Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም በእንተ #መጻጉዕ @Mgetem የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምን ፈታኸኝ እኔ እኮ ብኩን ነኝ... | መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

ግጥም በእንተ #መጻጉዕ
@Mgetem

የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምን ፈታኸኝ
እኔ እኮ ብኩን ነኝ...
አንተ ስትሰቀል ከአይሁድ ጋር የምገኝ
እኔ እኮ ምንም ነኝ ተራ የህመም ሰው
ጌታዬ እንድትምረኝ ምክንያትህ ምንድነው

በከሀሊነትህ ቢቆምም የኔ አሳር
ከደግነት ደጅህ የቆረጥኩኝ ምሳር
ብትወደኝ ብትምረኝ እኔ ምንተዳዬ
ከሰቀሉህ ጋራ ልስቀልህ ጌታዬ
እንዲ ነኝ መጻጉዕ ውለታ የምረሳ
ስወድህ እንድኖር ህመሜን አትፈውስ ቀንበሬን አታንሳ
ስንኩል ነው የኔ እግሬ ለሐሰት ያጋደለ
ጠማማ ነው ልቤ ፍቅርህን የጣለ
ቀጤማ ነው እጄ ክፋት ያቃጠለው
ያዙት ያን ክርስቶስ ብሎ የሚጠቁመው
እውር ነው ብሌኔ እያየ የሚከዳ
ከደግነት ኩሬ መአት የሚቀዳ
እዳ ነኝ ለራሴ እዳ ነኝ ለዓለም
ሲጀመር ነው የካድኩህ ሲፈጸም አይደለም
ከወንዙ ጥግ ሆኜ በአልጋዬ ላይ ሳለሁ
አምንብህ ነበረ ስትፈውስ እያየሁ
አልጋህን ተሸከም ስትለኝ ምን አልባት
ልቤን አናተበው የመራመድ ክፋት
አትማረኝ መድኅኑ በአልጋዬ ላይ ልክረም
አልጋዬን መሸከም ለኔ መጥፋት እንጂ መፈወስ አይደለም
እባክህ ክርስቶስ እባክህ ጌታዬ
አንተን ከምከዳ አልጋዬን አዝዬ
የዳዊት ልጅ ተወኝ አትፈውሰኝ ይቅር
መች እክድህ ነበር ልክ እንዲህ ከነበር ::

ዳዊት አየነው
@Mgetem
@Mgetem_group
@Mgetem