2023-03-27 05:36:50
ረመዷን ⁵
እኔን ጨምሮ
- ምድራዊና ቁሳዊ ጉጉታችን እጅግ ስለበዛ፣
- አኺራ አለብን ብለን የምናስበው ሳንቀር እዚሁ ፍላጎት ስር ችንክር ብለን ስንቀርና፣
- አኺራን ባንክድም ለዱንያ የምንሰጠውን ያህል ትኩረት ስንነፈገው ጊዜ ነው ከሰሞኑ በዚህ ረመዷን ተጨንቄ የማስጨንቃችሁ።
እስቲ እነዚህን የሱረቱል ሙእሚኑን ተከታታይ አናቅፅ እንመልከትማ። ስለ ሰው ልጅ የአፈጣጠር እርከኖች ይናገራል። አብረን ሕይወትን እንፈልጋለን እሺ
وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ
12) በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡
ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ
13) ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡
ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ
14) ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡
ثُمَّ إِنَّكُم بَعْدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ
15) ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ፡፡
አሰባችሁት ግን ? ታዲያ ሕይወት የት አለች? አስደንጋጭ አይደል? ይህን ሁሉ አስደናቂ አፈጣጠር ዘርዝሮ እየነገረን መጥቶ ምድር ላይ ትኖራላችሁ አላለም። ልክ የሆነች ቅፅበት አድርጎሳይጠቅስ አለፋትና ቀጥታ ወደ ሞት ሄደ። ሱብሐነል መሊክ! ለመጠቀስና መወሳት እንኳ ብቁ አይደለቺም። አላህ በቅዱስ ቃሉ ዘለላት።
ነብያችን (ሰዐወ) እንዲህ ይሉናል:-" ዱንያ ከአኺራ አንፃር አንዳችሁ አውራ ጣቱን ባህር ውስጥ አስገብቶ ይዛ የምትወጣውን ያህል መጠን እንጂ ሌላ አይደለችም።"
እስቲ ከዚህች ጣት ላይ ድርሻችንን እንፈልግ! ምን ያህል ናት? ለዚህች ዱንያ ነው አኺራ የሚሸጠው፣ ሰው እንዴት ጣቱ ላይ ባለች እርጥበት ከባህር ውሃ ይብቃቃል? ለርሷ ሲባል ወንጀል ይሰራል፣ ዝምድና ይቆረጣል፣ ታላቁን አምላክ እናስከፋለን። ዐቅል ያለው ሰው ይህን አያደርግም።
ኢስላም ሁሉን ትቶ ቁጭ ማለትን፣ ሌሎች ላይ ጥገኝነትንና ስራ አለመስራትን እጅግ ይጠላል። እንደውም ተከታዮቹ በራሳቸው የተብቃቁና ቁሳዊ ሕይወታቸው ሚዛናዊነትን የተላበሰ፣ ከምድርም ድርሻቸውን እንዳይረሱ አነሳሽ እምነት ነው። ድንበር አልፎ፣ ፍጡራንን ረጋጭና ፈጣሪን አስቆጭ እንዳይሆንም ይመክራል።
https://t.me/mettiey
447 views02:36