Get Mystery Box with random crypto!

የጌታ መምጣት በድንገት ይሆናል። ዛሬ ወጣ ያለ ነገር ላውራችሁ፣ ዘመናችን | ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ

የጌታ መምጣት በድንገት ይሆናል።
ዛሬ ወጣ ያለ ነገር ላውራችሁ፣

ዘመናችን በጣም ለጌታ ዳግም ምጽአት የቀረበ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። በትንሹ በቴለግራም ብቻ በጣም ብዙ መንፈሳዊ እና እጅግ ጠቃሚ groups and channels ተከፍቷል። በቃ በጣም በምገርም ሁኔታ ብዙዎች ትውልድን ለማትረፍ እየተረባረቡ ይገኛሉ።
ከምን ለማትረፍ ነው ግን??? ተመልከቱ ወዳጆቼ የጌታችን የኢየሱስ መመለስ ታላቁ ተስፋችን ብሆንም ካልተዘጋጀን እና ካልተጠነቀቅን ለብዙዎች መጥፍያቸው ይሆናል። በኖኅ ዘመን እንደሆነ ሰዎች በአለም ስረባረቡ እንመለከታለን። ለክፋት እንኳን ለዝሙት፣ ለመዳራት፣ ለውሸት እና ለተለያዩ ክፋቶች መረባረብ ይታያል። ታድያ በኖኀ ዘመን 120 አመት ተመሳሳይ ስብከት ተሰብኮ ከሰሙ እና ከታዘዙ ከስምንት ሰው በላይ እንዳልዳነ በዚህም ዘመን ጌታችን አለም ባልነቃበት ሁኔታ በድንገት ይመጣል።
አንተ/አንች ከየተኛው ወገን ነህ/ነሽ? ከተዘናጉ ወይስ ራስን ለጌታ ክብር ለማብቃት ከምረባረቡ ነዎት? ይህንን ቻናል እንኳን ሰው ብዙም join ለማድረግ ይቸገራሉ፣ መልካም ነገር እያለውም ብዙዎቹ left ያደረጉታል። እጅግ የተወደዳችሁ ጌታ በድንገት ይመጣል፣ በኖኅ ዘመን እንደሆነ የጥፋት ውኃ ከመጣ፣ ጊዜው ካበቃ በኋላ እንደተረዱት እንዳንሆን እንጠንቀቅ።
ማቴ ምዕራፍ 24 በጌታ ፍቅር በጥሞና እየተረዳችሁት አንብቡ።
ጌታችን በድንገት ይመጣል። ለብዘዎች የዘገየ ብመስል እንኳን መምጣቱ አይቀርም።
ከምነጠቁት፣ ምድር ላይ ለመከራ፣ ለጥፋት ከማይቀሩት እንዲንሆን፣ በሁሉም መንገድ በተሌግራም፣ በfb በሌሎችም ምድያዎች መንፈሳዊ ነገር እንከታተል፣ መጽሐፍ ቅዱስን እናንብብ፣ በጸሎት እንበርታ። ጌታ ኢየሱስ ተቀብላችሁ የእግዚአብሔር ወገን ያልሆናችሁ እናንተም ጌታን በመቀበል ወደመርከቡ ግቡ። መርከባችን ኢየሱስ ነው። ተባረኩ።

አስተያየታችሁን you can write in comment box
And join us:
@relationship4christ