Get Mystery Box with random crypto!

ግሸን ማርያም ! ።።። ኤልያስና ኤልሳ በእድሜ ገርጅፈው ልጄ 'ማይሉትን... ደፍረው 'ማይቀርቡትን | መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

ግሸን ማርያም !
።።።
ኤልያስና ኤልሳ በእድሜ ገርጅፈው
ልጄ 'ማይሉትን...
ደፍረው 'ማይቀርቡትን...
አቅፋ ስማዋለች በ አስራምስት ዓመቷ
ድንግል ወላዲቷ
.
ሰዎች ውሸት አሉ ማረጓ ተናቀ
ግና...
አዲስ ሰማይ አይቶ ሰማይ ተደነቀ
.
በማህፀን እሳት ... መለኮትን ማጀብ
አጀብ!
.
የዓለም ትልቁን በማህፀን ይዛ
ማማለድ አትችልም አለኝ ያ ፈዛዛ
አሁን ምን ይሉታል ለትልቁ ታጭቶ ትንሹን መከልከል
እንደዚህም አይደል !
.
አለቀብን ወይን ሳሳብን ማጀቱ
እሱ ግን ባረከው ስትነግረው እናቱ
ቅጠል ለቅሞላታል ያኔ ህፃን ሳለ
ወላጅህን አክብር
ይሉት የኦሪት ህግ እንዲሁ ቀጠለ...
.
ተከትዬህ ከጫፍ መስቀልህ ስር ቆሜ
በመለየት ፍርሀት በፅኑ ታምሜ
ሳለቅስ ሲከፋኝ ስደበት ሳነባ
ድንግልን ሰጠኸኝ የሞገሴን ካባ !
Michael Aschenaki
@Mgetem
@Mgetem