Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ (ውርስ ትርጉም) ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ @Mgetem “ብላቴና” | መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
@Mgetem

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
መነሻ ቅኔ ፦ ዕዝል ጉባዔ ቃና
ዘመሪጌታ ጥበበ ደስታ

ሕፃን ኢያእመሬ ነፍስ ዓዲ፤
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ
.......................................................
መፃጕዕ ለ 38 ዓመት ሲማቅቅበት ከነበረ ደዌው የፈወሰው ክርስቶስን በቤተመቅደስ በጥፊ ስለ መምታቱ መሪጌታ ጥበበ ደስታ የተቀኙትን ቅኔ መነሻ በማድረግ የተገጠመ
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ
.......................................................
@Mgetem
@Mgetem
@Scgpx9