Get Mystery Box with random crypto!

Abdurahman Seid (ሜጢ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mettiey — Abdurahman Seid (ሜጢ) A
የቴሌግራም ቻናል አርማ mettiey — Abdurahman Seid (ሜጢ)
የሰርጥ አድራሻ: @mettiey
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.22K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-06 18:39:27 ነቢዩላህ ሙሣን (ዐ.ሰ) በዘዴ ያጨችው ወጣት [ ከሱራ አል ቀሶስ የሚወሰድ ትምህርት || በኡስታዝ ኑዕማን ዓሊ ኻን [ NAK Amharic Studios ]

ዘወትር ቅዳሜ ተርጉመን የምናቀርበውን የቁርኣን ፕሮግራም እነሆ! ከወደዱት አይተው ለሌሎች ያጋሩ!

[

]
446 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 01:09:26
ኺታሙሁ ሚስክ

ከነብያችን (ሰዐወ) አገር ጠይባ ዚያራ ካለቀና ከጅዳ ጥቂት ቀናት ቆይታዬ በኋላ፣ ፕሌን ውስጥ አንድነትን፣ወንድማማችነትንና መከባበርን ሲያስተምሩና ሲኖሩ እኔ በግሌ ከማውቃቸው ስብዕና ጋር ወንበር ተጋራሁ። እርሳቸውም ፈዲለቱ ሸይኽ ዶክተር ጀይላን ኸድር ገመዳ ናቸው።

አብረን ስለተመለስን አልሐምዱሊላህ ብለው ጨበጡኝ። ፕሌኑ ተነስቶ ወደ አየር ሲገባ የሰፈር ዚክር አብረን አልን። እነሆ ከተቀመጡ ጊዜ አንስቶ ምላሳቸው አላህን ያወሳል፣ በመሃል ስለ ኢስላምና ሙስሊሙ ጉዳይ ሐሳብ ያነሳሉ።

በሁለት ረከዓም ቢሆን በተቀመጥንበት ዊትር እንስገድ አሉና የሱረቱል ዒምራንን የመጨረሻ ገፆች አነበቡ። እነሆ የዊትርንም ዱዓ አደረጉ። በስተመጨረሻም ውድና ልዩ ምክሮችን ለገሱኝ።

መሰል ስብዕናዎች በሕይወት አጋጣሚም ይሁን በመኗኗር ውስጥ የሚጥሉብን አሻራ አብሮ ይቆያል። ሁሉንም ከተግባር የተቆራኘ የእውቀት ባለቤቶችን እድሜ ጀሊሉ ያርዝመው።

https://t.me/mettiey
559 views22:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 19:58:43
688 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 19:57:40 አስሐበን -ነቢ የረሱል ጓዶች
የፅናት አምሳል የመርህ ወዳጆች
ዘማች እግረኛ የኡማው ፈርጦች
ለቅኑ መንገድ ከዋክብት ጌጦች።

(ከባቲ ወንድሞች የዜማ ግጥም የተወሰደ)

ሙስዓብ የመካውያኑን ሙሽሪኮች ትኩረት ከነብያችን ወደርሱ ለማድረግ የኢስላምን ባንዲራና ከርሳቸው ጋር በመልክ መመሳሰሉን ተጠቀመ። ተረባርበው ገደሉት። ሙሐመድን ገደልነው ብለውም ወበሩ። የርሱም አወዳደቅ በፊቱ ከመሆኑ ጋር አፈር ውስጥ ድብቅ ነበር ያለው። የታሪክ ፀሃፊያኑ "ያንቱን ሞት ከማይ ቀድሜ ልሙት" ያለ ነበር የሚመስለው ይላሉ።

ያ የሙስዓብ ኢብኑ ዑመይር ቀብር ነው ብለው ሲያሳዩዋችሁ አንዳች ስጋ ከአካል ተቆርጦ የሚረግፍ ያህል ነው ንዝረትና ህመሙ። ያ ቅምጥል ለግላጋ ወጣት ከፈን አጥቶ በቅጠል ሲቀበር ክስተቱ በሐሳብ ግጥም ይላል። ነብዩ ጀናዛው አጠገብ ሆነው 'ሙስዓብን መካ ጎዳናዎች ላይ በቅምጥል ህይወት አውቀዋለሁ፣ ዛሬ ደግሞ መከፈኛ አጣ፣ ሙስዓብ ሆይ ሰላም ባንተ ላይ ይሁን ሰላም በናንተ ላይ ይሁን የኡሑድ ሰማዕታት ሆይ ሲሉ ድምፃቸውን የሰሙ ያህል መስሚያን ያንኳኳል።

ይህ ጀበሉ-ር-ሩማት  ሲሆን በነብያችን (ሰዐወ) ልዩ የጦር ሜዳ ላይ ንባብ ቀስተኞች ከበው ከላዩ ላይ ሳይወርዱ የመካን ሙሽሪኮች ድንገተኛ ጥቃት ይመክቱና ቀስት ያስወነጭፉባቸው ዘንድ ጥብቅ ትዕዛዝ የተሰጠበት ቦታ ነው።

ነብያችን ሙተዋል ስለተባለ ብቻ ሶሐባው ሁሉ ውሉ ጠፍቶበታል። ሙሽሪኮቹ ያለምንም ርህራሄ እየተከታተሉና እያደኑ ይገድሏቸው ይዘዋል። እርሳቸው ሞተው የኛ መኒር ትርጉም ምንድንነው በሚል የቻሉትን ታግለው ይወድቁ ይዘዋል።

የኛ ነብይ ግን በዚያች ትዕዛዝ መጣስ የተነሳ በዙሪያቸው ጥቂት ሶሐቦች ብቻ እየተከላከሉላቸው እዚያው ኡሑድ ባለ አንድ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ። ጥርሳቸው ተሰበረ። የብረት ቀለበት የግንባር አጥንታቸውን ሰብሮ ገባ።

በዚህ የተሰባበረ አካላቸውና ህመማቸው መሃል እንኳ ሆነው መለኮታዊ ተልዕኳቸውን አልዘነጉም። የሰውነት ድክመትና ትክትና አልጎበኛቸውም። በርግጥ አካላቸው ዝሏል፣ ኃይላቸው ደክሟል።

ከዚያ ከወደቁበት ተነስተው የዛለ አካላቸውን ይዘው ብትንትኑ የወጣውን ሰሐባ ሁሉ ለመሰብሰብ ከፍታ ቦታ ለማማተር እያዩ ባለበት ቅፅበት ከዕብ ኢብኑ ማሊክ (ረዐ) አያቸውና በደስታ "ረሱለሏህ በሕይወት አሉ" ብሎ አንዴ ሲናገር በርሱ የደስታ ስህተት የጠላት ዒላማ እንዳያገኛቸው በእጃቸው ምልክት "ቆይ አንዴ ዝም በልማ" አሉት።

ከፍ ወዳለው ተራራ ለመውጣት ቢፈልጉም የአካላቸው ዝለት፣ ቁስለትና ስብራት አቀባቸው። በክንዶቹ ወደርሳቸው ሲወረወሩ የነብሩ ቀስቶችን ሲከላከል የነበረው ጦልሐ ኢብኑ ዑበይዲላህ (ረዐ) ጎንበስ ብሎላቸው በትከሻው ላይ ተወጣጡ። 'ጦልሐ ጀነትን አፈሰ አሉ'።

እነሆ ሰሐባው ሁሉ ወኔው ተሰበሰበለት። በደንብ ተዋግተውም ከመጀመሪያው ዙር ሽንፈት በኋላ መከላከል ቻሉ። የኢስላምን ባንዲራ ከሙስዓብ መሰዋት በኋላ ዓሊይ ያዟት። ከዚያች ቅፅበት በኋላ አልወደቀችም።

ያ የሐምዛ ቀብር ነው ሲሉህ አላህ ለነብዩ በአስቸጋሪ ጊዜ መከታ እንዴት እንዳደረገላቸው፣ በዚህ ዘመቻም የአካል ክፍላቸው መቆራረጡ የነቢን ሐዘን እንዴት እንዳበረታው፣ የሐምዛ እህትና የርሳቸው አክስት ሰፊያ የሐምዛን አካል እንዳታይ ረሱሉ አርቋት እንዳታይ ማለታቸው ሁሉ በሐሳብ ግጥም ይላል።

ሲራን ላነበበ፣ የሰማዕታቱን ገድል ላስታወሰ ሁሉ ትኩስ መርዶ ነው። ለኢስላም መቋቋም የተከፈለን ዋጋ ሁሉም በእዝነ-ህሊናው ያመጣል። ሳያስበው ልቡ ትመታለች፣ ዓይኖቹም ያነባሉ።

የሙስሊም ወንድም ክብርና የሙስሊሞች ህብረት ልክ እንደዚህች ተራራ ናት። ችላ ብለህ የለቀቅካትና የተረማመድካት ጊዜ አንተንም ሌሎችንም ለኻሊድ አይነቱ ስትራቴጂስት አሳልፈህ ትሰጣለህ። በመጨረሻውም ዙር ተቀርጥፈህ የምትበላው ጥቁር በሬም አንተው ትሆናለህ። ተራራውን ጥብቅ። ትግልና ፍልሚያህን ግን ለቅፅበትም እንዳትተው።

መልካም ለይለተል ጁምዓ
871 views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 15:05:53
የሙስሊሞች ጉዳይ ²

ታላቅ የዳዕዋና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጎዴሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ:-
ግዙፉን የሜጢ ኑር መስጂድ ግንባታ ለማጠናቀቅ እና በእውቀት የበለፀገ ማዕከል ለማድረግ የረዥም ጊዜ እቅድ የተያዘለትን አካዳሚክ ት/ቤት እና ኢስላማዊ ማዕከል (መርከዝ) ግንባታ ለማስጀመር በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ ኑር መስጂድ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ግንቦት 06/2015 ይካሄዳል።

በእለቱም:-
ኡስታዝ አቡበክር አህመድ
ኡስታዝ አህመድን ጀበል
ኡስታዝ መሐመድ ፈረጅ
ኡስታዝ አብዱልመናን (አቡ ያሲር)
ኡስታዝ ሀይደር ከድር
ኡስታዝ ሸኽ ዩሱፍ አህመድ (ቴፒ)
ሸኽ ዛኪር ኢብራሂም....
እና ሌሎችም አንጋፋ የሀገራችን ኡለሞች፣ ኡስታዞች፣ ዳኢወችና የተለያዩ የመንግስት ባለድርሻ አካላትይገኛሉ።

በዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ በአካል በመገኘት ይህንን መስጂድ፣ አካዳሚክ ት/ቤት እና ኢስላማዊ ማዕከል (መርከዝ) ግንባታ በመደገፍ ዛሬ ለአላህ ትልቅ ብድርን አበድረው ለነገው የአኼራ ቤትዎ በእጥፍ ይሸምቱ ዘንድ ሁላችሁም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እንድትታደሙ ተጋብዛችኋል።

የመስጅዱ አካውንት ስም:-ኑር መስጂድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:-1000075561249
አዋሽ ባንክ:-014221154206200
1.2K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 09:51:42 Channel photo updated
06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:46:59
ረመዷን ³⁰

ዒድ ሙባረክ

አላህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን። አላህ ዐዘ ወጀል ወሩን አስፁሞ ስላስጨረሰን ምስጋና ይድረሰው። ኡማችን ከፍ ትበል፣ ምድራዊ የምትክነት ሚናዋንም የምትወጣ ያድርጋት።

https://t.me/mettiey
228 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 20:28:35 "ዐረቦች ሰላሑዲን አል-አዩቢን ከ1000 ዓመታት ጀምሮ በናፍቆት ይጠብቁታል። ዛሬ ቢመጣ ግን ከሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ያስገቡት ነበር።" (ማሕሙድ አል-ሐሰናት)
774 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 05:04:12
ረመዷን ²³

ምላሹ ትንሽ ይዘገያል

አላህ በአንተ ጉዳይ የሚያመቻቸው ጉዳይ ስላለ ምላሹ ትንሽ ይዘገያል። ልብ ውስጥ ትንሽ ድርቀት ስላለ አላህ ለማለዘብ ጊዜን ይወስዳል።

- ልብ ውስጥ በአምልኮ የመኮፈስ
- ለራስ የተጋነነ ልኬት የመስጠት ስሜት እስኪሟሽሽ፣
- ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ የምትል ብልሹ ንፅፅር እስኪቀልጥ፣  
- ኃጢአት ላይ ለተነከረ ሰው ከማዘን ይልቅ አሳንሶ የማየት ክፉ ባህሪ እስኪጠፋ ድረስ የዱዓ ምላሽ ጊዜን ይወስዳል። ከዚያ ግን "አል-ሙጂብ" መልስ ይሰጣል።
--_____________________--

لَتَرْكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٍ

ከኹኔታ ወደ ሌላ ኹኔታ ትለዋወጣላችሁ፡፡ (አል-ኢንሺቃቅ 19)

- ካላችሁበት ጠጨባጭ ወደ ተሻለው
- ከመጣበብ በኋላ ወደ መስፋፋት
- ከህመም ወድ ጤንነት
- ከሐዘን ወደ ደስታ
- ከመለያየት በኋላ ወደ መገናኘት ትመጣላችሁ

ምድራዊ ሕይወት በአንድ ገፅታ አትዘወትርም። ሰዎች በውስጧ የተለያየ ሁኔታን ያሳልፋሉ። እድለኛ ግን አላህ ጋር በአንድ ሁኔታ የዘወተረ ነው። (ከመፅሐፍት የተወሰደ)

በአላህ ላይ መልካምን እንጠርጥር

https://t.me/mettiey
131 views02:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 22:20:11
"ሰዓታትን ሸጦ 83 ዓመታትን የማይገዛ ሰው ሲበዛ ቸልተኛና የተሸወደ ነው።" (ሸይኽ ጡረይፊ)

لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ

መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ (አል-ቀድር 3)

ለሊቱ 23ተኛ ስለሆነና ከጁሙዓ ለሊት ጋር ስለገጠመ ለይለቱል ቀድር ሊሆን ይከጀላል ይላሉ ቀደምት ዑለሞች።

ቁርአን፣ ኢስቲግፋርና ዱዓ ማብዛት በተለይ

اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ كَرِيمٌ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عني

"አላህ ሆይ አንተ (ያለ ገደብ) ይቅር ባይ ነህ፣ ይቅርታንም ትወዳለህ፣ ይቅር በለኝ።" ማለትን ማብዛት የነብያችን (ሰዐወ) ምክር ነው።

ብልጥ ማለት ቅፅበትም ትሁን ዕድልን የሚጠቀም ነው።
319 views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ