከግብ ውጭ ቤት ተከራይቶ አብሮ መኖር ይጀምራሉ፣ በእርግዝና መከላከያ መድሃንቶች ብዙ ብቆዩም መጨረሻ አከባብ በትንሽ ስህተት እርግዝና ይፈጠራል። እረፍት ወደቤት ስትመለስም ብዙም ስላላስነቃ የውሸት ባሏም እየደወለ ያበረታት ስለነበር ብዙም ሳትጨነቅ ክረምቱን አሰለፈች ለሶስተኛ አመት ትምህርቷ ግብ ስትመለስ ለ3 ወር የቀረበ እርግዝና ተሸክማ ነበር። እንደበፍቱ ቤት ተከራይቶ አስበዛ እየገዙ ለመኖር አስባ የነበረ ብሆንም ልጁ አልተስማም፣ እርግዝናውም ግልጽ እየሆነ ስመጣ ሊያገኛትም ማፈር ጀመረ። እየደወለች ብትጨቀጭቀውም ሊያገኛት አልፈለገም። በጣም ብዙ እየተጨነቀች ትምርቷንም አምና ወዝድሮ ሞልታ እያለች ያው መወለዱ አይቀርምና የትንሳኤ በአል አከባብ ወንድ ልጅ ተገላገለች።
ይህንን የሰሙ በተሰቦቹዋም ጠሏት፣ መደወልም ሆነ ገንዘብ መላክ አቆሙ።
ህጻን ይዞ ዶርም መቆየት አትችልምና አንድወር ያኽል ዶርም ተደብቃ ከኖረች በኋላ ጓደኞቿ ተባብሮ ቤት ተከራይቶ አስወጧት። እና ከባድ ሕይወት ከግብ ውጭ መጋፈጥ ጀመረች። አንዳንድ መልካም ተማሪዎች ሴት መምህራንን አስተባብሮ ገንዘብ በየወሩ እያዋጡ ይደግሟት ጀመሩ።
እንድህ አቃልዬ አወራሁት እንጅ ላይፏ እጅግ በጣም አሰቃቅ እና ከባድ ሕይወት እያሳለፈች ህጻኑን ያለአባት፣ ትምህርቷን ያለወላጅ እገዛ እየኖረች ትገኛለች።
እናም ትላለች ሴቶች ዩኒቨርሲቲ ሆነው የፍቅር ጓደኛ በፍጹም መያዝ የለባቸውም፣ ምናልባት ከያዙም ሰማይ ምድር ብሆን እንኳን ዝሙት መጀመር ይለባቸውም። ለሁሉም ጊዜ አለው ለመማርም፣ ለማግባትም፣ ለመውለድም፣ ለመዳርም ለመሞትም ወዘተረፈ።

@relationship4christ
269 viewsEphron Milikias, 12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:01:12 “ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል ክፉም በጎም ልንመልስልህ አንችልም።”
— ዘፍጥረት 24፥50
Wow በጣም በምገርም ሁኔታ ጋብቻ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው በፍጹም በሰው ስጦታ ወይም ችሎታ አይሆንም።
የእግዚአብሔር ሃሳብ የነበረው:-
አንደኛ አብርሃም ሎሌውም "ከዘመዶቼ" ማለቱ የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው። ስለዚህ ክርሰቲያን እህቶች እና ወንድሞች ክርስቲያን ካልሆነ ሰው ጋር እግዚአብሔር አልፈቀደምና ተጠንቀቁ።
ሁለተኛ ክብር ባለው መንገድ የበተሰብ ይሁንታ መጠየቅ የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው። በአገራችም ባህል ይሁን በሌላ ብቻ በተለያዩ መንገዶች የበተሰብሽን ክብር የማይጠብቅ ይሁንታቸውን ሊጠይቅ የማይፈልግ የትዳር አጋርሽ/ህ ሊሆን አይችልምና ተጠንቀቁ።
ትዳር ከእግዚአብሔር ሲሆን የበረከት እና የመጽናናት ምንጭ ይሆናል።

@relationship4christ
320 viewsEphron Milikias, edited  05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:55:50 የሁለተኛ ዙር ውድድር ውጤት እንደሚቀጥለው ነው።
1ኛ . ---> 13+17+19=49
2ኛ Mili ---> 25+13=38
2ኛ Abush. ---> 21+17=38
ሁሉም ተሳታፊዎች የሶስተኛው ሽልማት በቀደመ ያገኙታል ማለት ነው።
341 viewsEphron Milikias, 19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:28:56 quiz 4 (2nd ሐሙስ) https://t.me/c/1778042024/873
189 viewsEphron Milikias, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:45:15 quiz 4 (2nd ሐሙስ)
https://t.me/c/1778042024/873
319 viewsEphron Milikias, edited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:14:46 የጌታ መምጣት በድንገት ይሆናል።
ዛሬ ወጣ ያለ ነገር ላውራችሁ፣

ዘመናችን በጣም ለጌታ ዳግም ምጽአት የቀረበ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። በትንሹ በቴለግራም ብቻ በጣም ብዙ መንፈሳዊ እና እጅግ ጠቃሚ groups and channels ተከፍቷል። በቃ በጣም በምገርም ሁኔታ ብዙዎች ትውልድን ለማትረፍ እየተረባረቡ ይገኛሉ።
ከምን ለማትረፍ ነው ግን??? ተመልከቱ ወዳጆቼ የጌታችን የኢየሱስ መመለስ ታላቁ ተስፋችን ብሆንም ካልተዘጋጀን እና ካልተጠነቀቅን ለብዙዎች መጥፍያቸው ይሆናል። በኖኅ ዘመን እንደሆነ ሰዎች በአለም ስረባረቡ እንመለከታለን። ለክፋት እንኳን ለዝሙት፣ ለመዳራት፣ ለውሸት እና ለተለያዩ ክፋቶች መረባረብ ይታያል። ታድያ በኖኀ ዘመን 120 አመት ተመሳሳይ ስብከት ተሰብኮ ከሰሙ እና ከታዘዙ ከስምንት ሰው በላይ እንዳልዳነ በዚህም ዘመን ጌታችን አለም ባልነቃበት ሁኔታ በድንገት ይመጣል።
አንተ/አንች ከየተኛው ወገን ነህ/ነሽ? ከተዘናጉ ወይስ ራስን ለጌታ ክብር ለማብቃት ከምረባረቡ ነዎት? ይህንን ቻናል እንኳን ሰው ብዙም join ለማድረግ ይቸገራሉ፣ መልካም ነገር እያለውም ብዙዎቹ left ያደረጉታል። እጅግ የተወደዳችሁ ጌታ በድንገት ይመጣል፣ በኖኅ ዘመን እንደሆነ የጥፋት ውኃ ከመጣ፣ ጊዜው ካበቃ በኋላ እንደተረዱት እንዳንሆን እንጠንቀቅ።
ማቴ ምዕራፍ 24 በጌታ ፍቅር በጥሞና እየተረዳችሁት አንብቡ።
ጌታችን በድንገት ይመጣል። ለብዘዎች የዘገየ ብመስል እንኳን መምጣቱ አይቀርም።
ከምነጠቁት፣ ምድር ላይ ለመከራ፣ ለጥፋት ከማይቀሩት እንዲንሆን፣ በሁሉም መንገድ በተሌግራም፣ በfb በሌሎችም ምድያዎች መንፈሳዊ ነገር እንከታተል፣ መጽሐፍ ቅዱስን እናንብብ፣ በጸሎት እንበርታ። ጌታ ኢየሱስ ተቀብላችሁ የእግዚአብሔር ወገን ያልሆናችሁ እናንተም ጌታን በመቀበል ወደመርከቡ ግቡ። መርከባችን ኢየሱስ ነው። ተባረኩ።

አስተያየታችሁን you can write in comment box
And join us:
@relationship4christ
453 viewsEphron Milikias, edited  05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 22:23:46 ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ pinned «ሰላም የተወደዳችሁ የዚህ ቻናል አባላት: አስደሳች ዜና ይዘንላችሁ መጥተናል!!! ይህም ሳምንቱን ሙሉ በተመሳሳይ ሰአት አብረን በተለያዩ ርዕስ ወደ ጌታ ፊት የምንቀርብ ይሆናል። ዋና አላማው አንድና አንድ ጸሎትን ያነገበ ሲሆን፣ ስለ ትዳር፣ ስለስራ እንጸልያለን። ስለ ቤተሰብ፣ አከባቢዎቻችን፣ ስለ ሀገራችን፣ ሌሎችንም ርዕሶች በመጋራት የምንጸልይበት ጊዜ ይኖረናል። ስለ ጸሎቱ ሂደት ከታች ባለው…»
19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:34:56 Quiz ማክሰኞ 2

https://t.me/c/1778042024/860
449 viewsEphron Milikias, edited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 04:46:57 ትናንተ ተሳስተህ/ሽ ሊሆን ይችላል፣ በሕይወት እስካለህ ግን አሁንም ሌላ ብሩህ እድል አለክ።
ዛሬንም እንዳታባክነው ተጠንቀቅ፣ ለመጸለይ፣ ለመቀደስ፣ ለስኬት ለመሄድ፣ ለመመስከር ጊዜው አሁን ነው።
537 viewsEphron Milikias, 01:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 19:24:00 #ንጽህና_ከጸሎት_ይበልጣል!

አንድ በቅርበት የማውቀው ወጣት አገልጋይ አለ ይህ ልጅ አባቱም አገልጋይ ናቸው። ልጁ በተደጋጋሚ ሲጸልይ ያዩታል። አንድ ቀን ልጃቸውን "ጸሎት ብቻ አታብዛ ህይወትህ ንጹህ እንዲሆን ትጋ" እንዳሉት አጫውቶኛል። በጸሎት ንጽህና እንደሚጠበቅ አምናለሁ። ከዛ በላይ ግን አኪያሄድን እንደ እግዚአብሔር ቃል በማድረግ ይጠበቃል። በጸሎትና በመጸለይ በጣም አምናለሁ። ለግልም ለአካሉም እጅግ አስፈላጊ ነው።

  ይህ በእንዲህ እንዳለ የብዙዎች ጸሎት፣ የአንዳንዶች ይቅርታ፤ የብዙዎች ንስሃ ሳይ ጥያቄ ይፈጥርብኛል። ጸሎት በማብዛት ብቻ ህይወት አይጠራም እግዚአብሔር ራሱ የማይሰማው የጸሎት አይነትና ህይወት አለና።

    የህይወታችን ንጽህና እንደ ቃሉ ብንሰራው ይቅርታችን የእውነት፤ንስሃችን የፍሬ ፤ ፍቅራችን ያለ ማስመሰል፤ አኗኗራችን ለጌታ ቢሆን ጸሎታችን ታላቅ አቅም ይኖረዋል። "በተሳሳተ መንገድ ላይ ቆመን የምናበዛው ጸሎት ለውጥ አያመጣም።" አቋቋማችንን፤ አረማመዳችን ማጥራት ለጸሎታችን ታላቅ ሐይልን ይሰጣል።

ጸሎታችን መንገዳችንን ከማስተካከል ጋር ቢሆን፤ ይቅርታ ስንጠያየቅ ከልባችን ቢሆን፣ ንስሃ ስንገባም ከመመለስ ጋር ቢሆን ለምድሪቱ ታላቅ ለውጥ ይሆናል። ሰሞኑን ስንጸልይ አኪያሄዳችንንም እያስተካከልን ይሁን ለማለት ነው።


@relationship4christ
@relationship4christ
721 views@Born again, edited  16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ