Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mgetem — መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mgetem — መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
የሰርጥ አድራሻ: @mgetem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.79K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
.
.
.
.
.
.
.
.
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Mgetem_Bot
@Mgetem_group

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-24 20:10:34

708 viewsㅤㅤㅤㅤㅤ, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 20:10:32 አዲስ ዘለሰኛ ዝማሬ
ዘማሪ ዲ/ን ብርሃኑ ዓለማየሁ
ምነው ሃገሬ ምነው
ግጥም: ዲ/ን ዶ/ር ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ





402 viewsㅤㅤㅤㅤㅤ, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 20:01:25

388 viewsㅤㅤㅤㅤㅤ, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 13:52:58 ግጥም በእንተ #መጻጉዕ
@Mgetem

የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምን ፈታኸኝ
እኔ እኮ ብኩን ነኝ...
አንተ ስትሰቀል ከአይሁድ ጋር የምገኝ
እኔ እኮ ምንም ነኝ ተራ የህመም ሰው
ጌታዬ እንድትምረኝ ምክንያትህ ምንድነው

በከሀሊነትህ ቢቆምም የኔ አሳር
ከደግነት ደጅህ የቆረጥኩኝ ምሳር
ብትወደኝ ብትምረኝ እኔ ምንተዳዬ
ከሰቀሉህ ጋራ ልስቀልህ ጌታዬ
እንዲ ነኝ መጻጉዕ ውለታ የምረሳ
ስወድህ እንድኖር ህመሜን አትፈውስ ቀንበሬን አታንሳ
ስንኩል ነው የኔ እግሬ ለሐሰት ያጋደለ
ጠማማ ነው ልቤ ፍቅርህን የጣለ
ቀጤማ ነው እጄ ክፋት ያቃጠለው
ያዙት ያን ክርስቶስ ብሎ የሚጠቁመው
እውር ነው ብሌኔ እያየ የሚከዳ
ከደግነት ኩሬ መአት የሚቀዳ
እዳ ነኝ ለራሴ እዳ ነኝ ለዓለም
ሲጀመር ነው የካድኩህ ሲፈጸም አይደለም
ከወንዙ ጥግ ሆኜ በአልጋዬ ላይ ሳለሁ
አምንብህ ነበረ ስትፈውስ እያየሁ
አልጋህን ተሸከም ስትለኝ ምን አልባት
ልቤን አናተበው የመራመድ ክፋት
አትማረኝ መድኅኑ በአልጋዬ ላይ ልክረም
አልጋዬን መሸከም ለኔ መጥፋት እንጂ መፈወስ አይደለም
እባክህ ክርስቶስ እባክህ ጌታዬ
አንተን ከምከዳ አልጋዬን አዝዬ
የዳዊት ልጅ ተወኝ አትፈውሰኝ ይቅር
መች እክድህ ነበር ልክ እንዲህ ከነበር ::

ዳዊት አየነው
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem
875 viewsㅤㅤㅤㅤㅤ, 10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 08:10:04 ​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ
.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9
1.4K viewsKesatebirhan, 05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 13:36:18

665 viewsㅤㅤㅤㅤㅤ, 10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 08:39:42
«ተዋሕድዋ» - ኦርቶዶክስ እና አድዋ
+++++++++++++++++++++++++++++++
ይኽ ጥናት ቀመስ አድዋዊ ጽሑፍ ከሦስት ዓመት በፊት የዳረጎት ዲጂታል መጽሔት ላይ የወጣና ዛሬ ለ127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በጸሐፊው ተተርኮ የቀረበ ነው።






241 viewsㅤㅤㅤㅤㅤ, edited  05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 19:30:33 Watch "ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል" on YouTube


750 viewsKesatebirhan, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 17:16:50 Watch " አዲስ የበገና ዝማሬ "በባሕርይ ምስጉን "በዘማሪት ሕጻን አድያም ኪሮስ" on YouTube


1 viewKesatebirhan, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 19:48:43

397 viewsㅤㅤㅤㅤㅤ, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ