Get Mystery Box with random crypto!

ኑዛዜ ማን ነበር እንደኔ ከየፅዋው ቀማሽ ከጭን ሸለቆ ስር፣ የገነት ምንጭ ማሽ አሁን እዚህ ሆኘ | ጥቅስ Entertainment

ኑዛዜ

ማን ነበር እንደኔ
ከየፅዋው ቀማሽ
ከጭን ሸለቆ ስር፣ የገነት ምንጭ ማሽ
አሁን እዚህ ሆኘ
ከኪሴ እያወጣሁ፣ ዘመኔን ስደምር
ከመኖር አርፌ፣ ማስታወስ ስጀምር

ከጣፋጩ ብትይ፣ ወይም ከሚመረው
ያንቺ ጣም ብቻ ነው፣ አፌ ላይ የቀረው።

በዕውቀቱ ስዩም

@quotes_entertain