Get Mystery Box with random crypto!

ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ያድናል። አንድ አጭር ታርክ ላጋራችሁ። ታርኩ ምናልባት ይጠቅማችሁ ይሆ | ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ

ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ያድናል።

አንድ አጭር ታርክ ላጋራችሁ። ታርኩ ምናልባት ይጠቅማችሁ ይሆናልና፣ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም የሚጠቅማችሁን አጋራቹዋለሁ።
ባለታርኳ የዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ ስትሆን ዩኒቨርሲቲ አንደኛ አመት ተማሪ እያለች ከአንድ ተማሪ ጋር ፍቅር ይጀምራሉ። ብዙም ሳይቆዩ ከሁለተኛ አመት ጀምሮ ከግብ ውጭ ቤት ተከራይቶ አብሮ መኖር ይጀምራሉ፣ በእርግዝና መከላከያ መድሃንቶች ብዙ ብቆዩም መጨረሻ አከባብ በትንሽ ስህተት እርግዝና ይፈጠራል። እረፍት ወደቤት ስትመለስም ብዙም ስላላስነቃ የውሸት ባሏም እየደወለ ያበረታት ስለነበር ብዙም ሳትጨነቅ ክረምቱን አሰለፈች ለሶስተኛ አመት ትምህርቷ ግብ ስትመለስ ለ3 ወር የቀረበ እርግዝና ተሸክማ ነበር። እንደበፍቱ ቤት ተከራይቶ አስበዛ እየገዙ ለመኖር አስባ የነበረ ብሆንም ልጁ አልተስማም፣ እርግዝናውም ግልጽ እየሆነ ስመጣ ሊያገኛትም ማፈር ጀመረ። እየደወለች ብትጨቀጭቀውም ሊያገኛት አልፈለገም። በጣም ብዙ እየተጨነቀች ትምርቷንም አምና ወዝድሮ ሞልታ እያለች ያው መወለዱ አይቀርምና የትንሳኤ በአል አከባብ ወንድ ልጅ ተገላገለች።
ይህንን የሰሙ በተሰቦቹዋም ጠሏት፣ መደወልም ሆነ ገንዘብ መላክ አቆሙ።
ህጻን ይዞ ዶርም መቆየት አትችልምና አንድወር ያኽል ዶርም ተደብቃ ከኖረች በኋላ ጓደኞቿ ተባብሮ ቤት ተከራይቶ አስወጧት። እና ከባድ ሕይወት ከግብ ውጭ መጋፈጥ ጀመረች። አንዳንድ መልካም ተማሪዎች ሴት መምህራንን አስተባብሮ ገንዘብ በየወሩ እያዋጡ ይደግሟት ጀመሩ።
እንድህ አቃልዬ አወራሁት እንጅ ላይፏ እጅግ በጣም አሰቃቅ እና ከባድ ሕይወት እያሳለፈች ህጻኑን ያለአባት፣ ትምህርቷን ያለወላጅ እገዛ እየኖረች ትገኛለች።
እናም ትላለች ሴቶች ዩኒቨርሲቲ ሆነው የፍቅር ጓደኛ በፍጹም መያዝ የለባቸውም፣ ምናልባት ከያዙም ሰማይ ምድር ብሆን እንኳን ዝሙት መጀመር ይለባቸውም። ለሁሉም ጊዜ አለው ለመማርም፣ ለማግባትም፣ ለመውለድም፣ ለመዳርም ለመሞትም ወዘተረፈ።

@relationship4christ