Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄ ሁሉም ሰው ሲወለድ ስለምን ያለቅሳል ገና በጨቅላነት እንባውን ያፈሳል ጥርጣሬ በጠባ | ጥቅስ Entertainment

ጥያቄ

ሁሉም ሰው ሲወለድ ስለምን ያለቅሳል
ገና በጨቅላነት እንባውን ያፈሳል

ጥርጣሬ

በጠባብ ማህፀን ለእርሱ ግን በሰፋ
አድርጎት ነበረ መወለድን ተስፋ

ቢረዳ ነው እንጂ ገብቶት አንድነገር
ወይም ከባድ ምስጢር
ለኋላው ሞታችን እትብት የሚቀበር
ለካስ ቀብድ ነበር

ይህንን ሲረዳ ህፃን ልጅ ያለቅሳል
ለሚመጣው ሰግቶ እንባውን ያፈሳል
ለመወለድ ሳይሆን ለመሞት ይኖራል

Yibest Belay

@quotes_entertain