Get Mystery Box with random crypto!

የማይከፈት በር ለግቶ .... ፈክቶ .... ስቆ ሰክሮ ..... መሽቆ... ባርቆ ተምዘግዝጎ .. | ጥቅስ Entertainment

የማይከፈት በር

ለግቶ .... ፈክቶ .... ስቆ
ሰክሮ ..... መሽቆ... ባርቆ
ተምዘግዝጎ ...... ወድቆ
ዞሮ ...... ናላ አዙሮ
በውሉደ ጌሾ ...... በጥንስስ ሰክሮ
ቤቴ ካላት ጎጆው ...... ከበር ተገትሮ
አይከፈትልህ ሲለው ለሰካራም
ግድግዳውን እንጂ በሩን አያንኳኳም።

ይስማዕከ ወርቁ

@quotes_entertain