Get Mystery Box with random crypto!

' እጅ_ከፍንጅ ' - አንዲት ባለትዳር ፥ በጓዳዋ ሳለች ፥ ጉንዳን ቆነጠጣት ከእግር እስከ ራሷ ፥ | ጥቅስ Entertainment

" እጅ_ከፍንጅ "
-
አንዲት ባለትዳር ፥ በጓዳዋ ሳለች ፥ ጉንዳን ቆነጠጣት
ከእግር እስከ ራሷ ፥ ተርመስምሶ ገብቶ ፥ ነክሶ ፋታ አሳጣት
-
ይሄን ጊዜ ጮኸች፤
ልብሶቿን አራግፋ ፥ ራቁቷን ቀረች!
-
ጩኸቷን የሰማ ፥ ላጤ ጎረቤቷ ፥ ገባ ተንደርድሮ
ያቺን ቆንጆ እንስት ፥ እርቃኗን ሲያያት ፥ ቀረ ተገትሮ!
-
በዚህ ሁነት መሃል ፥ ሰይጣን አይኑን ሲጥል ፥ ባል ድንገት
ይደርሳል
ሰበብ የጠፋ 'ለት ፥ የጉንዳን ወረራ ፥ ትዳርን ያፈርሳል ።
---------//----------
( በርናባስ ከበደ )
@quotes_entertain
@quotes_entertain
Join & share