Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mgetem — መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mgetem — መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
የሰርጥ አድራሻ: @mgetem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.79K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
.
.
.
.
.
.
.
.
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Mgetem_Bot
@Mgetem_group

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-10-15 17:15:46 የኢትዮጵያን ነገር…..

አባ አባ ብዬ - በለመንኩህ ለቅሶ - ተሰምቷል ጩሀቴ
በውን ያስጨነቀኝ - ተራራው ፈተና - ተነስቷል ከፊቴ
የተማመንኩበት - የሥምህ ስንቅነት - አንዳች አልጎደለ
ተስፋ ያደረግሁት - የጸሎትህ ሥምረት - በሕይወቴ አለ
የተደገፍኩበት - የደጅህ ዋስ’ነት - ሜዳ አልጣለኝም
እንባ የረጨሁበት - የ’ስማኝ!’ ዋይታዬ - አልወደቀብኝም
ከህጻንነቴ - አንተን ተማምኜ - የሄድኩበት መንገድ
በጥቅጥቁ ጫካ - አንበሳው አልነካኝ - አልሆንኩ አልቦ ዘመድ
ልጅነቴ ሁሌ - ገብረ ሕይወት እያለች -በምልጃህ ተማምና
ትናንት እንዳልተውካት - ዛሬም ስትጣራህ -ለነፍሴ ጭንቅ ና፡፡

Abboo! - Aabboo! ብዬ - ሀገር አሻግሬ - ስምህን እጠራለሁ
ከግብጽ በረሃ - ለምትሻህ ኢትዮጵያ - ቶሎ ና እላለሁ
ታስፈልጋታለህ - እንኳንና ለሰው - ለአናብስት ሁሉ
የጽድቅህን ፍሬ - የቀመሱ ነፍሳት - አባ አባ ይላሉ
የንጽኅናህ ግርማ - ከግብጽ እስከ ኢትዮጵያ - ሀገር እያወደ
አንበሳውም ነብሩም - እያገለገለህ፣- አንተን እያጀበ- ካንተ ጋራ ሄደ፡፡
አቡዬ ና ድረስ- ና ገስግስ ዘንድሮም - ቶሎ ና ለሀገሬ
እረፉ በላቸው - እንዳይናከሱ - ሰውንና ሰውን - ሰውንና አውሬ፡፡

ዛሬም ቁም ዝቋላ - ግባ ከባህሩ - እጆችህን ዘርጋ
ፈልግ ልጆችህን - የጸሎት ፍሬህን - የጠበቅኸውን መንጋ
ከሰሜን ከደቡብ - ከምስራቅ ከምዕራብ - የተጋደልህለት
“ኢትዮጵያን ማርልኝ !” - ብለህ ከአምላክህ ፊት - ብዙ የጸለይክለት
የረገጥከው መሬት - ያረፍክበት ደብር - የነካህ አፈሩ
ዳግም በዛሬው ቀን - ጸሎትህን ይሻል - መላው ሀገሩ
ምድረ ከብድ ድረስ - ተገኝ በዝቋላ - አንሳ እጆችህን
እስከምንጠገን - ተሰብረናልና - እየን ልጆችህን
አታሳፍረንም - ገብረ መንፈስ ቅዱስ - ብለን ስንጠራህ
እንግዲህ አቡዬ - የኢትዮጵያን ነገር - አሁንም አደራህ!!






5.0K viewsOl, 14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 12:36:25

4.3K viewsK, 09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 07:20:01 አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ


4.5K viewsOl, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 19:10:31

4.7K viewsK, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 19:56:15 እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ የጽንሰቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ያልተወለደው ባለ ቅኔ ከዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ


932 viewsOl, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 15:32:42 እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ የጽንሰቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ያልተወለደው ባለ ቅኔ ከዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ






1.1K viewsOl, 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 15:29:28
ፃድቁ አቡነ ሃብተማርያም በቃልኪዳን ማዕጠንታቸው ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ የጸለየችውን ጸሎት ያሳርጉልን።





901 viewsSol, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 10:29:44
ግሸን ማርያም !
።።።
ኤልያስና ኤልሳ በእድሜ ገርጅፈው
ልጄ 'ማይሉትን...
ደፍረው 'ማይቀርቡትን...
አቅፋ ስማዋለች በ አስራምስት ዓመቷ
ድንግል ወላዲቷ
.
ሰዎች ውሸት አሉ ማረጓ ተናቀ
ግና...
አዲስ ሰማይ አይቶ ሰማይ ተደነቀ
.
በማህፀን እሳት ... መለኮትን ማጀብ
አጀብ!
.
የዓለም ትልቁን በማህፀን ይዛ
ማማለድ አትችልም አለኝ ያ ፈዛዛ
አሁን ምን ይሉታል ለትልቁ ታጭቶ ትንሹን መከልከል
እንደዚህም አይደል !
.
አለቀብን ወይን ሳሳብን ማጀቱ
እሱ ግን ባረከው ስትነግረው እናቱ
ቅጠል ለቅሞላታል ያኔ ህፃን ሳለ
ወላጅህን አክብር
ይሉት የኦሪት ህግ እንዲሁ ቀጠለ...
.
ተከትዬህ ከጫፍ መስቀልህ ስር ቆሜ
በመለየት ፍርሀት በፅኑ ታምሜ
ሳለቅስ ሲከፋኝ ስደበት ሳነባ
ድንግልን ሰጠኸኝ የሞገሴን ካባ !
Michael Aschenaki
@Mgetem
@Mgetem
1.7K viewsSol, 07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 08:25:07

1.6K viewsK, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 19:19:44

639 viewsK, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ