የኢትዮጵያን ነገር….. አባ አባ ብዬ - በለመንኩህ ለቅሶ - ተሰምቷል ጩሀቴ በውን ያስጨነቀኝ - ተራራው ፈተና - ተነስቷል ከፊቴ የተማመንኩበት - የሥምህ ስንቅነት - አንዳች አልጎደለ ተስፋ ያደረግሁት - የጸሎትህ ሥምረት - በሕይወቴ አለ የተደገፍኩበት - የደጅህ ዋስ’ነት - ሜዳ አልጣለኝም እንባ የረጨሁበት - የ’ስማኝ!’ ዋይታዬ - አልወደቀብኝም ከህጻንነቴ - አንተን ተማምኜ - የሄድኩበት መንገድ በጥቅጥቁ ጫካ - አንበሳው አልነካኝ - አልሆንኩ አልቦ ዘመድ ልጅነቴ ሁሌ - ገብረ ሕይወት እያለች -በምልጃህ ተማምና ትናንት እንዳልተውካት - ዛሬም ስትጣራህ -ለነፍሴ ጭንቅ ና፡፡ Abboo! - Aabboo! ብዬ - ሀገር አሻግሬ - ስምህን እጠራለሁ ከግብጽ በረሃ - ለምትሻህ ኢትዮጵያ - ቶሎ ና እላለሁ ታስፈልጋታለህ - እንኳንና ለሰው - ለአናብስት ሁሉ የጽድቅህን ፍሬ - የቀመሱ ነፍሳት - አባ አባ ይላሉ የንጽኅናህ ግርማ - ከግብጽ እስከ ኢትዮጵያ - ሀገር እያወደ አንበሳውም ነብሩም - እያገለገለህ፣- አንተን እያጀበ- ካንተ ጋራ ሄደ፡፡ አቡዬ ና ድረስ- ና ገስግስ ዘንድሮም - ቶሎ ና ለሀገሬ እረፉ በላቸው - እንዳይናከሱ - ሰውንና ሰውን - ሰውንና አውሬ፡፡ ዛሬም ቁም ዝቋላ - ግባ ከባህሩ - እጆችህን ዘርጋ ፈልግ ልጆችህን - የጸሎት ፍሬህን - የጠበቅኸውን መንጋ ከሰሜን ከደቡብ - ከምስራቅ ከምዕራብ - የተጋደልህለት “ኢትዮጵያን ማርልኝ !” - ብለህ ከአምላክህ ፊት - ብዙ የጸለይክለት የረገጥከው መሬት - ያረፍክበት ደብር - የነካህ አፈሩ ዳግም በዛሬው ቀን - ጸሎትህን ይሻል - መላው ሀገሩ ምድረ ከብድ ድረስ - ተገኝ በዝቋላ - አንሳ እጆችህን እስከምንጠገን - ተሰብረናልና - እየን ልጆችህን አታሳፍረንም - ገብረ መንፈስ ቅዱስ - ብለን ስንጠራህ እንግዲህ አቡዬ - የኢትዮጵያን ነገር - አሁንም አደራህ!! 5.0K viewsOl, 14:15