Get Mystery Box with random crypto!

ጥቅስ Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ quotes_entertain — ጥቅስ Entertainment
የቴሌግራም ቻናል አርማ quotes_entertain — ጥቅስ Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @quotes_entertain
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.11K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የተለያዩ ሥነ ጥበባዊና አስተማሪ ፅሁፎች እንዲሁም ምስሎች የሚተላለፉበት ነው።
ማንኛውም እንዲተላለፍሎ የሚፈልጉትን ሥነ ጥበባዊ ስራዎች፡ #ግጥም
#ስዕል
#ወግ ...ወዘተ ይላኩልን
Creator: @zekariass20

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-07-23 21:45:28
✤Join @quotes_entertain
1.5K viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-23 21:45:07
✤Join @quotes_entertain
1.3K viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-23 17:59:44 የማይከፈት በር

ለግቶ .... ፈክቶ .... ስቆ
ሰክሮ ..... መሽቆ... ባርቆ
ተምዘግዝጎ ...... ወድቆ
ዞሮ ...... ናላ አዙሮ
በውሉደ ጌሾ ...... በጥንስስ ሰክሮ
ቤቴ ካላት ጎጆው ...... ከበር ተገትሮ
አይከፈትልህ ሲለው ለሰካራም
ግድግዳውን እንጂ በሩን አያንኳኳም።

ይስማዕከ ወርቁ

@quotes_entertain
1.4K viewsedited  14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-21 23:25:11 ኑዛዜ

ማን ነበር እንደኔ
ከየፅዋው ቀማሽ
ከጭን ሸለቆ ስር፣ የገነት ምንጭ ማሽ
አሁን እዚህ ሆኘ
ከኪሴ እያወጣሁ፣ ዘመኔን ስደምር
ከመኖር አርፌ፣ ማስታወስ ስጀምር

ከጣፋጩ ብትይ፣ ወይም ከሚመረው
ያንቺ ጣም ብቻ ነው፣ አፌ ላይ የቀረው።

በዕውቀቱ ስዩም

@quotes_entertain
3.6K viewsedited  20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-21 21:56:31 ጥያቄ

ሁሉም ሰው ሲወለድ ስለምን ያለቅሳል
ገና በጨቅላነት እንባውን ያፈሳል

ጥርጣሬ

በጠባብ ማህፀን ለእርሱ ግን በሰፋ
አድርጎት ነበረ መወለድን ተስፋ

ቢረዳ ነው እንጂ ገብቶት አንድነገር
ወይም ከባድ ምስጢር
ለኋላው ሞታችን እትብት የሚቀበር
ለካስ ቀብድ ነበር

ይህንን ሲረዳ ህፃን ልጅ ያለቅሳል
ለሚመጣው ሰግቶ እንባውን ያፈሳል
ለመወለድ ሳይሆን ለመሞት ይኖራል

Yibest Belay

@quotes_entertain
3.8K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-21 16:17:58
ዩኔስኮ ሊቨርፑል ከተማን ከዓለም ቅርስነት ሰረዘ
ጥንታዊቷ የወደብ ንግድ ከተማዋ ሊቨርፑል እ.ኤ.አ በ2004 ነበር፤ ልክ እንደ ጣሊያኗ ቬኒስ፣ እንደ ህንዱ ታጅ መሐል፣እንደ ግብጽ ፒራሚዶች ሁሉ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበችው፡፡

@quotes_entertain
3.9K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-20 11:53:07
Workneh Abebe 52 years old, have worked at #GERD as a Joyner & concrete frame work since the beginning of the Africa's biggest dam. He says "I wouldn't leave without finishing it".

@quotes_entertain
@quotes_entertain
4.9K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-19 22:37:09 " እጅ_ከፍንጅ "
-
አንዲት ባለትዳር ፥ በጓዳዋ ሳለች ፥ ጉንዳን ቆነጠጣት
ከእግር እስከ ራሷ ፥ ተርመስምሶ ገብቶ ፥ ነክሶ ፋታ አሳጣት
-
ይሄን ጊዜ ጮኸች፤
ልብሶቿን አራግፋ ፥ ራቁቷን ቀረች!
-
ጩኸቷን የሰማ ፥ ላጤ ጎረቤቷ ፥ ገባ ተንደርድሮ
ያቺን ቆንጆ እንስት ፥ እርቃኗን ሲያያት ፥ ቀረ ተገትሮ!
-
በዚህ ሁነት መሃል ፥ ሰይጣን አይኑን ሲጥል ፥ ባል ድንገት
ይደርሳል
ሰበብ የጠፋ 'ለት ፥ የጉንዳን ወረራ ፥ ትዳርን ያፈርሳል ።
---------//----------
( በርናባስ ከበደ )
@quotes_entertain
@quotes_entertain
Join & share
5.5K views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-19 14:18:35
✤Join @quotes_entertain
5.8K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-19 13:38:55
#BREAKING

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺህ በቀለ ፦

"ዛሬ ሀምሌ 12ቀን 2012ዓም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሶአል። ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ: ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ማለት ነው።

በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደህነና እንዴት እያገዘን እንደህነ መረዳት እንችላለን። ለዚሁም ምስጋና ይግባው።

እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው አመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል:: በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውውጤት ላይ እናደርሳለን።"

@quotes_entertain
5.4K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ