2022-09-22 10:47:37
ትልቁ ሊያጠቃችሁ የሚችል ጥላታችሁ ማን ይመስላችሁዋል
ያ በወጣሽ በገባሽ ቁጥር ሰፈር ውሰጥ በጎሪጥ የሚያይሽ ልጅ ይሆን ያቺ ስለናንተ ክፉ የምታወራው አሽሟጣጭ ሴት ትሆን አይ በጭራሽ ሁለቱም አይደሉም!
ትልቁ ሊያጠቃችሁ የሚፈልግ ጥላታችሁ ራስ ቅላችሁ ውስጥ ነው ያለው!
አንጎል ይባላል!
አንጎላችሁ ማንበብ እንዳለባችሁ ስለሚያቅ ማህበራዊ ሚዲያን እንድትጠቀሙ ይገፋፋችኀል ፣ አንጎላችሁ ስራ ጀምራችሁ ገንዘብ ማግኘታችሁ አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ስለሚያውቅ ሙዚቃ እንድታዳምጡ ያረጋል ፤ መፀለይ እንዳለባችሁ ስለሚረዳ ፊልም እንድታዩ ያረጋችኀል!
ለዛም ነው ይህ ሁሉ ነገር ከሆነ በሁዋላ ሄዶ ሄዶ የሚቆጫችሁ! ወይኔ ባነበብኩ ኖሮ ፤ በሰራሁ ኖሮ ፣ ኖሮ...ኖሮ ...ኖሮ የሚሉ የፀፀት ደምፆች በአይምሯችሁ የሚመላለሱት!
ስለዚህ አንጎላችን ከኛ በተቃራኒ እየሰራ ነው ማለት ነው! ለምንድነው ከኛ በተቃራኒ አንጎላችን የሚሰራው!
አንጎላችንን እንደ film music junkies food and social media ያሉ ልማዶችን ያለ ምንም ልፋት እጅግ በጣም ብዙ የደስታ እና የእርካታ ኑውሮ ኬሚካል ስለሚያገኝ ፤ በቀጣይም መደገም አንዳለባቸው ይወስናል!
በተቃራኒ መልኩ ደግሞ ፤ ማንበብ ፤ ጠንክሮ መስራት ፤ ከጓደኞቻችሁ ጋር መወየየት ያሉ ተግባራቶችን ልፋት እና ድካም ያላቸው ተግባራት ስለሆኑ የሚለቁት የ ደስታ ሰጪ ኑውሮ ኬሚካል መጠን ትንሽ ስለሆነ ፤ አንጎላችን እነኚ ነገሮች የሚደገሙበትን እድል ያጠበዋል ፤ አዎን ፣ደስታ ስለማይሰጣችሁ እንድታነቡ ፤ እንድትለፉ ፤ እንድትሰሩ አይፈልግም!
ብዙ ደንበኞቼ ፣ ማንበብ ይደብረኛል ፤ መስራት ይደብረኛል እንዴት ላርግ ብለው ይጠይቁኛል!
እየደበራችሁ ማንበብ መጀመር አለባችሁ ፤ እያስጠላችሁም ቢሆን መስራት መጀመር አለባችሁ አለባችሁ ፣ አንጎላችሁን የምትገሩት በዚህ መንገድ ነው!
ሻወር መውሰድ የምትፈሩ ከሆነ ጥሩ ምሳሌ ልስጣችሁ ፣ ልክ ለመታጠብ ማሰብ ስትጀመሩ ትልቅ ፍርሀት መቶ እላያችሁ ላይ ጉብ ይላል ፣ ያንን የሚያረገው አንጎላችሁ ነው ምክንያቱም ውሃ ሲነካችሁ ያለው ስሜት የሚያንቀጠቅጥ ፣ የሚበርድ እንዲሁም የሚጎዳ እንደሆነ ይነግራችኀል ፤ እውነታው ግን ደፍራችሁ ሻውር ውስጥ ከገባችሁ በኀላ ውስጡ ለረጅም ሰዓት መቆየት መፈለጋችሁ ነው!
ልክ እንደ ሻውር ውሃ ሁሉ ንባብ ውስጥም ዘላችሁ ልትገቡ ይገባል ፣ ጥሩ ስሜት እስኪሰማችሁ አትጠብቁ ፣ ጥሩ ስሜተ እስኪሰማቸሁ እጠብቁ አንጎላችሁ እንድትለፉ አይፈልግም ፤ፊልም ፤ ወይ ሙዚቃ ወይ Social media ነው የሚፈልገው!
አንጎላችሁን መቆጣጠር ይኖርባችሗል ፤ እናንተ አንጎላችሁን መቆጣጠር ካልቻላቹ ፤ እሱን እናንተን ይቆጣጠራችሗል! አንጎላችሁ ከተቆጣጠራችሁ ደግሞ ተበላችሁ ፤ የስሜታችሁ ባሪያ ሆናችሁ ነው የምትቀሩት!
የስኬታማ ሰዎች መገለጫ እንዲህ ነው ፤ የተገራ አንጎል ነው ያላቸው! እኔ እና እናንተም እንዲህ ነው የምናድገው
ሁሌ በየቀኑ በቻLu መልዕክትች ይነቃቁ
JOIN HERE : @CHALU_A | @CHALU_A
4.2K viewsቻLu, 07:47